TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ADAMA የአዳማ ከተማ የከሰዓቱን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የቲክቫህ አዳማ ቤተሰቦች በፎቶ አስደግፈው ልከውልናል።

PHOTO: IBRO(አዳማ ቲክቫህ ቤተሰብ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

"አዳማ ዛሬ ከነጋ ጀምሮ በሁሉም አቅጣጫ #ሠላም ነው። ሠላማዊ ህይወት እንድቀጥል ህዝባችን በማህበራዊ ሚድያ በማይታወቁ እና አከባቢው ላይ በማይገኙ ሰዎች የሚረጨውን የክፍፍል ወሬ ችላ በማለት ለሠላም ሊተጋ ይገባል።" ባይሳ(ቲክቫህ ቤተሰብ) ከአዳማ ፖስታቤት አከባቢ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

የአዳማ ከተማ የዛሬ ውሎ ፍፁም የተረጋጋና ሰላማዊ ነው። የንግድ ተቋማት ወደስራቸው ተመልሰዋል፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ወደቀደመው ሁኔታ እየተመለሰ ይገኛል። አብዛኛው የትምህርት ተቋማት ግን ዛሬም እንደተዘጉ ናቸው ተማሪዎች አልተገኙም። የቲክቫህ ቤተሰቦች እንደሚሉት በተማሪዎች መካከል ግጭት እንዳይፈጠር በመስጋት ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት አላኩም ብለዋል። በትላናንትናው ዕለት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከተማይቱ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷን ገልፆ በቀጣይ ቀናትም ትምህርት ቤቶች ወደ ስራ ይመለሳሉ ሲል ገልጿል።

PHOTO: IBRO(አዳማ ቲክቫህ ቤተሰብ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA #JIMMA #BALE_ROBE

ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ዛሬ በአዳማ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በኮንፈረንሱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይም በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ካሉ ዞኖችና ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ የሆኑበት የሰላም ኮንፈረንስ በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው። በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር ዞን፣ ባሌ ሮቤ እና ከጅማ ከተማ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 600 የሚልቁ ነዋሪዎች ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመምከር ላይ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት፥ በጥፋት ድርጊቶች ውስጥ የተሳተፉ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነት ይረጋገጣል።

ባሌ ሮቤ ላይ በተደረገው ውይይት የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ሰሞኑን የተፈጸመው ድርጊት ህብረተሰቡን እንደማይወክል ተናግረዋል። አያይዘውም እንደዚህ አይነት ዋጋ መክፈል እንደማያስፈልግ ጠቅሰው፥ ችግሮች ሲከሰቱ መመካከርና መደማመጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ውይይቱ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የታየውን የሰላም እጦት ችግር ከመሰረቱ ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA -- የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር የብሄርና የሃይማኖት ብዝሃነትን በአግባቡ ለማስተዳደር የሃይማኖት አባቶችና የህብረተሰቡ ሚና በሚል ርዕስ ያዘጋጀዉ ክልል አቀፍ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነዉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀይማኖት መሪዎች የህዝቦችን መስተጋብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለፁ። የህዝቦች የእስር በርስ መስተጋብር እንዲጠናከርና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ፡፡ በዛሬው እለት ከኦሮሚያ ክልል ሁሉም አካባቢዎች የተወጣጡ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካች የተገኙበት የሰላም ኮንፍረንስ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

(ዋልታ ቴሌቪዥን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ODP #ADAMA

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የክልል አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም እና መተዳደሪያ ህገ ደንብ ዙሪያ እየመከሩ ነው። በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ውይይት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የኦዲፒ የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።

በምክክር መድረኩ በውህድ ፓርቲው ፕሮግራም፣ በመተዳደሪያ ህገ ደንብና የድርጅቱ አወቃቀር ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ባለፈም በፓርቲው ዙሪያ በሚነሱ የተለያዩ የግልጸኝነት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADAMA

ወጣቶች "የሰላም ኃይል" በመሆን በሀገሪቷ ውስጥ የሚስተዋሉ ግጭቶች ለማስቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ። “ወጣቶች ለሰላም ”በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ዛሬ አዳማ ከተማ ተጀምሯል።

የጉባኤው ምክትል ፀሐፊ አቶ ሂሉፍ ወልደስላሱ በኮንፍረንሱ መድረክ  እንዳሉት በቅርቡ በሀገሪቱ እየተበራከቱ በመጡት ግጭቶች ውስጥ ወጣቶች ተሳታፊና ተጎጂዎችም ናቸው። በተሳሳተ መረጃና በስሜት በመገፋት ግጭቱ የሚያስከትለውን ጉዳትና ቀውስ ካለማመዘን ወጣቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ አመላክተዋል።

“ግጭቶች በባህሪያቸው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጎዱ በመሆኑ ችግሮቹን ለማከምና ለማስወገድ ሁላችንም አንድ ሆነን መስራት አለብን“ ብለዋል። በተለይም ወጣቶች የሰላም ኃይል መሆናቸውን ተገንዝበው በሀገሪቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ግጭቶች ለማስቆምና አለመግባባቶች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

https://telegra.ph/ETH-12-12-2

(ENA)

@tikvahethiopia
#ADAMA

በአፋርና ሶማሌ ወንድማማች ህዝብ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በመፍታት እርቀሰላም ለማውረድ በሚደረገው ጥረት  የአገር ሽማግሌዎችና ዑጋዞች ሚናቸውን በግንባር ቀደምነት እንዲወጡ የሰላም ሚኒስቴር አስገንዝቧል። የኢትዮጵያ የአገር ሽማግሌዎች መማክርት በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባበት ለመፍታት በአዳማ ከተማ ዛሬ መምከር ጀምሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KFO #OFC #ADAMA

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] በአዳማ ሊያደርግ የነበረው ህዝባዊ ውይይት በፀጥታ ኃይሎች መከልከሉን የአዳማ ቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀውናል።

ውይይቱ ለምን? በማን? ሊከለከል እንደቻለ ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ቤተሰቦቻችን ተናገረዋል። ውይይቱ ለመካፈል መጥተው የነበሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውም ተገልጾልናል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia