TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬇️

ፖሊስ በቡራዩ ከተማና አካባቢው ከተፈጸመው ወንጀል ጋር በተያያዘ የተለያዩ #መረጃዎችን መያዙን ገለጸ።

በቡራዩ ከተማና አካባቢው በተፈጸመ ወንጀል በማስተባበር፣ በማነሳሳት፣ ገንዘብ በማከፋፋል እና በመኪና በመሸኘት የተጠረጠሩ እነ #ሳምሶን_ጥላሁን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ ሃሰተኛ መታወቂያ፣ የመንግስት መሃተምና ቲተር እንዲሁም በቤት ውስጥ 74 #ገጀራና ቢላ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ በተጠረጠሩት ሳምሶን ጥላሁን፣ አለሙ ዋቅቶላ፣ ቡልቻ ታደሰ፣ ሃሺም አሚር፣ ሽፈራሁ ኢራና እና አሊ ዳንኤል አስተያየት እና መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራን አዳምጧል።

መርመሪ ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለ ጀምሮ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ባንኮች የገንዘብ ዝውውሩን እንዲገለጽ ደብዳቤ መላኩን ገልጿል።

1ኛ ተጠርጣሪ ሳምሶን ጥላሁን የነዋሪዎችን መሬት #በመቀማትና ለሌለች አሳልፎ በመስጠት ግጭት አንዲፈጠር ማድረጉን ፖሊስ መረጃ እንዳለው ገልጿል።

የበርካታ ወጣቶች ፎቶና ሃሰተኛ መታወቂያ የመንግስት #መሃተምና ቲተር በተጠርጣሪው እጅ መገኘቱንም አስረድቷል።

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አቀባበል ድጋፍ በወጡ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ፓስተር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሽጉጥ መተኮሱምን ነው ፖሊስ የገለጸው።

ሶስተኛ ተጠርጣሪም በቡራዩ በቤቱ ውስጥ ለወንጀሉ መፈጸሚያ የሚውል 74 ገጀራና ቢላ መያዙን የገለጸው። ፖሊስ የቀሩ ተጠርጣሪዎችም መስከረም 5 #በመንግስት_ተሽከርካሪዎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ማመላለሳቸውንና ገንዘብ ማከፋፈላቸውን ለችሎቱ አብራረቷል።

ለተጨማሪ መረጃ የሟቾችን አስከሬን ምርመራ ውጤት እና የተባባሪ ግብረሃይሎችን በቁጠጥር ስር ለማዋል የ28 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድቤቱን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ሳምሶን ጠበቃ በበኩላቸው ፖሊስ በተናጠል እና በዝርዝር የያንዳንዳቸውን ተሳትፎ አልገለጸም አሁን ሽብር ድርጊት ነው፣ የተባለውም ተጠርጣሪዎችን በእስር ለማቆየትና ዋስትና ለማስከልከል ነው፤ ፍርድ ቤቱ ይህን ከግምት አስገብቶ ዋስትና ይፍቀድና ክርክሩን በውጭ ሆነው ያካሂዱ ሲሉ ጠይቀዋል።

ተጠረጣሪዎቹ ሁሉም በተናጠል በአንደበታቸው ፖሊስ እያደረገው ያለው ምርመራ አኛን ለማሰር ነው ወንጀሉን አልፈጸምንም፣ አያያዛችንን በተመለከተ ከአይምሮ ህሙማን ጋር ታስረን #ስንሯሯጥ ነው የምናድር፣ ጨለማ ውስጥ ነው የታሰረነው ሰባዊ መብታቸን ይጠበቅ የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበው ምርመራ የሸብር ድርጊት መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን፥ ዋስትና አያሰጠም ሲል ለመርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አከናውኖ እንዲቀርብ ለጥቅምት 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የተጠርጣሪዎችን ሰባዊ አያያዝ በተመለከተም የአዲስ አበባ ፖሊስም ሆነ ፌዴራል ፖሊስ ማስተካከያ አንዲያደረግ ትዛዝ ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ወንጀል የተጠረጠሩ ከ250 በላይ ተጠርጣሪዎች ለዛሬ በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት በቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እየሰጡ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ፖሊስ እስካሁን በተሰጠው የ14 ቀን ጊዜ ከወንጀሉ ውስብስብና ሰፊ መሆን ጋር ተያይዞ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም የተጠርጣሪዎችን ቃል ተቀብሏል፤ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን የምስክርነት ቃል ለመቀበልና ዝርዝር ምርመራ ለማከናወን ተጨማሪ 14 ቀን ጊዜ ጠይቋል።

በዚህም የወረዳው ፍርድ ቤትም ለፖሊስ የስምንት ተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia