TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦሮሚያ ፖሊስ⬇️

በሻሸመኔ ከተማ ዛሬ በተጠራ የድጋፍ ስልፍ በተከሰተ ግርግር እና መጨናነቅ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ በግርግሩ በሰው አካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንም ገልጿል።

ኮሚሽኑ በህዝቡ አስተባባሪነት ለድጋፍ ሰልፍ በውጡ ዜጎች ላይ በተከሰተ አለመረጋጋት በተፈጠረው መገፋፋትና መጨናነቅ የሰው ህይወት ማለፉንና ንብረትነቱ የሻሸመኔ አስተዳደርና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት የሆነ አንድ መኪና መቃጠሉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አለማየሁ እጅጉ ለኢቲቪ ዜና ተናግረዋል።

በተለያዩ ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችና ድረ ገጾች እየተዘዋወሩ ያሉት መረጃዎች እውነተኛነታቸው ሳይረጋገጥ ወደ #ተሳሳተ ድምዳሜ ስለሚያደርሱ ጥንቃቄ ያስፈልጋልም ብለዋል።

እስከ አሁን ፖሊስ የግርግሩ መነሻ ምክንያት ለማጣራት በምርመራ ላይ መሆኑን ገልጸው በድጋፍ ሰልፉ ከሻሸመኔና ዙሪያዋ ከፍተኛ ቁጥር
ያለው ህዝብ መገኘቱን ገልጸዋል።

ኮሚሽነር ጄኔራል አለማየሁ እጅጉ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ሻሸመኔ ከተማ እና በዙሪያዋ የነበረው ግርግር ተረጋግቶ መደበኛ እንቀቃሴዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ፖሊስም በቀጣይ ቀናት ምርመራውን በማጠናቀቅ #ተጠርጣሪዎችን ለሕግ ለማቅረብ ይሰራል ብለዋል።

ሕብረተሰቡም በመረጋጋት #ትክክለኛ_መረጃዎችን ከፖሊስ እና የጸጥታ ሀይሉ ማግኘት እንደሚገባው አሳስበዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል ክልል⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኦዳ ዳለቲ እና በጉባ አልመሃል ላይ በተፈጠሩ ግጭቶች 69 ተጠርጣሪዎችን #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት #የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከፌደራልና ከአጎራባች ክልሎች ጋር እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የከልሉ መንግስት የህግ የበላይነት ለማስከበር #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ነሐሴ 26 እና 27 2010 ዓ'ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኦዳ ቢልዲጊሉ ወረዳ ዳለቲ ቀበሌ ላይ በተፈጠረው ግጭት 48 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ የማጣራት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ግጭቱ በቤኒሻንጉልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ላይ የተከሰተ በመሆኑ የማረጋጋት ስራዉንም ሆነ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር
የማዋል ሂደቱ በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ ነዉ አቶ ማሃመድ የተናገሩት፡፡

በተመሳሳይም መስከረም 3 2011 ዓ.ም በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሃል ቀበሌ ላይ በደረሰዉ ጥቃት 21 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተካሄደባቸዉ ይገኛል፡፡

ሰኔ 17 እስከ 21 በአሶሳ ከተማ፣ በሽርቆሌ ወረዳ እና በማኦኮሞ ልዩ ወረዳ ላይ ተከስቶ በነበረዉ ግጭት በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑንም አቶ መሃመድ ገልፀዋል፡፡

#በአሶሳ ከተማ እና በሸርቆሌ ወረዳ ላይ ተከስቶ በነበረዉ ግጭት ከ 1 መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የኦፕሬሽ ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ጥረት እያደረገ ነዉ ያሉት ሃላፊዉ ከፌደራል መንግስት የተላከ ቡድን እንዳለም ተናግረዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በፍርድ ቤት ታሪክ የመጀመሪያው⁉️

የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም የተጠረጠሩ 36 ግለሰቦች ትናትና #ምሽት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

36ቱ ተጠርጣሪዎች የብሔራዊ መረጃና ደንህነት፤ የፌዴራል ፖለሲ ምርመራ ቢሮ፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች በስራ ሃላፊነትና በሰራተኛነት ሲያገለግል የነበሩ ናቸው።

ትላንት ከ11 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት 30 በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ታሪክ #ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛው የወንጀል ችሎት ፖሊስ #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለበትን ምክንያት አድምጧል።

በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ከቀረቡት ተጠርጣሪዎች መካከል 16 ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት፣ ስድስቱ ከፌዴራል ፓሊስ ምርመራ ቢሮ፣ ሁለቱ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን፣ ስምንቱ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሲሆኑ፥ ሶስቱ ግለሰቦች ደግሞ ተጠርጣሪን በማስመለጥና #ሰነድ በማጥፋት የተጠረጠሩ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ ያልተሰጣቸው ስልጣን በመጠቀም ሰዎችን የኦነግ፤ የአርበኞች ግንቦት ሰባት እና የተለያዩ የሽብር ቡድኖች አባል ናቹ በማለት ፊታቸውን በጥቁር ጨርቅ በመሸፈን በአንቡላንስ ጭነው በማይታወቅ ቦታ እስከ 1 ዓመት በማሰር የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በማረሚያ ቤት እየታረሙ የሚገኙና ተጠርጥረው ጉዳያቸው የሚከታተሉ ሰዎችን ወደ ሸዋሮቢት እንዲሄዱ በማድረግ በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ድብደባ እንዲፈፀም አድርገዋል ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

እንዲሁም ተጠርጣሪዎቹ ሴቶችን መድፈር፣ጥፍር መንቀል እና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ እንደነበረ ፓሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በተለይም ባልታወቀ ቦታ የሚያስሯቸውን ሰዎች ከአይን ማጥፋት ጀምሮ የተለያዩ የአካል ጉዳት እንዳደሩ ፓሊስ ከተጠቂዎቹ በተቀበለው የምስክርነት ቃል ማረጋገጡን አብራርቷል።

በዚህም የበርካታ ዜጎች የአካልና የስነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው ፓሊስ ለፍርድ ቤት ያስታወቀው።

ምርመራውን ለአምስት ወራት ሲያከናውን ቢቆይም ተጠርጣሪዎቹ በስራ ላይ የነበሩ በመሆኑ በዚህ መንገድ ጥቃት የደረሰባቸው ዜጎች የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ፍርሃት እንደነበረባቸው ፖሊስ ጠቁሟል።

ፓሊስ ተፈፅሟል የተባለውን ወንጀል ውስብስብ በመሆኑና የበርካታ ምስክሮችን ቃል ለመቀበል 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ለፍርድ ቤቱ ጠይቋል።

ሁሉም ተጠርጣሪዎች የሰባዊ መብታቸው ተጠብቆ ውጪ ሆነው እንዲከታተሉ፤ ከአያያዛቸውና በሌሎቹ ጉዳዮች ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱም የሁሉንም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት ውድቅ በማድረግ የ33 ተጠርጣሪዎች በጉዳዩ ያላቸው ተሳትፎ በተናጥል እንዲቀርብ በማድረግ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜውን ፈቅዷል።

ሶስቱ ተጠርጣሪዎች መረጃ በማሸሽና ተጠርጣሪዎችን በመሰወር የተጠረጠሩ በመሆኑ ለሐሙስ ህዳር 6 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ለአንድ ተማሪ ህልፈት ምክንያት የሆኑ #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ መጀመሩን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገለጹ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደዱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ ላይ በተማሪው ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ህይወቱ ላለፈው ተማሪ ቤተሰቦችና ጓደኞች መፅናናትን የተመኙት ዶክተር ደብረጽዮን፥“ድርጊቱ አስነዋሪ ነው” ብለዋል።

“ትግራይ የብሄሮችና ብሄረሰቦች መኖሪያ መሆኗን አምኖ ለመጣ ተማሪ እንዲህ አይነት ተግባር መፈፀም ሰላም ወዳዱን የክልሉን ህዝብ ባህልና ታሪክ የማይገልፅ ነው” ብለዋል።

ድርጊቱን የፈፀሙ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር መጀመሩን አስረድተው፥ ተጠርጣሪዎቹ ጥፋታቸውን በማጣራት የክልሉ መንግስት ወደ ህግ የሚያቀርባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በመስዋእትነት የተረጋገጠው ሰላም በጥቂት ግለሰቦች አይደፈርስም ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ፥ “ህብረተሰቡ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መነሳት ይኖርበታል” ነው ያሉት።

በክልሉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይም በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የጠየቁት ዶክተር ደብረጽዮን፥ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኤዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia