TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የህወሓት (TPLF) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የተሳተፉበት ውይይት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ከሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል ባለስልጣናት ጋር መደረጉ ይታወሳል።

በወቅቱም ከ ' ህወሓት ' ህጋዊ እውቅና  ማግኘት ጋር በተገናኘ ውይይት ተደርጎ ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከውይይቱ በኃላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫቸው ፤ ' ህወሓት / TPLF ' መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው ገልጸው ነበር።

በዚህም ያለው #የህግ_ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም መመራቱን ሲናገሩ ተደምጠው ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ሲል የ ' ህወሓት ' ን ህጋዊ ሰውነት #መሰረዙ ይታወቃል።

ፓርቲውም " ስረዛው ይነሣልኝ " ሲል ጥያቄ ቢያቀርም ቦርዱ ያን ሊያደርግ የሚችልበት ምንም ህጋዊ መንገድ እንደሌለ አሳውቆ ነበር።

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ " ምናልባትም ህወሓት ዳግም እውቅና ሊያስገኝለት የሚያስችለው እንደሆነ እየተነገረ ነው።

@tikvahethiopia