TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ

ዛሬ በሀዋሳ በመንግስት ሀላፊዎች ላይ የተፈፀመው #ድብደባ!

ከደቂቃዎች በፊት አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከደቡብ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ከሆኑት ከዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ጋር በስልክ ቆይታ አድርጎ ነበር ስለጉዳዩ ይህ ብለዋል፦

"በመጀመርያ በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው። ጠዋት እኔ ስመራው የነበረው ስብሰባ ሌላ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ወጣቶች መጥተው ስብሰባው ይቁም ሲሉ confront ሳናረጋቸው አመራሮችን ወዲያው #በትነናል። የወላይታ ዞን ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋ ስምዖን ላይ ግን #ጥቃት ተፈፅሟል። ይህ ስብሰባ ይካሄድበት የነበረው አዳራሽ ውስጥ ከመጡት ወጣቶች ጋር #ግጭት ነበር። ዝርዝሩን አላውቅም። አሁን ሰላም ነው። አቶ ፀጋ ለህክምና ሶዶ ደርሷል። ከትንሽ ደቂቃ በፊትም አናግሬዋለሁ።"

ማነው ድብደባውን የፈፀመው ተብለው በጋዜጠኛው ለቀረበላቸው ጥያቄ፦

"እከሌ ኤጄቶ ነው እከሌ አይደለም ለማለት አልችልም። ግን ሶሻል ሚድያ ላይ ኤጄቶ ስብሰባው እንዲበተን ይፈልጋል የሚል መልእክት ጠዋት ስብሰባ ከመግባቴ በፊት አንብቤ ነበር።"

የሶሻል ሚድያ ምስል: አቶ ፀጋ ስምኦን

Via Elias Mesret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የደቡብ ክልል #ምክትል_ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶክተር #ጌታሁን_ጋረደው በወጣቶች #ታግተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና #ሀሰት ነው።

ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው: "...በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው።"

Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
'MINDSET'🔝

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ስርጸት ተግባራዊ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት እና በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ዙሪያ ተወዳዳሪ ብሎም ተመራጭ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ አስተሳሰብ ላይ የተመረኮዘ ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው ማህብሰብ መሰጠቱን ገለፀ፡፡

ስልጠናውን ከሀገረ ደቡብ ኮሪያ ተጋብዘው የመጡ አለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ደቡብ ኮሪያውያን ፕሮፌሰሮች መስጠታቸው ነው የተገለፀው፡፡

ስልጠናው #አስተሳሳብ ላይ የተመሰረተ ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት በሚቻልበት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ በስልጠናው የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳዳር እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

ደቡብ ኮሪያ እጅግ ደሀ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የምትገኝ የነበረች እና ዜጎቿም ዝቅተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው ነበሩ፣ ነገር ግን ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ዛሬ ላይ ለውጥ ማምጣት መቻላቸውን ስልጠናውን እየሰጡት ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ላይ ደቡብ ኮሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንደስትሪ ግንባታ በመጀመሪያው ተርታ ተሰልፋ ትገኛለች፤ይህ የሆነው ታዲያደቡብ ኮሪያውን ለቀጣዩ ትውልድ እንስራ፣ሳንበገር ተሃምር መፍጠር እንችላለን ብለው እጅ ለእጅ ተያይዘው በቁርጠኝነት በመስራታቸው የመጣ ለውጥ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከድህነት ተላቀን ለቀጣዩ ትውልድ #የተሸለች ሀገር ለማውረስ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት ለመሆን በጋራ እንረባረብ ሲል #መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ውጤትን የተመለከተ መግለጫ!

የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስትሩ ሚኒስቴር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ምክትል ዳይሬክተሮች ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ እና አቶ መሳይ ደምሴ፣ እንዲሁም የየክልሎች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ጋረደው የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ቶላ ባሪሶ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ይልቃል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተከታታይ #ውጤቱን በተመለከተ በጋራ በተላለፈው #ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁም መሰረት በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያጋጠመ ችግር መኖሩን በተለይ በደንብ ጥሰት ዙሪያ #በማረጋገጫ የተያዘባቸው ተማሪዎች ውጤት መሰረዙ እና በደንብ ጥሰቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በየደረጃው ተጠያቂ የሆኑበት ሁኔታን እንዳለ ሆኖ፤ ፈተናዎቹ ከሰጡባቸው ቀናት ሀሙስና አርብ ማለትም በ6 እና 7/10/2011ዓ.ም ከተሰጡት ፈተና ውጤቶች በተለየ ከቅዳሜና እሁድ በኋላ ሰኞ እና ማክሰኞ ማለትም በ10 እና 11 10/2011ዓ.ም በተሰጡት ፈተናዎች በግልጽ የታየ የውጤት ግሽበት መኖሩ በመረጋገጡ የዩንቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥቡ በአራቱ የትምህርት ዓይነቶች ላይ መሰረት ያደረገ እንደሚሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ እነዚህም እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ፊዚክስ ለተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆኑ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ጂኦግራፊ ለማህበራዊ ሳይንስ ይሆናሉ፡፡

ይህም ሲሆን ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ሊገነዘቡ የሚገባቸው ተማሪዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመምህርነት ሙያ ለመማር ከመረጡ ተማሪዎች ውጪ ለዩንቨርስቲ መግቢያ ብቻ የሚያገለግልና የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ተብለው ዩንቨርስቲ እንደሚገቡና ከአንድ ዓመት የፍሬሽማን ኮርሶች በኋላም በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት የፈለጉትን የትምህርት ፊልድ መርጠው መማር የሚችሉ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የተከሰተውን #ግሽበት በተመለከተም የማጣራት ሂደቱን የሚያካሂድ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሆነ ኮሚቴ መቋቋሙን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ያሳወቁ ሲሆን ተጠያቂው አካል አስተማሪና የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

በመግለጫው ማጠቃለያም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ እንደገለጹት የመቁረጫ ነጥቡን በተመለከተ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች የተፈተኑ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የሚታይላቸው መሆኑንና በጥቂት ቀናት ውስጥ በኤጀንሲው የሚገለጽ መሆኑን እንዲሁም በታየው የውጤት ግሽበት ምክንያት የተያዙት የተማሪዎች ውጤቶች #እንደሚለቀቅ ጨምረው አሳውቀዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia