TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WFP

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከመደበኛ እርዳታ ውጪ ለ62,900 አባዋራዎች የምግብ እርዳታ አቀርባለሁ ብሏል።

ከቀናት በፊት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

ውይይቱ በሶማሊ ክልል ውስጥ በአንድ አንድ ቦታዎች የተከሰተዉን ድርቅ ለመቋቋም ያለመ ነው።

በዉይይቱ ላይ አቶ ሙስጠፋ ፥ በተለይ ዳዋ ዞን ከፍተኛ የድርቅ አደጋ የተከሰተባቸዉ ቦታዎች አንዱ መሆኑን በመግለፅ በአሁኑ ወቅት የዓለም ምግብ ፕሮግራሙ ከሚሰጠው መደበኛ እርዳታ ዉጪ አስቸኳይ እርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸዉ የሚመሰገን ስራ ነዉ ብለዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ስቲቨን ዌር ኦማሞ ከክልሉ መንግሥት ጋር በድርቁ ሁኔታ ዙሪያ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው የሶማሊ ክልል መንግስት ድርቁን ለመቋቋም ላደረገው ቁርጠኝነትና 200 ሚሊዮን ብር በመመደብ የሰራዉን ስራ ምስጋና በማቅረብ ድርሻቸዉን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ኃላፊው በዳዋ ዞን ውስጥ ለሚገኙ የድርቁ ተጎጂዎች ለሆኑ 62,900 አባዋራዎች በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያደርሱ ተናግረዋል።

#SomaliRegionCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዳዋ ዞን ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ ፦ በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተው ድርቅ የሞቱት የቁም እንስሳት 47,215 መድረሳቸውን ከአንድ ሪፖርት መመልከት ችለናል። ሪፖርቱ የተዘጋጀው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በተካሄደ ዳሰሳ ሲሆን ይህም የተመራው በዳዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ በዳዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት፣ ከዞኑ የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና…
#SomaliRegion

በሶማሊ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች እገዛ እንዲደረግ ተጠየቀ።

የሶማሊ ክልል የሰላም እና አንድነት ምክር ቤት በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ አሰመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፦

1. የክልሉ ህዝብ በተፈጥሮ ድርቅ አደጋ ምክንያት ከቀያቸዉ የተፈናቀሉ ወንድሞቻቸዉን ባላቸዉ ነገር በማገዝና ከጎናቸዉ በመቆም።

2. የክልሉ ማህበረሰብ ባላቸዉ ነገር በድርቅ የተጎዱና አቅመ ደካማ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎችን በመረዳት።

3. ዲያስፖራው ማህበረሰብ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው የተፈጥሮ ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ።

4. ግብረሰናይ ድርጅቶች በድርቅ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

#SomaliRegionCommunication

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹

የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች በአፍሪካ ቀንድ እየተስተዋሉ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

የሀገር ሽማግሌ ገራድ ኩልሚዬ ገራድ መሐመድ ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነገር ሁሉ የሶማሌ ክልል ህዝብ ጉዳት በመሆኑ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን የሀገርን ጥቅም ለማስከበር መሰራት አለበት።

የተለያዩ ሀይሎች ወደ ሶማሊያ መጥተው የአፍሪካ ቀንድን ለማበጣበጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴን እንቃወማለን።

ሀይሎቹ ለጎረቤት ሶማሊያ ህዝብ ጥቅም የሚያመጡ ሳይሆኑ ጦርነት በመክፈት ችግር የመፍጠር ዓላማ ያላቸው በመሆናቸው ህዝቡ ሊቃወማቸው ይገባል።

የሶማሌ ክልል ህዝብ እና የሶማሊያ ህዝብ ድንበር ቢለያቸውም ወንድማማቾች በመሆናቸው የአብሮነት ታሪካቸውን ሊጠብቁት ይገባል።

ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት መብቷን ለማረጋገጥ የምትሰራቸውን ስራዎች የሶማሌ ክልል ህዝብ ይደግፋል።

የባህር በር ጥያቄ አብረን የምናድግበት እንጂ የሚያራርቀን አጀንዳ እንዳልሆነ ለጎረቤቶቻችን ሶማሊያውያን ማሳወቅ እንወዳለን " ብለዋል።


የሀገር ሽማግሌ ኡጋዝ አሊ ምን አሉ ?

" ሶማሊያ ከሩቅ ሀገራት ይልቅ ከጎረቤቶቿ ጋር በመወያየት የሚፈጠሩ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ አግባብ ልትፈታ ይገባል።

ከውጭ የሚመጡ ኃይሎች የኢትዮጵያንና የሶማሊያን ጉርብትና ከማበላሸት ያለፈ ዓላማ አይኖራቸውም " ብለዋል።


ሌላ በውይይቱ ምን ተባለ ?

- ሶማሊያውያን ችግር በገጠማቸው ጊዜ ሁሉ ቀድማ የምትደርሰው ኢትዮጵያ ናት። ይህ አጋርነት እንዲቀጥል የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።

- የኢትዮጵያ ህዝብና የሶማሊያ ህዝብ ሽብርተኝነትን አብሮ እንደተዋጋ፣ ሰላምን የሚያደፈርስ ሌላ ኃይል በመካከል ሊገባና ሊጎዳቸው አይገባም፤ ይህን ሁሉም ሊረዳው ይገባል።

- የአፍሪካ ቀንድን በእጅ አዙር ችግር ውስጥ ለማስገባት የሚጥሩ ኃይሎች ዕድል እንዳያገኙ ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል።

- ሳማሊያውን የራሳቸው ያልሆኑን ጦርነት ወደ ሀገራቸው በመጋበዝ ቀጠናውን ወደ ቀውስ እንዳይከቱ።

በውይይት መድረኩ ፥ በአሁኑ ወቅት ከ500 ሺህ በላይ የሶማሊያ ስደተኞች በኢትዮጵያ መኖራቸው ፤ ባለፋት ዓመታትም በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኞች መጠለያቸው ኢትዮጵያ እንደነበረችና ሀብት ንብረትም ማፍራታቸው ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ሶማሊያውያን በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ እየተማሩ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

#SomaliRegionCommunication

@tikvahethiopia