TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦነግ⬇️

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ ድርጅታቸው #ትጥቁን ለመፍትት ከመንግስት ጋር አለመስማማቱን ተናገሩ። አቶ ዳውድ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ትጥቅ ፈተኖ ነው የሚለውን መረጃ አስተባብለዋል።

አቶ ዳውድ ለዋልታ ሲናገሩ "እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት ስምምነት የለም። #የታጠቀው አካል ትጥቅ #ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ #የምንፈታበት ምክንያት የለም።" ብለዋል። አክለውም "ትጥቅ መፍታት የሚባል sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።" ሲሉ ለዋልታ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። አቶ ዳውድ ሰኔ 16 በጠቅላ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው #የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። በቡራዩና በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ገልፀዋል።

አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል #እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን አንስተዋል።

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲዳማ🕊ወላይታ‼️

በሲዳማና ወላይታ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ዕርቀ ሠላም ለማውረድ #በገለልተኛ ሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ካለፈው ሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የዕርቅ ውይይት በሁለቱ ሕዝቦች ተወካይ ሽማግሌዎች መካከል ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።

በተደረገውም ውይይት የሚያቀራርብና እጅግ #ጠቃሚ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት የተደረሰ ሲሆን ይህንን በሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማጠቃለል ከሁለቱም ወንድም ሕዝቦች የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ኀዳር 9/2011 ዓ.ም በሀዋሳ #ሲዳማ_ባህል_አዳራሽ የዕርቅ ኮንፈረንስ የሚደረግ ሲሆን ኀዳር 11 /2011 ዓ.ም ተመሳሳይ መድረክ #በወላይታ_ሶዶ ተካህዶ የዕርቅ ኮንፈረንስ እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ዕርቁ በሁለቱም #ወንድም ሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን መሻከር በማስወገድ መተማመንና ዘላቂ ሰላምን ለማውረድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል።

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝም፤የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲዳማ🕊ወላይታ!

🔹ኀዳር 9/2011 - ሀዋሳ(ሲዳማ ባህል አዳራሽ)
🔹ኀዳር 11/2011 - ወላይታ ሶዶ

#Update የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት መረጃውን/ዳታ/ የማስገባት ሥራ #በገለልተኛ አካል እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽሕፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ ሂደት መሪ አቶ ጋሻው ተፈራ፣ ቀደም ሲል ዕጣ የማውጣቱ ሥራ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ)ይሠራ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን የግንባታው ባለቤት የሆነው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ሥራውን ተረክቦ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 32 ነው ሲል አሳውቋል።

ጥቃት የተፈጸመበት ቀበሌ ከወረዳ ከተማ በ75 ኪሎ ሜትር የሚርቅ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደተናገረው በጥቃቱ 32 ሰዎች (23 ወንድ እና 9 ሴት) ሲገደሉ ፤ 10 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።

ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ 200 ሰዎች ተፈናቅለዋል ያለ ሲሆን እነሱን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ሲል ገልጿል።

በጥቃቱ መኖሪያ ቤቶች እና አንድ ትምህርት ቤት ተቃጥሏል።

ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ፥ "ጥቃቱን የፈጸመው አካል ኦነግ ሸኔ ነው፤ ከጀርባ በመሆን ህወሃት እየደገፈው ይገኛል" ብለዋል።

በሌላ በኩል ኢሰመኮ ስለጉሊሶ ወረዳው ጥቃት ፦

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የፌዴራል ሰራዊት ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የታጠቁና ያልታጠቁ በቁጥር 60 የሚሆኑ ቡድኖች 32 የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎችን ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ግድያ መፈፀማቸውን ገልጿል።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ነው ብለዋል፡፡

ዜጎቹ ከቤታቸው ወደ ትምህርት ቤት ተወስደው ግድያ እንደተፈጸመባቸው ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

የጥቃቱ አድራሾች ለፍርድ እንዲቀርቡም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት አመራሮች ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሰራዊት እንደሆኑ መናገራቸው የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ሴቶችና ሕፃናት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡

የፌዴራል መንግስትና የክልል ባለስልጣናት ግድያው #በገለልተኛ_ቡድን እንዲጣራ እንዲያደርጉ እና የሰላማዊ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ አስፋላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia