TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Congratulations የጅማ ዩንቨርስቲ በአዲስ አበባ ኤ ቢ ኤች ካምፓስ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ዛሬ ሀምሌ 27 አስመርቋል። ውድ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!

Via ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
#Congratulations የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 790 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስምንት የጤና ትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪና በደረጃ አራትና አምስት ያሰለጠናቸውን 846 ተማሪዎች ትናንት አስመርቋል። ኮሌጁ በ30 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው ባለ 3 ፎቅ ሁለገብ ዘመናዊ የመማሪያ ህንጻም ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations #ASTU የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ወደበኃላ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርቃት ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን አቀርባለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተከናወነ ስነ ስርዓት የተመረቁት 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ እና ስምንት የሁለተኛ ድግሪያቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥም 21 ተመራቂዎች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል። እነዚህ ተመራቂዎችም ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ መሆናቸው ነው የተመለከተው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድም ለተመራቂዎች ዲፕሎማ ከሰጡ በኋላ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ተመራቂዎች በስነ ምግባር፣ በወታደራዊ ጥበብ፣ በሙያዊ ብቃት እና በላቀ ዝግጅት የሰራዊት አባላትን ለመምራት እና ለድል ለማብቃት የሚያስችላቸውን እውቀት እና ከህሎት ለማግኘት ለአንድ ዓመት ትምህርታቸውን መከታተላቸውን አንስተዋል።

በመሆኑም በትምህርት የገበዩትን እውቀት ከዚህ በፊት ካገኙት ልምድ፣ በንባብ ከሚያገኙት እና በተፈጥሮ ከያዙት እውቀት ጋር በማዋሃድ በትጋት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ነው ያሳሰቡት።

ወታደራዊ ተቋማት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ መሪዎች፣ በስነ ምግባር አርኣያዎች፣ ሀገርን እና ወገንን በመጠበቅ አኩሪዎች፣ ህግና ስርዓትን በማክበር እና በማስከበር ተምሳሌት እንዲሆኑም ያስፈልጋል ብለዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

ASTU 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ!

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ/ASTU/ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 353 ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም በዩኒቨርስቲ የሚታዩ #በዘርኝነት የሚከሰቱ #መጠፋፋቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ በመሆናቸው ይህ ትውልድ መፍቀድ የለበትም ብለዋል፡፡ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም በበኩላቸው ተማሪዎች በተማሩበት መስክ ጠንካራ ሰራተኛ በመሆን የአገልጋይነት ስሜት በመላበስ የተጣለባቸውን አደራ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ከ25 አመታ በፊት የተቋቋመው ዩኒቨርስቲው በልዩ የመግቢያ ፈተና በዓመት 5ሺህ የሚሆኑ ለፈተና ቢቀርቡም 1500 ብቻ ናቸው ዕድሉን የሚያገኙት ተብሏል፡፡ ዩኒቨርስቲው የምርምር እና የጥናት የልህቀት ስራዎችን የሚያካሂድበት 8 የልህቀት ማዕክል አሉት፡፡

በዩኒቨስቲው የሚገኘው ላብቶሪ ለዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር አገልግሎቱን እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡ ሙህራን በዘርፉ ላይ ምርምር እና ጥናት ሊያካሂዱበት የሚችል በአይነቱ ለየት ያለ የምርምር ማዕከል በዩኒቨርስቲው ውስጥ እየተገነባ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations #Somaliland Military Officers graduate from #Ethiopian Military Academy, Won medals!

Via Horn
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል። ለመላው ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!

ፎቶ📸AMANI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ባለሙያዎችን በስካይ ላይት ሆቴል እያስመረቀ ነው፡፡ ኮሌጁ በቅድመ- እና ድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን የሕክምና ባለሙያዎችን ነው በማስመረቅ ላይ ያለው፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴና የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱም የክብር ዶክትሬቶች ይሰጣሉም ተብሏል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia