TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፓሬሽን(ሜቴክ) የስራ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ቁጥር ዛሬም ጨምሯል። በተጠርጣሪዎች ላይ ያለው መረጃም ገና #ተጠናክሮ አላለቀም። ከዚህ በኃላም በቁጥጥር ስር የሚውሉ እንዳሉ እና #የሚለቀቁም ሊኖሩ እንደሚችሉ ሸገር 102.1 ዘግቧል። ይህንን መረጃ በተመለከተ ነገ አልያም ከነገ በስቲያ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን💥💫የTIKVAH-ETH የሞባይል መተግበሪያ(application) ነገ ምሽት 2:00 እናተ ጋር ይደርሳል!!

.የተመረጡ ሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜናዎች
.ስፖርት
.ቢዝነስ
.መዝናኛ

Apk. 4.1 mb (ነገ ምሽት እናሰራጨዋለን) ለአድሮይድ!

ለአይፎን(ios) ተጠቃሚዎች በሚቀጥለው ወር ይቀርባል።

መተግበሪያው፦ የቻናላችንን ተደራሽነት ለመጨመር በማሰብ የተዘጋጀ ነው። የቴሌግራም ቻናላችን #ተጠናክሮ ይቀጥላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ሱዳን ውስጥ በፕሬዝደንቱ ላይ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም #ተጠናክሮ ዋና ከተማዋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል። የሀገሪቱ ፖሊስም በኻርቱም እና ኦምዱርማን ከተሞች ከዕለተ ዓርቡ የጸሎት ሥርዓት በኋላ ወደ ጎዳና በወጡት ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ «ነፃነት፣ ሰላም፣ ፍትሕ» የሚሉ መፈክሮችን ያሰሙ እንደነበርም አመልክቷል። የሱዳን ባለሙያዎች ማሕበር ለፊታችን እሁድም ታላቅ ሰልፍ በኻርቱም ከተማ ለማካሄድ የጠራ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞች በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እና መንደሮች እንደሚቀጥልም አስታውቋል። ሱዳን ውስጥ ተቃውሞው የተቀሰቀሰው ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ሲሆን፤ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽር እና ሌሎች ባለስልጣናት ለኤኮኖሚው ድቀት ዩናይትድ ስቴትስን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

በሌላ በኩል...

ሱዳንን ባናወጠው የፀረ-መንግስት ተቃውሞ 22 ሰዎች መሞታቸውን አፍሪካ ኒው ስ ዘግቧል፡፡ 22 ግለሰቦች መገደላቸውን ኃላፊዎች ሲገልፁ መሰረቱን በኒውዮርክ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ታዛቢ ቡድን ህፃናትን አጠቃሎ 40 የሚጠጉ ህይወታቸው ማለፉን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ DW እና አፍሪካኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ250,000 ብር በላይ ድጋፍ ተደርገ🔝

በባህርዳርና በደብረ ታቦር የሚኖሩ የአስቴ ወረዳ ነዋሪዎች በቅርቡ የተቃጠሉትን ሁለት መስጅዶች ለመስራት የሚያስችል ሩብ ሚሊዮን ብርና #የሲሚንቶ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ተወላጆቹ በራሳቸው ተነሳችነት ብሩን ከመሰብሰብ ባለፈ ቦታው ደረስ በመሄድ የጎዳቱን ሁኔታ በመመልከት የአለኝታነት ድጋፋቸውን እንዳሳዩ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
በዛሬው ዕለት ገልጸዋል፡፡

ተወላጆቹ ለመስጅዶች ግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ ካስረከቡት 250 ሺህ ብር በተጨማሪም ለግንባታው የሚውል 100 ኩንታል ሲሚንቶ አበርክተዋል፡፡

ተወላጆቹ ድርጊቱን አውግዘው ምንም ዓይነት እኩይ ዓላማ ያለው አካል ትንኮሳ #ቢፈፅም የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንድነት የበለጠ ይጠናከራል እንጂ ምንም ዓይነት የሚፈጠር ነገር የለም ብለዋል፡፡

ድጋፉን ያሰባሰቡት የሁለቱም እምነት ተከታይ የወረዳዋ ተወላጆች አጥፊዎቹ ታድነው ተገቢው ቅጣት እንዲሰጣቸውም በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ጠይቀዋል፡፡

አጥፊዎችን ለመለየት ከተያዙት 6 #ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ምርመራው #ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡ የተቃጠሉት መስጅዶች ግንባታ በፍጥነት እንደሚጀመር ተመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ላይ የተቃጠለውን የጃራ ገዶ መስጅድ የአካባቢው ማህበረሰብ 27 ሺህ ብር በማዋጣት መልሶ የመስራት ሂደቱን እንደጀመረ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ለኢቢሲ አመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት‼️

በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት #ተጠናክሮ መቀጠሉን የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር #ሂሩት_ወልደማርያም ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ሠላማዊው የመማር ማስተማር ሂደቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከዚህ ቀደም ችግሮች ይስተዋሉባቸው የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉባቸውን ችግሮች አመራሮቻቸው የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ለመፍታት ተሞክሯል ብለዋል።

ተማሪዎችም የእረፍት ጊዜ እንዲወስዱ በማድረግም ችግሮቹን ለማርገብ መሰራቱን ገልጸው፤ ሠላሙን ዘላቂ ለማድረግም የተማሪዎች አመለካከት ላይ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹን ሊያነቃቁ የሚችሉ ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ ውይይቶችም በተለይም ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጎን ለጎንም በአመለካከተ ላይ አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ድራማና ሌሎች የጥበብ ሥራዎችም በስፋት እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎች ከኅብረተሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ለማድረግም የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑም መደረጉን ሚኒስትሯ አስረድተዋል።

ይህም ደግሞ ተማሪዎች ዓላማቸውን በደንብ አጥብቀው እንዲይዙ በማድረግ በየትኛውም ኃይል ተጠልፈው እንዳይወድቁ ለማድረግ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 45 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምቦ ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ!

በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የአምቦ ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ400 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ሀያት ረጀንሲ ሆቴል በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #ለማ_መገርሳና ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ ወቅቱ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለህዝብ የሚሰራበት መሆኑን በመጥቀስ፥ ይህ ጅምር ፕሮግራም በሌሎች አካባቢዎችም #ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

በዕለቱ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢየ ፕሮግራም ከ400 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የአምቦ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ዶክተር #መንግስቱ_ቱሉ ለfbc ተናግረዋል።

በዚህ መሰረትም ፦

1. አቶ በላይነህ ክንዴ 15 ሚሊየን ብር
2. አቶ ገምሹ በየነ 5 ሚሊየን ብር
3. አቶ ተክለብርሀን አምባዬ 1 ሚሊየን ብር
4. ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ 100 ሺህ ብር
5. ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ 100 ሺህ ብር እና ሌሎች ባለሃብቶችም ለልማቱ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ለልማቱ ገቢ ማሰባሰቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእጅ ስዓታቸውን ለጨረታ ያቀረቡ ሲሆን ፥ ጨረታውንም አቶ ገምሹ በየነ በ 5 ሚሊየን ብር ማሸነፍ ችለዋል።

በአጠቃላይ በዕለቱ በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ 400 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ነው የተገለፀው።

በገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ በተገኘው ገንዘብም በአምቦ ከተማ 12ሺህ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣20 ሺህ ሰው የሚይዝ ደረጃውን የጠበቀ ስቴዲየም፣ለሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የአርት ጋለሪ ግንባታና ለሌሎች ፕሮጀክቶች ስራ ማስፈፀሚያ የሚውል ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተደረገ በሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ የተሰሙ መፈክሮች፦

√ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ያለን #አብሮነታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!

√የክልልነት ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስ!

√የወላይታ ህዝብ በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ አንድነትን #ይደግፋል!

√ሀገራዊ ለውጡ #ተጠናክሮ እንዲቀጥል የህግ የበላይነት ሊከበር ይገባል!!

√መንግስት በወላይታ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት #ሊያስቆም ይገባል።

√የደቡብ ክልል ምክር ቤት የህዝባችንን የክልል ጥያቄ አዳፍኖ መያዙን አጥብቀን #እንቃወማለን!

√በ1950ቹ የነበረው የወላይታ አውሮፕላን ማረፊያ #ይመልስልን!

√አሁን ያለው ሀገራዊ ለውጥ በምንም አይነት ሁኔታ #ሊደናቀፍ አይገባም!!

√እኛ የለውጥ #ደጋፊዎች ብቻ ሳንሆን የለውጥ #ባለቤቶች ነን!!

√ሀገር ለነበረው ወላይታ #ክልል መሆን አይከለከልም!!

√ስራ ወዳድነት #ክብር እንጂ ውርደት አይደለም!

√ወላይታ በሞግዚቶች መመራት በቃው! ጋሞ፣ ጎፋ፣ ሲዳማ፣ ዳውሮ የወላይታ ወንድም ሕዝቦች ናቸው!

√ኢትዮጵያዊነት ፀጋ እንጂ ኩነኔ ሊሆን አይገባም!

√የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለወላይታ!


በአሁን ሰዓት በወላይታ ሶዶ ስታዲየም ብዙ ሺ ሰዎች በተገኙበት የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ እንደሆነ ለመስማት ችለናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ ደቡባዊ ዞን አንበጣ መንጋን ከመከላከሉ በተጓዳኝ የደረሰ "ሰብልን የመሰብሰቡ" ስራ #ተጠናክሮ ቀጥሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ከደቂቃዎች በፊት የሰጡን አጭር መረጃ ፦

- ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 4 ሰዎች የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

- የረዳቶቹ ዕድሜ 28፣ 25 እና 24 ነው ፤ ሹፌሩ ደግሞ 33 ዓመቱ ነው።

- ታማሚዎቹ ምንም ምልክት የላቸውም።

- ወደ ክልሉ የሚገቡ ሰዎች ላይ ጠንካራ ምርመራ እየተደረገ በመሆኑ ነው ግለሰቦቹ የተገኙት።

- እኚህ አራት (4) ሰዎች ወደ ትግራይ የገቡት ወደ ሚያዚያ 23 አካባቢ ነው።

- በአሁን ሰዓት የጤናቸው ሁኔታ ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ነው።

- ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ወደለይቶ ማቆያ የማስገባቱ ስራ #ተጠናክሮ ቀጥሏል።

- ዛሬ በክልሉ ጤና ቢሮ #ዘግየት ብሎ ሪፖርት የተደረገው ኬዝ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ መግለጫ ከሰጡ በኃላ የተረጋገጠ በመሆኑ ነው (ወደ 7:00 አካባቢ ነው ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠው) ፤ ከ8:00 በኃላ በይፋ መግለጫ ተሰጥቷል።

#TIKVAHETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia