TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WorldCup

የኳታሩ አለም ዋንጫ ሊጀምር የወራቶች እድሜ ብቻ ሲቀሩት የአለም ዋንጫው በዛሬው ዕለት አስቀድሞ በተያዘለት ቀን #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ደርሷል።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሸራተን ሆቴል በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ የቀድሞ የባርሴሎና እና የቼልሲ የመስመር ተጫዋች ብራዚላዊው ጁሊያኖ ቤሌቲ እና የ ኮካ ኮላ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአለም ዋንጫው በሀገራችን የሁለት ቀናት ቆይታ ሲኖረው በነገው ዕለት ከ ረፋዱ 4:30 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ በመገኘት የስፖርት አፍቃሪው አብሮ ፎቶ መንሳት እንደሚችል ተገልጿል።

አስቀድሞ ዴቪድ ትሪዝጌት እንደሚመጣ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ ባጋጠመው ከአቅም በላይ የሆነ የግል ጉዳይ ሊገኝ አለመቻሉ ታውቋል።

Via @tikvahethsport (ቲክቫህ ስፖርት)
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይገምቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማን ይሆናል ? #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና ከ12:00 ጀምሮ የዓለም ዋንጫው ባለድል ለመሆን ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ። የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል ? የዋንጫው ባለቤት የሚሆነውን #ሀገር በትክክል ለመገመቱ 20 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ250 የሞባይል ብር ካርድ በሥጦታ የምናበረክት ይሆናል። 20 ትክክለኛ ገማቾች የሚለየቱ መልዕክቱን በላኩበት ቅደም ተከተል…
#Update #WorldCup

በFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እያደረጉ የሚገኙት #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና መደበኛ 90 ደቂቃውን በ2 ለ 2 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

ምንም እንኳን አርጀንቲና በሜሲ እና ዲማሪያ ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ በበላይነት ብታጠናቅቅም ፈረንሳይ በሁለተኛው አጋማሽ ቡድኗን አጠናክራው በወጣቱ ምባፔ ሁለት ጎሎች አቻ መሆን ችላለች።

ጨዋታው አቻ መሆኑን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።

ይህን የዓለም ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ፍልሚያ ሚሊዮኖች እየተከታተሉት ይገኛሉ። ማን አሸናፊ ይሆን ?

More : https://t.iss.one/tikvahethsport

@tikvahethiopia