TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጄነራሎቹን ገድሏል ስለተባለው የግል ጠባቂ...

ቅዳሜ ሰኔ 15/2011 ምሽት ጠቅላይ ኤታማዦር ጄነራል ሰዓረ መኮንን ከአጋራቸው ጄነራል ገዛዒ አበራ ጋር በገዛ ጠባቂያቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።

በቀጣዩ ቀን የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ ጄኔራሉን እና ወዳጃቸውን በጥይት መትቶ #ገድሏል የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ አስታውቆ ነበር።

ሰኞ ከሰዓት ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ጄኔራሎቹን ገድሏል የተባለው ጠባቂ ራሱን ማጥፋቱን ተናገሩ። ሰኞ ምሽቱን ደግሞ ፌደራል ፖሊስ ቀደም ሲል ራሱ የሰጠውን መግለጫ አስተባብሎ ጠባቂው በሕይወት እንደሚገኝ አስታውቀ።

እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች እንዴት ሊወጡ ቻሉ? ጄነራሎቹን ገድሏል የተባለው ጠባቂስ አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል? የጠቅላይ ሚንሰትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉስ ጥላሁን፦

''በአዲስ አበባም ይሁን በባህር ዳር የተፈጠረው ችግር ድንገተኛ ነው፤ አደናግጧል፤ አደናብሯል። ሁሉም መረጃ በአንድ ግዜ አይገኝም። በወቅቱ የሚደርሱ መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሃን ሲሰጡ ነበረ። መረጃዎች የሚስተካከል፤ የሚታረም ነገር ሊኖራቸው ይችላል። ሰው ነው የሚሰራው፤ ሰው ነው የሚናገረው። መረጃው ደግሞ ታቅዶ፣ ተደራጅቶ፣ ተገምግሞ የሚሰጥ ዓይነት መረጃ አይደለም። እንደዚህ አስቸኳይ በሆነበት ሰዓት፣ ሕብረተሰቡ መረጃ በሚፈልግበት ሰዓት፣ መገናኛ ብዙሃን በሚያጣድፉበት ሰዓት እንዲህ ዓይነት ስህተቶች አያጋጥሙም ማለት አይደለም'' ይላሉ።

ተጠርጣሪው እንዴት በቁጥጥር ሥር እንደዋለ እና አሁን ስለሚገኝበት ሁኔታ የተጠየቁት አቶ ንጉሱ፤ ''የግል ጠባቂው በጄነራሎቹ ላይ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ተታኩሶ ነበረ። በዚህም የተኩስ ልውውጥ እሱም ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት እና ወደ ህክምና ሥፍራ ተወስዶ ጥበቃ እየተደረገለትና የጤና ክትትል እያደረገ ነው'' ነው ሲሉ መልሰዋል።

''የጤንነቱን ጉዳይ ሃኪሞች፤ የጥበቃውን ሁኔታ ደግሞ የጸጥታ መዋቅሩ እየሰሩ ነው። ሌሎች ጉዳዮች ወደፊት የሚጠሩ ይሆናሉ'' በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

Via #BBC
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia