TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዱላ አታቀብሉ፤ አታጋግሉ!⬇️

የኦነግ አመራሮች አቀባበል #ያማረ እንዲሆን እና የኦነግ ደጋፊ የሆኑ ወንድሞች ደሥ እንዲላቸው ማገዝ #ተገቢ ነው። ከፀቡ በፊትም በሰከነ
መንገድ #ተነጋግሮ መግባባት መልመድ አለብን። አላሥፈላጊ የሆነ #ፉክክር እና #ብሽሽቅ አያሥፈልገንም።

ለወጣቱ ለባለፉት 27 ዓመታት ሲሰበክለት የኖረው #ልዩነት እንጅ ወንድማማችነት እና መተባበር አይደለም። ሥለዚህ በትንሽ ነገር ወደፀብ ለማምራት ቀላል ሆኗል። ጦር ለማወጅም ማሰላሰል አያሥፈልግም። #ሞባይልን ወጣ አድርጎ መተኮሥ ነው። ሃላፊነት የማይሰማው እና #ቢራ እየጠጣ "አትነሳም ወይ" የሚል ብዙ ነው። የእብድ ገላጋዩ እና ዱላ አቀባዩ የትየለሌ ነው። የሚመክር እና አንተም ተው፣ አንተም ተው የሚል ነው የሚያሥፈልገን። በዚህ የተነሳም ሰፊው መንገድ ይጠበናል። #የምንፈልገውን ባንዲራ ለመሥቀል ሌላውን ማውረድ ተገቢ አይደለም።

ሌሎችም የሚፈልጉትን እና #አርማየ ነው የሚሉትን ቢሰቅሉ የሌላውን #መብት እሥካልነኩ ድረሥ #መብታቸው ነው። ሥንተባበር ሁሉም #ቀላል ይሆናል። ሆደ ሰፊነት ያሥፈልጋል።

ፌሥቡክ ላይ የምታጋግሉ ሰከን በሉ!
.
.
ከዳንኤል ተፈራ (የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰመጉ⬇️

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው #ጅምላ እስር በመንግሥት ሙሉ ማብራሪያ ሊሰጥበት እንደሚገባ፣ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ጥያቄ አቀረበ፡፡ #ሰመጉ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

ሰመጉ በመግለጫው ምንም እንኳን ፖሊስ ከተማዋን #ለማረጋጋት ዕርምጃ መውሰዱ #ተገቢ እንደሆነ ቢያምንም፣ ‹‹ከሕግ አግባብ ውጪ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጠነ ሰፊ እስራት መፈጸሙ፣ የጅምላ እስራቱ ሰላማዊ ዜጎችንም ጭምር ዒላማ ማድረጉ፣ ጥቂት የማይባሉ ታሳሪዎች ላይ ፖሊስ ድብደባ መፈጸሙ፣ በሕግ ወንጀል  እንዳልሆነ በግልጽ ባልተደነገጉ ሥፍራዎች ያገኛቸውን ዜጎች ማሰሩ፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እስራቶቹ መፈጸማቸው፣ እንዲሁም ሰላማዊውን ሕዝብ ጭንቀት ውስጥ በከተተና ግልጽነት በጎደለው ሁኔታ የጅምላ እስሩን መነሻ ምክንያትና የታሳሪዎችን ዕጣ ፈንታ በፍጥነት ለሕዝብ ይፋ አለማድረጉ››፣ የፖሊስን ዕርምጃ ሕጋዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የእስሩን ገፈት የቀመሱ ግለሰቦች፣ ‹‹የተቀናቃኝ ፓርቲዎች አመራሮች ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የአቀባበል ዝግጅቱን ለምን #አስተባበራችሁ? ለምን የፓርቲዎች ደጋፊዎች ሆናችሁ? የሚሉና ተመሳሳይ የምርመራ ጥያቄዎች እንደቀረበላቸው›› ሰመጉ ከታሳሪዎች ባገኘው መረጃ መሠረት ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ታሳሪዎቹን በመደበኛ ፖሊስ ጣቢያዎች ለማቆየት ያልቻለበትን ምክንያት ግልጽ አላደረገም የሚለው ሰመጉ፣ ይህ የፖሊስ ድርጊት ‹‹የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በግልጽ የጣሰ በመሆኑ፣ ከሕግ አግባብ ውጪ የተያዙ፣ ክስ ሳይቀርብባቸው ወይም ሳፈረድባቸው የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱ፤›› በማለት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

አገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በነበረችበት ወቅት በተለያዩ ወታደራዊ ካምፖች ታስረው የነበሩ ዜጎች ይደርስባቸው የነበራት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ትውስታ ከአዕምሮ ባልጠፋበት በዚህ ወቅት፣ ለሥልጠና በሚል ሰበብ መንግሥት ዜጎችን ወደ ወታደራዊ ካምፕ በማጋዙ ለሌላ ዙር መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳያጋልጣቸው የሚል ሥጋቱንም ሰመጉ ገልጿል፡፡

‹‹በሁከትና በግርግር ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል በሕግ ሥር የሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸውን ተጠብቆ የመያዝ መብታቸው እንዲከበር፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በወዳጆቻቸውና በሕግ አማካሪዎቻቸው የመጎብኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው፣ እንዲሁም #ክስ ያልተመሠረተባቸው ዜጎች በፍጥነት እንዲለቀቁ፤›› ሲል ሰመጉ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አረአያ ጋር የተደረገ ውይይት!

“እኛ የሠራነውና የመጣው ውጤት የተራራቀ ነው” ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትላንት የቅሬታ ቅጽ ሲሞሉ ውለዋል። የኦሮሚያና የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮዎች ደግሞ በአንዳንድ የአገሪቱ ትምሕርት ቤቶች በፈተና ሂደቱ ላይ የነበረው ችግር ሳይስተካከል ውጤቱ ይፋ መደረጉ #ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል። አገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አረአያ ገብረእግዚያብሔር ለአሜሪካ ድምፅ ሁኔታውን ሲያስረዱ፤ ስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት በተሰኘው ፈተና ላይ የእርማት ችግር መፈጠሩን ተረጋግጧል።

ፈተናውን ለሚያርመው ማሽኖች የተሰጡት የመልስ ቁልፎች ቦታ በመቀያየራቸው ከ319ሺሕ ተፈታኞች ግማሽ በሚሆኑት ውጤት ላይ ስህተት ተፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል ነው፤ ያብራሩት። የኦሮሚያና የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮዎች ቀረበ የተባለው ቅሬታም “ለእኛ አልደረሰንም” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ኤጀንሲው በአማራ፣ በኦሮሚያ በደቡብና በቤንሻንጉል ክልሎች የሚገኙ 848 ተማሪዎች ውጤት ይዞ እያጣራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ቴስት የተፈጠረውን የእርማት ችግር በመፍታተ የተስተካከለው ውጤት በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ እንደሚደረግም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። በሌሎች ተማሪዎች እየቀረበ ያለውን ቅሬታ በተመለከተም “ጭብጥ ያለው ከሆነ እናያለን” ሲሉ አረጋግጠዋል። የፈተናውን ውጤት አስመልክቶ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተያየት መስጠት መብት መሆኑን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ በማህበራዊ ሚድያ የሚሰጡ አስተያየቶች ግን መረጃን ብቻ መሰረት እንዲያደርጉ መክረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ / ቪድዮ ፦ የቀድሞው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ስብሃት ነጋ አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።

አቶ ስብሃት ወደ አሜሪካ ያቀኑት ለህክምና መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም አቶ ስብሐት ነጋ ለፍ/ቤት በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ገልፀው ህክምናቸውን አድርገው ለመመለስ ወደ ውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸው ክስ መስርተው እንደነበር ይታወሳል።

በህዳር 23 ቀን 2015 በነበረ ቀጠሮ ጉዳያቸውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ የፍትሃብሔር ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት አቶ ስብሃት ነጋ ወደ ውጪ ሀገር እንዳይወጡ መከልከሉ #ተገቢ_አይደለም የሚል ውሳኔ ሰጥቶ ነበር።

ይኸው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመፈጸሙን ተከትሎ አቶ ስብሃት በጠበቃቸው አማካኝነት ውሳኔው እንዳልተፈፀመላቸው ገለጸው በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል።

በዚህም በቀረበው አቤቱታ መነሻ ለምን የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዳልተፈጸመ ከፌደራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች የሚመለከታቸው ኃላፊዎች  ቀርበው  እንዲያብራሩ ከተደረገ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔው እንዲፈጸም በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

አቶ ስብሃት ነጋ በዚህ መልኩ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መነሻ  ከብዙ መጉላላት በኋላ ለህክምና ከኢትዮጲያ ወደ ውጭ ሀገር መውጣት ችለዋል።

Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
Video / Photo : Social Media

@tikvahethiopia