TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የነዋሪዎች መታወቂያ መታደል ጀመረ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጊዜው #አቋርጦት የነበረውን ነባሩን የነዋሪዎች መታወቂያ እንደገና ማደል መጀመሩን ካፒታል አስነብቧል፡፡ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ኮምፒውተር ላይ የጣት አሻራን በመስጠት ሊያትመው ባሰበው አዲስ የነዋሪዎች መታወቂያ ላይ #በብሄር ማንነት ፋንታ #የደም_ዐይነትን ለማስፈር አቅዶ ነበር፡፡ ሆኖም ባጋጠመው የሶፍትዌር ቴክኖሎጅ ችግር እና በባለድርሻ አካላት ቅንጅት ማነስ ሳቢያ ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም፡፡ እናም ቀደም ሲል በ5 ብር ይሰጥ የነበረውን ነባሩን የቀበሌ መታወቂያ እንደገና ለነዋሪዎች በ10 ብር ክፍያ መስጠት ጀምሯል፡፡ ለመታወቂያ ዕድሳት ከ10-20 ብር፣ የጠፋውን ለመተካት ደሞ ከ10-30 ብር ይከፈላል፡፡ በቅርቡ ግን ሁሉንም ነገር አስተካክየ አዲሱን መታወቂያ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሏል- ኤጀንሲው፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia