TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጨፌ ኦሮሚያ ከሃምሌ 7 እስከ ሃምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡ በጉባኤው በክልሉ የ70 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነአቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ ላይ የቀሪ አንድ ምስክርን ቃል ዛሬ ረፋድ ሰምቷል፡፡ ዐቃቢ ሕግ በተከሳሾች ላይ የሰነድ ማስረጃ እና የሰው ምስክሮችን አቅርቦ ካሰማ በኋላ ፍርድ ቤቱ የቀረቡትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ብይን እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በእነአቶ በረከትና አቶ ታደሰ የክስ መዝገብ ሦስተኛው ተከሳሽ ከጤና ችግር ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ተሻለ የሕክምና ተቋም እንዲላኩ ጠይቀዋል፡፡ እንደ አብመድ ዘገባ ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ ያቀረቡትን የሕክምና ማስረጃ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በ2011 በጀት አመት 198 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡንና ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ22 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

📎በ2012 በጀት ዓመት ሚኒስቴር መ/ቤቱ #በፓርላማ እንዲሰበሰብ የፀደቀለት የገቢ ዕቅድ 224 ቢሊየን ብር ሲሆን ይህን ዕቅድ በመለጠጥ 248 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ ነድፎ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተደራጅታችሁ በሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ ብንባልም እስካሁን #መመሪያ ስላልተዘጋጀ ስራ ፈትተናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናገሩ፡፡ አስተዳደሩም መመሪያው #በቅርቡ ይወጣል ብሏል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሥራ እድል የተመቻቸላቸው እና አስፈላጊውን መስፈርት ያሟሉ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በዛሬው እለት የቀጠር መዲና ዶሃ ገብተዋል። ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳውዲ አረቢያ፣ ቀጠር እና ዮርዳኖስ ጋር የስራ ስምምነት የተፈራረመ ቢሆንም ስምምነቱ ተግባራዊ ሳይሆን ረዥም ጊዜ ቆይቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሀላፊ እና የዑለማ ሀላፊ ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ጉባኤ (Senate) ሐሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው ስብስባ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለሆኑት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሀላፊ እና የዑለማ ሀላፊ ለሆኑት ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ ቅዳሜ ሐምሌ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው በሚያካሂደው የምረቃ በዓል ላይ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጣቸው ወስኗል፡፡

የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ስነስርዓቱም ቅዳሜ ሐምሌ 6 ቀን 2011 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምረቃ ስነስርዓት በሚካሄድበት በሚሊኒየም አዳራሽ ይከናወናል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የቢሮ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አሁን ያለበት ህንፃ ለሌላ አላማ የተገነባ እና ለሚዲያ ስራ አመቺ ባለመሆኑ አዲስ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታ ለማካሄድ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

በተቋሙ ስር ያሉ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ችግር እና በሌሎች የሎጂስቲክ እጥረቶች ዙሪያም የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ስራ አስኪያጁ ለኢ/ር ታከለ ኡማ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኩል ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

ለኮርፖሬሽኑ አዲስ የሚዲያ ኮምፕሌክስ የግንባታ ቦታ የከተማ አስተዳደሩ አመቺ የሆነ ቦታ እንደሚሰጥም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ከሁለቱ አካላት የተውጣጡ 4 አባላትን የያዘ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ያዘጋጀውና ''ለኢንዱስትሪ ልማት እንሩጥ'' በሚል መሪ ቃል እሁድ ሀምሌ 7/2011 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው 3ኛው ዙር የአምስት ኪ.ሜ የኢትዮጵያ የቢዝነስ ሩጫ መራዘሙን ም/ቤቱ አስታወቀ። ም/ቤቱ ለኢፕድ በላከው መግለጫ በመስቀል አደባባይ ሩጫውን ለማካሄድ የዝግጅት #መደራረብና ፈቃድ ባለማግኘት ምክንያት ፕሮግራሙ ወደ ሀምሌ 14/2011 ዓ.ም መተላለፉን አስታውቋል።

አዝናኝ እና ለጤና አስተዋፅዖ ባለው ስፖርታዊ ሁነት መላው ማህበረሰብ በተለይም የግሉ ዘርፍ አባላት በኢንዱስትሪ ልማት ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ጎልብቶ በዘርፉ ያላቸው ሚና እና ተጠቃሚነት እንዲያድግ ለማበረታታት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ የሩጫ ፕሮግራም ለሶስተኛ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን በዚህም ም/ቤቱ ይቅርታ ጠይቋል። የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በፕሮግራሙ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ም/ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ኮማንድ ፖስት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፦

በአማራና ቤኔሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ ከሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይና በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር የሚደረግበት ኮማንድ ፖስት ተግባራዊ እንዲደረግ ተወሰነ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CP-07-12
ከኮማንድ ፖስት የተሰጠ መግለጫ👉https://telegra.ph/CP-07-12-2
#update ቦይንግ ኩባንያ በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ በደረሱት አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች 100 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መድቤያለሁ ቢልም ባለ ጉዳዮቹ ግን ስለ ካሳው የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡ ቦይንግ እነማንን ለካሳው እንደሚመርጥም አልታወቀም፡፡ ካሳይ ከፋዮቹ ከአየር መንገዶቹ ሳይሆን የአውሮፕላኑ አምራች መሆኑም ያልተለመደ ነው- ብሏል ሮይተርስ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ስለ ካሳው ምንም መረጃ የለንም ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያና ኬንያ መንግሥታትም ከቦይንግ ጋር ስለ ጉዳዩ አልተነጋገሩም፡፡ አውሮፕላኑ የተከሰከሰባቸው ሰፊ ማሳዎች ባለቤት አርሶ አደሮችም ማሳዎቻቸው እስካሁን ታጥረው ያሉ ሲሆን ካሳ ስለመፈቀዱ በይፋ የሰሙት ነገር የለም፡፡

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ያወጣው መመሪያ የህግ ክፍተት እንዳለበት የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አስታወቀ።

ተጭማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CONDO-07-12
#TPLF/ህወሓት እና #ADP/አዴፓ

"አሁን የአዴፓ ድርጀት የራሱን ትላልቅ ጓዶች የገደለ ሃይል ማውገዝ አቅቶት በአርበኝነት ተረት ለመፍጠር ሲሞክር ስታይ ወይ ተምታትቶበታል ወይም ድርጅቱ የሆነ ነገር ይበል፡፡የራስህ ጓዶች የገደለን ሰው አርበኛ ነው ጀግና ነው ማለት የጀመረ ድረጅት በግሌ አጠገቡ መቀመጥ ይከብደኛል፡፡እና የሄንን በደንብ አጥርቶ ይምጣ ነው ያልነው፡፡አሰላለፍ ማለት እሱ ነው፡፡ስለአሰላለፍ ስታወራ እገሌ ጀግና ነው እገሌ አንዲህ ነበረ ኣይደለም የምትለው፡፡ #አምባቸው_መኮነን ህዝብ የመረጠው የአማራ ክልል መሪ ነው፣ምግባሩ ከበደ በህዝብ የተመረጠ የአማራ ክልል መሪ ነው፣ሌሎቸም እነዚህ ሰዎች በጠራራ ፀሃይ የገደለ ሰው አርበኛ ነው፣አንበሳ ነበረ ማለት ትክክል ኣይደለም ፡፡ አሁን በዚህ ግርግር ውስጥ በኣደባባይ ሰውን የገደለ ላለማውገዝ ተረት የሚፈጥር አመራር ፣እኔ እንደ ጓድ ፣ የሞቱት ጓዶቼ ናቸው የሄን ዓይነት አቋም የሚያሳይ ድርጅትጋር አብረን ለመጓዝ እርግጠኞች መሆን አንቸልም የሚል የአቋም መግለጫ መስጠት ጤነኝነት ነው፡፡ለድርጅቱም ማዘን ንው፡፡" አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢሳት ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

ምንጭ፦ TPLF ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ነገ ሐምሌ 06/2011 በባሕር ዳር ስብሰባውን እንደሚጀምር ታውቋል። #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ሰኔ 15 በነበረው የፀጥታ ችግር ከታሰሩ 218 ተጠርጣሪዎች መካከል 113ቱ መፈታታቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ እስከሚካሂድ ድረስ ከተማዋን ማስተደደሬን እቀጥላለሁ ብሏል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-07-12-4
ኢትዮ ቴሌኮም የአዲስ በጀት ዓመትን መጀመር አስመልክቶ ደንበኞችን ለማመስገን ለሦስት ቀናት የሚቆይ የኢንተርኔት ፣ የአጭር የጽሁፍ መልእክት እና የድምጽ አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል ድርጅቱ #ወደፊትም ይህን አሰራር ተግባራዊ ማድረጌን እቀጥላለሁ ብሏል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

"ይህች ሃገር የቆመችው #በጠመንጃ ብዛት ሳይሆን በህዝቦቿ ፀሎት ነው፤ በእስልምና እና በክርስትና ሃይማኖት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በየ ቤተ-እምነታችሁ ለሃገራችሁ ፀሎት አድርጉ፤ ልጆቻችሁንም ስለ ሃገር ፍቅር ስለ አንድነት አስተምሩ!" ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ

ሰላማችን ህልውናችን ነው!!
ሰላም እደሩ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀገራችን የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት #እያስመረቁ ይገኛሉ።

🎓TIKVAH-ETH ለመላው ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡

🗞ቀን ሃምሌ 6/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 9637 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በ10 ኮሌጆችና 12 ትምህርት ቤቶቹ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 9637 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 2763 ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው 5876 ተማዎችን በመደበኛ ፕሮግራም፣ የቀሩትን 3761 ተማሪዎችን ደግሞ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 230ዎቹ በሶስተኛ ድግሪ የተመረቁ ናቸው።

ከእነዚህም 2085 ተማሪዎችን በማታ ፕሮግራም፣ 319 ተማሪዎችን በርቀት እንዲሁም 1995 ተማሪዎችን ደግሞ በክረምት ፕሮግራም ነው አሰልጥኖ ዛሬ ያስመረቀው።

በተጨማሪም ለአገሪቷ ሰፊ ግልጋሎት በመስጠት ለሚታወቁት ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እንዲሪስ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም የክብር ዶክተሬት ማዕረግ ሰጥቷል።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን አጠቃላይ ከ32 ዩኒቨርሲቲዎች 120 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመረቁም ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ተመራቂ ተማሪዎች ለሀገር በመስራት ብድሯን መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 9 ሺህ 637 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ወላጆች ማየት የሚፈልጉት የተመራቂ ተማሪዎችን ስኬት ነው ያሉ ሲሆን፥ ተመራቂ ተማሪዎችም ወላጆቸውን ማስታወስ ይገባቸዋል ብለዋል።

እንዲሁም ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ያሉ መምህራኖቻቸውን ሊያስታውሱ እንደሚገባ እና እነሱን ሊያስደስቱ የሚችሉ ተግባራትን እንዲፈፅሙ አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመራቂ ተማሪዎች በማንኛውም ጉዳች ሊደራደሩ ይገባል ያሉት ሲሆን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ግን ድርድር አያስፈልግም ብለዋል።

ለተመራቂ ተማሪዎች መልካም ምኞታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ዩኒቨርስቲዎች የምርምር፣ የተለያዩ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባቸው እና ጥልቅ ትንተና የሚካሄድባቸው ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

ተመራቂዎችም የአገልግሎት መርሆችን፣ መስጠት፣ ፍቅር እና በህይወት ዘመን ለመማር ዝግጁ መሆንን ሊከተሉ ይገባል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 9 ሺህ 637 ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም እና ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia