TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ጉብኝት ለመጀመር በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የሚገባ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የጉብኝቱ አላማ የሀገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ነው ተብሏል። የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑኩ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆያታ በተለያዩ ዝግጅትቶች ተሳታፊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ልዑኩ የፊታችን የካቲት 9 ቀን ባህርዳር፣ የካቲት 10 በአዳማ፣ የካቲት 12 በሀዋሳ እና የካቲት 14 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተሞች በሚካሄዱ ባህላዊ #የሙዚቃ_ኮንሰርቶች ተሳታፊ ይሆናል ተብሏል። ለዚህ ባህላዊ የሙዚቃ ኮንሰርትም #ሁሉም ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊያን ተሳታፊ እንዲሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። በሚቀጥለው ወርም የሁለቱ ሀገራትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ  ለማጠናከር የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ  ወደ ኤርትራ የሚያቀና መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በሚገኙ #ሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ልዩ ወረዳዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ #ታውጇል#ETHIOPIA

#State_of_emergency

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ካምቦዲያ ከኮቪድ-19 ታማሚዎች #ነፃ ሆነች!

በካምቦዲያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 122 ሰዎች መካከል #ሁሉም በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው ማገገማቸው ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት የመጨረሻዋ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ (የ36 ዓመት ሴት) ከሆስፒታል ወጥታለች።

ካምቦዲያ ከሚያዚያ 4/2012 ዓ/ም በኃላ አዲስ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ኬዝ ሪፖርት አላደረገችም።

የሀገሪቱ መንግስት አሁንም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የጣላቸውን ገደቦች አላነሳም። ትምህርት ቤቶች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው ፤ በድንበር አካባቢ የሚደረገው ቁጥጥር እንደተጠናከረ ነው፤ ኳረንታይንም ቀጥሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪ ከጤና ሚኒስትሯ ውጭ #ሁሉም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብረ ኃይል አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ለቢቢሲ #አረጋግጠዋል

በኮቪድ-19 የተያዙት ሁሉም ሚኒስትሮች በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሲሆን በሙሉ ጤንነትም ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ የባለስልጣናቱ ጠባቂዎች እንዲሁም ሠራተኞች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በለይቶ ማቆያ ውስጥም ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በኮቪድ-19 ተይዘዋል የሚለውን ሪፖርት #አጣጥለውታል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ #ሁሉም አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች ከመጪው ሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፊትና የአፍ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታ እንደሚኖርባቸው አሳውቋል።

ይህን መመሪያ በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ መምሪያው በጥብቅ አስታውቋል፡፡

መመሪያው በመላው ሀገሪቱ #እየጨመረ የሚገኘውን ፤ እንዲሁም ወደ ከተማው የመግባት አዝማሚያ እያሳየ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ይረዳል ተብሎ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ረዳቶችና ተሳፋሪዎችን ፤ እንዲሁም የግልና የመንግስት መኪና አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎችን፤ ባጃጅና የመሳሰሉትን አነስተኛ የትራንስፖት ዘርፎች የሚያካትት ነው።

አሽከርካሪዎች ይህንን አውቀው በቀጣይ ሁለት (2) ቀናት ውስጥ ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የፊት ማስኮችን አድርገው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡

#SRTA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት እና ግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል " የማለፊያ ውጤት ያላመጡ " ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ…
#ውሳኔ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን አስመልክቶ ውሳኔ መተላለፉን አሳውቋል።

ከውሳኔዎቹ አንደኛው ከዚህ በፊት በተላለፈው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግባት ከቻሉት የክልሉ ተማሪዎች በተጨማሪ 4339 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ እንዲያገኙ ተወስኗል ብሏል።

እነዚህ 4339 ተማሪዎች እንዴት እና በምን አግባብ ቅበላ ሊያገኙ እንደቻሉ (የተበላሸ ውጤታቸው ተስተካክሎ ወይስ ሌላ ስለሚለው) ቢሮው ዝርዝር ማብራሪያ አልስጠም።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሌላ ተላልፏል ያለው ውስኔ ፥ በ2013 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመግቢያ ነጥብ ያላሟሉ የክልሉ #ሁሉም_ዞኖች ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመደበኛ ተማሪነት (as regular students) መፈተን እንደሚችሉ ነው።

ቢሮው ፤ ትምህርት ሚኒስቴር የውጤት መቁረጫ ነጥብ ተወስኖ እና ያለፉት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻው ቀን ከተወሰነ በኋላ ከአማራ ክልል በተነሳ ቅሬታ መነሻነት ቅሬታውን አዳምጦ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ማድረጉ ትልቅ መደማመጥ የተስተዋለበት ነበር ሲል ገልጿል።

" ይህም ለቀጣይ በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ የሀገር ግንባታ ጉዟችን አንድ ማሳያ ነው ብለን እናስባለን " ሲል አክሏል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከተፈጠረው ችግር አኳያ ውሳኔው ያላረካቸው አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል ያለ ሲሆን የክልሉ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እድሉን በድጋሜ ማግኘታቸውን እንደ ትልቅ አጋጣሚ አድርገው ለውጤታማነት እንዲጠቀሙበት አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ሀገራዊ_ምክክር 🇪🇹

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" በሀገራዊ ምክክሩ #ሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ የሚያስይዝበት አሰራር ይዘረጋል።

የውይይት ሃሳቦች ከታች ወደ ላይ ነው የሚሰበሰቡት።

በውይይቱ ይህ ይነሳ ያ አይነሳ የሚባል ነገር የለም ። ኮሚሽኑ በአጀንዳዎች ላይ ጣልቃ አይገባም።

ምክክሩ ልሂቁ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሐሳቡ በጥቂቶች እንዳይጨናገፍ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን።

በቀጣይ በየክልሉ እንደ አመቺነቱ ጽሕፈት ቤቶች ይቋቋማሉ ፤ የኮሚሽኑ ምክር ቤት መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን ስትራቴጂክ ዕቅዱን ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ግብዓት ይሰበሰባል።

አጀንዳ የመሰብሰብ ሥራ በገጽ ለገጽ ማህበረሰቡ በሚረዳው ቋንቋ ስለ ኮሚሽኑ በማስረዳት ሃሳቡን እንዲገልጽ ይደረጋል። በሌሎች አማራጮችም በስልክ፣ ኢሜይል እና ፖስታ በመሳሰሉት ማቅረብም ይቻላል።

ማሕበረሰቡ ሃሳቡን ከማቅረብ በተጨማሪ በማዕከል ደረጃ ለሚደረገው ምክክር ወኪሎቹን እንዲመርጥ ይደረጋል።

የአጀንዳ ሃሳቦች መሰብሰብ የሚጀመርበት ጊዜ #በቅርቡ_ይፋ ይደረጋል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 #በኢትዮጵያ_መንግስት እና #በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይዘት የሚገልፅ 12 ነጥብ ያለው #የጋራ_መግለጫ ከላይ ተያይዟል። ነገ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለትና ህዝቡም እረፍት እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ፣ አርሶ አደሮችም ወደ እርሻቸው ፣ ሰራተኞችም ወደ ስራቸው፣ ነጋዴዎችም ወደንግዳቸው እንዲመለሱ አጠቃላይ…
ስለ " ሰላም ስምምነቱ " ምን ተባለ ?

🕊 የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኢትዮጵያ ለሰላም ያላት ቁርጠኝነት አሁንም የፀና መሆኑን ገልፀው " ስምምነቱ #ወደተግባር እንዲለወጥ አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ጠንካራ አቋም / ቁርጠኝነት አለን " ብለዋል።

🕊 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (አንቶኒዮ ጉተሬዝ) ፦

በደቡብ አፍሪካ የተደረሰው የ " ሰላም ስምምነት " የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈውና ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን አስከፊ ጦርነት ለማስቆም ወሳኝ የሆነ የመጀመሪያ እርምጃ ነው ብለዋል።

#ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል አመራሮች ለሰላም የወሰዱትን እርምጃ እንዲደግፉ አሳስበዋል።

የጦርነት ማቆም የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ለተቸገሩ ሰላማዊ ዜጎች ሁሉ ሰብአዊ እርዳታን ከፍ ለማድረግ እና በጣም አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

🕊 አሜሪካ ፦

ከአፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ፣ ኢጋድ እና ከሌሎችም ጋር በመሆን የተደረሰው ስምምነት #ተግባራዊ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ድጋፏን እንደታደርግ ገልጻለች። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነቱ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እና ለልማት ያላቸውን ፍላጎት እንደምትደረግፍም አሳውቃለች።

🕊 የአውሮፓ ህብረት (ጆሴፕ ቦሬል) ፦

የሰላም ስምምነቱ ባስቸኳይ ሊተገበር ይገባል ያሉ ሲሆን በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ማቅረብ ፤ በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንደገና መጀመር #ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-03

@tikvahethiopia
#Update

" ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየር እና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል " - የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

ዛሬ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፤ ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ #ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብአዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን አስታውቋል።

የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።

ይህ የተገለፀው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለተለያዩ #ዓለም_አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

አምባሳደር ሽፈራው ፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ ተቋማት የየብስም ሆነ የአየር ትራንስፖርት ክፍት ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ ፣ በሁመራ በኩል ሽራሮ ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ፤ በጎንደር አዲ አርቃይ ማይጸምሪ ሽሬ እንዲሁም የወልዲያ አላማጣ መስመሮች ሁሉም ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንደሆኑ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ መስመር የሙከራ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፤ በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ በኩል ከገቡ 16 ከባድ መኪናዎች መካከል 3ቱ የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው መግባታቸውን አመልክተዋል።

" ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየር እና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል " ብለዋል ኮሚሽነሩ።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አንዳንድ የተፈጠረውን ሰላማዊ ሁኔታ የማይቀበሉ አሉ "

የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ የተፈጠረውን ሰላማዊ ሁኔታ (ከህወሓት ጋር ማለታቸው ነው) የማይቀበሉ እንዳሉ በመጠቆም ፤ እነዚህ ሰላማዊ ሁኔታውን አይቀበሉም ያሏቸው አካላት " በዛም በዚህም " ያሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ትላንት ከናይሮቢ ሲመለሱ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ፤ " አንዳንድ የተፈጠረውን ይሄን ሰላማዊ ሁኔታ የማይቀበሉ አሉ። በዛም በዚህም አሉ፤ ይሄ ትግል ይፈልጋል፤ ሰላም አልፈልግም የሚል እና ሰላም የሚፈልግ ትግል ከገጠመ ሰላም የማይፈልግ ሰው አሸንፎ አያውቅም ብለን እናስባለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢታማዦር ሹሙ እነዚህ " በዛም በዚህም " አሉ ሲሉ የገለጿቸው ሰላም አይፈልጉም ያሏቸው አካላትን በግልፅ ከመናገር ተቆጥበዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በኢትዮጵያ መንግስት / በመከላከያ በኩል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ለመፈፀም " በመሉ ልብ ዝግጁ ነን " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ዝግጁ የሚያደርገን (ለስምምነቱ ተፈፃሚነት) ለኢትዮጵያ ህዝብ ብለን ነው። " ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ " የትግራይ ህዝብ ህዝባችን ነው። እዛ የደረሰውን ችግር፣ ውድመት አይተናል፣ ይበቃዋል፤ ከዚህ በላይ በእሱ ላይ መፍረድ ህሊናቢስነት ነው። ሀገራችንም ይበቃታል፤ ወደ ተጀመረው ልማት ፣ ብልፅግና ብትሸጋገር ይሻላል የሚል ሀሳብ ይዘን ነው በዚህ ድርድር የተደራደርነው የተፈራረምነው አፈፃፀሙንም የተግባባነው " ሲሉ ተናግረዋል።

የመጣው የሰላም ዕድል ጥሩ ዕድል መሆኑን የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ " የተቻለንን ያህል ተግባራዊ እንዲሆንና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና #ሁሉም ወደነበረበት ወደሰከነበት እንዲመለስ እንመኛለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ይዘጋሉ።

የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል መንገዶች የሚዘጉት ለ " ፀጥታ ስራ ሲባል " መሆኑን ገልጾ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኞች ዝግ እንደሚደረጉ ነው ያመለከተው።

የጋራ ግብረ ሃይሉ ከቀናት በኋላ በአ/አ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚከናወነው #የአጀብ እና #የፀጥታ ስራዎች ምክንያት በማድረግ #ሁሉም_የፀጥታ_አካላት_የሚሳተፉበት ወታደራዊ የተግባር ልምምድ እንደሚከናወን አሳውቋል።

ለዚሁ ሲባል የሚከተሉት መንገዶች ለተሽከርካሪ እና ለእግረኞች ዝግ ይደረጋሉ ፦

🚘 ከጎተራ መሳለጫ ወይም ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ጎተራ መሳለጫ ጋር፤

🚖 ከቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሀር የሚወስደው ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መስቀለኛ  ላይ ፤

🚘 ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ቡልጋሪያ ማዞሪያ፤

🚖 ከሳር ቤት በአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ሳር ቤት አደባባይ፤

🚘 ከካርል አደባባይ በልደታ ፀበል ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት  ለሚመጡ ካርል አደባባይ፤

🚖 ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ፤

🚘 ከአብነት ወደ ጌጃ ሰፈር አብነት አደባባይ፤

🚖 ከሞላ ማሩ ወደ አብነት ፖሊስ ጣቢያ ለሚመጡ ሞላማሩ መስቀለኛ ፤

🚘 ከበርበሬ በረንዳ ወደ ቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ  ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤

🚖 ከተ/ሃይማኖት ወደ ጎማ ቁጠባ ተ/ሃይማኖት አደባባይ፤

🚘 ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ዝግ የተደረገ ሲሆን ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡ 

🚖 ከሽሮ ሜዳ ወደ 6 ኪሎ እና ወደ 4ኪሎ የሚያስኬደው መንገድ  ሽሮ ሜዳ ጋር የሚዘጋ ሲሆን ከ4 ኪሎ ወደ ቤተ መንግስት የሚወስደው መንገድ ዝግ ተደርጓል፡፡ 

🚘 ከቀበና ወደ 4ኪሎ ቀበና አደባባይ ፤

🚖 ከጀርመን አደባባይ እና ከሲግናል አካባቢ ወደ 4 ኪሎ ጥይት ቤት ለሚመጡ ጀርመን አደባባይ ፤

🚘 ከካዛንቺስ መናህሪያ ወደ 4ኪሎ እና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሴቶች አደባባይ፤

🚖 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ፤

🚘 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደበባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል መስቀለኛ ፤

🚖 ከቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ ወደ መስቀል ፍላወር ቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ፤

🚘 ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ አፍንጮ በር፤

🚖 ከፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው 6 ኪሎ ዝግ ይሆናል፤

🚘 ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው መንገድ 6 ኪሎ ቶታል ጋር ዝግ የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም ወደ 4 ኪሎ እና በቅርበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመጡ አቋራጭ መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።

በተጨማሪም #ለእግረኛ ተጠቃሚዎች፦

🚶መስቀል አደባባይ 4ተኛ ክፍለ ጦር ወይም ጥላሁን አደባባይ ዙርያ፣
🚶‍♂ኦሎምፒያ ዙርያ፣
🚶‍♂ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ ከቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከሀራምቤ ወደ መሰቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከትምህርት ሚኒስቴር በአራት ኪሎ ብሔራዊ ቤተ መንግስትና ወደ ቦሌ እንዲሁም ከቀበና ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ዝግ መሆኑ ተነግሯል።

ዝግ ሆኖ የሚቆየው ከለሊቱ 11፡ 00 እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ህብረተሰቡ #አማራጭ_መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ተላልፏል።

(የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል)

@tikvahethiopia