TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ወላይታዞን

“ ከ1,000 በላይ መምህራንና የቢሮ ሠራተኞች የሐምሌ ደመዎዝ አልተከፈለንም ” - የወላይታ ዞን መምህራን 

“ በአራት ወረዳዎች ሙሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው ” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ

በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው፣ በዚህም የትምህርት ሥራ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተጀመረ መምህራኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ክፍያ አለመፈጸሙን ተከትሎ አብዛኛዎቹ መምህራን ለማስተማር ፈቃደኞች ባለመሆናቸው የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደተስተጓጎለ ነው የገለጹት።

“ ከ1,000 በላይ መምህራንና የቢሮ ሠራተኞች የሐምሌ ደመወዝ አልተከፈለንም ” ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ እንኳን ደመወዝ ሳይከፈል ተከፍሏቸውም ኑሮውን መቋቋም እንዳልተቻሉ ባለስልጣናቱ በደንብ ሊረዱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ያልተከፈለውን ጨምሮ ከዚህ ወዲያ ደመወዛቸው በወቅቱ እንዲፈጸምላቸውም በአንክሮ ጠይቀዋል። 

ለምን ክፍያው አልተፈጸመም ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ  የጠየቃቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጉደና ሙሉ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው አምነው ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

“ አራት የወረዳዎች ላይ ሙሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው። የሐምሌ ወር ክፍያ ላልተፈጸመላቸውም ወረዳዎች ገቢ ሰብስበው እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው።

ከዚህ በፊትም ይታወቃል ከበጀት ካሽ ጋር ተያይዞ ወላይታ ዞን ላይ የደመወዝ ችግር ነበር። አሁን ግን እሱ ተቀርፎ ከዚህ በኋላ ሁሉም ሠራተኞች ሙሉ ደመወዝ ያገኛሉ።

በዞኑ ወረዳዎች የሚጠቀሟቸው በርካታ እዳዎች ስላሉ የሐምሌን ደመወዝ ሰብስበው እንዲጠቀሙ የሚል አቅጣጫ ተቀምጦ በዛው መልክ እየተሰራ ነው ያለው።

የመምህራን ብቻ ሳይሆን ሁሉም የመንግስት ሠራተኞች ወረዳዎች ላይ ሙሉ ደመወዝ አላገኙም። ግን ክፍያቸው እስከ 70 ፐርሰንት የደረሰ፤ እየጨረሱ ያሉ ወረዳዎችም አሉ።

ከሞላ ጎደል ችግሮች እየተፈቱ ነው። የሐምሌ ደመወዝ ስላልተከፈለ በሚል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የትምህርት ሥራን ለማስተጓጎል የሚሞከሩ ሙከራዎች አሉና እሱ ተገቢ አይደለም።

አለመከፈሉ ስህተት ነው ግን በተከፈለው ደመወዝ ሥራ መስራት ይገባል። እየሰሩ ይጠይቁ ”
ብለዋል።

በዞኑ የመምህራንን ጨምሮ የሌሎችም የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱ አለመፈጸም በተደጋጋሚ ማጋጠሙ የሚታወቅ ሲሆን ሠራተኞቹ የከፋ ችግር ለማሳለፍ እንደገደዱ እንደሆነ ከዚህ ቀደምም ሲያማርሩ ነበር።
 
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia