TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመጠጥ ውሃ ተመርዟል የተባለው ውሸት ነው!

በሀዋሳ ከተማ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየተናፈሰ ስለሚገኘው "የውሃ መመረዝ" ጉዳይ የሀዋሳ ከተማን የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ምክትል ስራ አስኪያጅ ክቡር አቶ ደምሴን በስልክ አነጋግሬያቸው ያገኘሁት ምላሽ ይህ ነው፦

"ምንም የተፈጠረ ነገር የለም! የከተማውን ህዝብ ለማሸበር የተደረገ ነገር ነው። ውሃው ለንደሱ አይነት ነገር/ለመመረዝ/ እድል የለውም። 24 ሙሉ በቂ ጥበቃ አለ። በውሃው #መስመር ላይም ለመመረዝ የሚሆን ምንም እድል የለም። እየተወራ የሚገኘው ሀዋሳ ብቻ አይደለም አለታ ወንዶ፣ ይርጋለም፣ ወንዶ ገነት፣ ...ምንም ነገር አልተፈጠረም የፈጠራ ወሬ ነው። ህዝቡም እንዲያውቀው በመገናኛ ብዙሃን ይገለፃል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia