TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ይሄ ካስተማረን...

የመን ውስጥ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 85 ሺ #ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ሴቭዘቺልድረን የተባለው ምግባረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት 14 ሚሊዮን የመናውያን ከባድ ረሃብ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ገልጾ ነበር።

ለዚህ ሀሉ መነሾው ደግሞ ሶስተኛ ዓመቱን የያዘው #የእርስ_በርስ_ጦርነት ሲሆን፤ ያስከተለው ጉዳትም በዓለማችን ካጋጠሙ ሰብዓዊ ቀውሶች ትልቁ አስብሎታል።

እስካሁን 6800 ንጹሃን ዜጎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ የምግብ እጥረት ደግሞ አብዛኛውን የሃገሬውን ሰው እየፈተነ ያለ ጉዳይ ነው።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከእነዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ፈተናዎች ያለፉት ደግሞ በኮሌራ ወረርሽኝ እየተጠቁ እንደሆነና በበሽታው ምክንያት1.2 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል።

85 ሺዎቹ ህጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን ለማረጋገጥና መረጃ ለማሰባሰብ እጅግ ፈታኝ እንደነበረ የረድኤት ድርጅቱ ገልጿል።

ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሃገሪቱ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በጦርነቱ መውደማቸው ነው።

ከጦርነቱ የተረፉት የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት ማግኘት እጅግ ውድ ስለሚሆን አብዛኛዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ሲያልፍ እንኳን በተገቢው ሁኔታ አልተመዘገቡም።

85 ሺዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ያለፈው እ.አ.አ. ከሚያዚያ 2015 እስከ ጥቅምት 2018 ድረስ እንደሆነ ተጠቁሟል።

#አልቆም ያለው ጦርነት የሃገሪቱን የገንዘብ አቅም እጅግ ያዳከመው ሲሆን፤ የምግብና አስፈላጊ እቃዎች ዋጋ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ ነው።

የመን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን ምግብ ከውጪ የምታስገባበት ወደብ በአማጺያን ቁጥጥር ሲሆን፤ በሃገሪቱ ያለው የምግብ ክምችት 4.4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ብቻ የሚበቃ እንደሆነ ሴቭዘቺልድረን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia