TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የወላይታ ሶዶ ውሎ‼️

በደቡብ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ የተባሉ ቤቶች #መፍረሳቸውን ተከትሎ በከተማይቱ ዛሬ ግርግር እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ። በከተማይቱ #የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርም የዓይን እማኞቹ ገልጸዋል።

አቶ ዳንኤል ዓለሙ የተባሉ የከተማይቱ ነዋሪ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በከተማይቱ #ግርግር የተቀሰቀሰው ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ ነበር። የግርግሩ መነሻም በተለምዶ “የጨረቃ ቤቶች” ተብለው የሚጠሩ በከተማይቱ ዙሪያ ከተገነቡ መኖሪያ ቤቶች መፍረስ ጋር የተያያዘ እንደሆነም ገልጸዋል። “በጣም ግርግር ነበር። የተወሰነ ጥይት ተኩሰዋል። ሰው ሩጫ ላይ ነበር” ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የከተማይቱ ነዋሪም ከቀኑ ስድስት በኋላ ጥይት ይሰማ እንደነበር አረጋግጠዋል። የቤቶችን መፍረስ በመቃወም መንገድ ዘግተው የነበሩ ሰዎችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱንም የዓይን እማኙ ገልጸዋል። ግርግሩን የፈሩ ሱቆች እና ምግብ ቤቶች ተዘግተው መዋላቸውን የሚናገሩት እኚሁ ነዋሪ ወደ 10 ሰዓት ገደማ ግን ከተማይቱ “ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተመልሳለች” ብለዋል።

በወላይታ ሶዶ ህገወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች እየፈረሱ የሚገኙት ቀድሞ የገጠር ቀበሌዎች የነበሩ ነገር ግን ከአንድ ዓመት ወዲህ በከተማይቱ ክልል ስር በተካተቱ ሶስት አካባቢዎች እንደሆነ ነዋሪዎች ለDW አስረድተዋል። ላሬና፣ ኦፎሳሬ እና ቆንቶ በተባሉት በእነዚህ ቦታዎች የእየፈረሱ ያሉት ቤቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የኮሚዩኒኬሽን የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መንግስቱ ቶራ ዛሬ በከተማይቱ የተፈጠረው ግርግር “የህገ ወጥ ግንባታን ለመከላከል እየተደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ አይደለም” ሲሉ አስተባብለዋል። “ሰባት ሰዓት አካባቢ ጎማ በመቃጠሉ ሰዉ አመጽ ሊቀሰቀስ ነው በሚል ሰግቶ፣ ፈርቶ ነበር። ግን ምንም ነገር የለም። ተረጋግቷል” ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

የከተማይቱ የባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ ካለፈው ከትላንት ጀምሮ የሶዶ ከተማ አስተዳደር እና በዙሪያ ያለው ወረዳ ህገወጥ ግንባታ የመከላከል እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ አስታውቋል። በህገወጥ ግንባታ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች “ስራውን ለማስተጓጎልና የከተማውን ጸጥታ ለማወክ” መሞከራቸውንም ጠቁሟል። “መንገድ በመዝጋት፣ ደን የማቃጠል ሙከራ በማድረግ እና ሌሎች ችግሮችን ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል” ያላቸው ግለሰቦችም “#በቁጥጥር ስር ውለዋል” ብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia