TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሰሞኑን ከባሕር ዳሩ ግድያ ጋር በተያያዘ የተያዙ #እስረኞች ብቻቸውን #ጨለማ ክፍል ውስጥ እንደታሰሩና አያያዛቸውን ኢሰብዓዊ መሆኑን #ጠበቃቸው ገልጠዋል፡፡ ጠበቃ #ኄኖክ_አክሊሉ ደንበኞቻቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማቆያ ክፍል ትናንት ከጎበኙ በኋላ ክፍሉ በጣም ጠባብና ቀዝቃዛ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡ ከክፍሏ የሚወጡት በ24 ሰዓት አንዴ ብቻ ነው፡፡ ቤተሰብና ወዳጅ እንዳይጎበኛቸው ተከልክለዋል፡፡ ጠበቃው የወከሏቸው ታሳሪዎች በሪሁን አዳነ (አሥራት ሜዲያ)፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ መርከቡ ኃይሌ (ባላደራ ም/ቤት) እና ማስተዋል አረጋ (የቀድሞ የገቢዎች ሚንስቴር ባልደረባ) ናቸው፡፡

Via #wezema
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኢትዮጵያ በ2 ዙር የምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቃ የውጤት ይፋ መሆን እየተጠበቀ ነው።

ምርጫው ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያለው ዜጋ የተሳተፈበት መሆኑ መግለፁ ይታወሳል።

ዛሬ አውሮፓ ህብረት ፣ እንግሊዝና ጀርመን፣ ጃፓንን ጨምሮ 12 ሀገራት ምርጫውን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የተሻሻሉ ሕችን ማውጣትን ጨምሮ ምርጫ ቦርድ የወሰዳቸውን ርምጃዎች አድንቀዋል፡፡

ሲቪል ማኅበራት በምርጫው ሂደት ያሳዩት ጉልህ ተሳትፎ አመርቂ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም ግን ፥ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በታሰሩበት ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ በተገደበበት፣ ጋዜጠኞች በሚዋከቡበት፣ የጸጥታ ችግር ባለበትና ፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ምርጫ ዘመቻ ለማድረግ በተቸገሩበት ሁኔታ ውስጥ ምርጫው መካሄዱን የገለጡት ሀገራቱ፣ የሀገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ ንግግር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

አሜሪካም ከኢትዮጵያ ምርጫ ጋር በተያያዘ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።

አሜሪካ ምርጫው በአለመረጋጋትና ግጭት ውስጥ የተካሄደ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻ እና ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ነው ብላለች።

አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሰራቸው እና ሌሎችም ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ መግባባት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ብላለች።

በድኅረ-ምርጫ ለፖለቲካዊ ንግግር፣ ግጭቶችን ለመፍታትና ለብሄራዊ ዕርቅ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ ብላለች። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡና ተኩስ እንዲቆም ድጋሚ ጠይቃለች። #Wezema

@tikvahethiopia