TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ👆

"በአሁን ሰዓት መላው የዩንቨርሲትው ማህበረሰብ ፊቼ ጫምባላላን በደማቅ ሁኔታ እያከበርን ነው። በዝግጅቱ ላይ ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ ተማሪዎች እና የጊቢው ሰራተኞች በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ። በአከባበሩ ላይ ላይ የተለያዩ በአሉን የሚያንፀባርቁ ዝግጅቶች እየቀረቡ ይገኛሉ።"

Via #KIYA ~~ /TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሃዋሳ~አዳሬ ሆስፒታል👆

"በሃዋሳ ከተማ ~~ በሀዋሳ አዳሬ ሆስፒታል "ፊቼ ጫምባላላን" በማስመልከት የደም ልገሳ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።"

ደም በመለገስ ህይወት እናድን!!

Via Dr. Hanibal Abera /TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለ2ኛ ጊዜ #የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ሙሃመዱ ቡሃሪ እና ምክትላቸው ፕሮፌሰር ዬሚ ኦሲንባጆም በዛሬው እለት በዋና ከተማዋ በአቡጃ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡

ሙሃመዱ ቡሃሪ የፕሬዝዳንትነቱ ስልጣን የመጨረሻቸው እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ይካቲት በተደረገው ዳግም ምርጫ ከ15 ሚልዮን በላይ መራጮችን ድምፅ አግኝተው ነበር ዳግም የተመረጡት፡፡

ድምፅ ለመስጠት ከተመዘገቡት 84 ሚሊዮን መራጮች መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ነበር ድምፅ የሰጡት፡፡

በበዓለ ሲመቱ የ29ኙም የናይጄሪያ ግዛቶች ዋና ገዢዎችን፣ ጨምሮ የሐገሪቱ ከፍተኛ ባለመስጣናት ተሳትፈዋል፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካን ኒዉስ/etv/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአቶ #ዳውድ_ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ከኦዴፓና ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ።በሃገር ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የኦነግ ታጣቂ ወደ ካምፕ ለማስገባት የተሰራው ስራ ላይ የማጠቃለያ ሪፖርት ዛሬ ቀርቧል። ሪፖርቱ በመንግስትና በኦነግ የዕርቀ ሰላም ኮሚቴና የሃገር ሽማግሌዎች አማካኝነት፥ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነው የቀረበው።

ከሪፖርቱ በኋላ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦነግ አመራሮች፥ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነትና አንድነት ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ኦነግ የክልሉ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚሰራቸውን ስራዎች #እንደሚደግፍም ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ተናግረዋል። አያይዘውም ከዚህ በኋላ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሰራዊት እንደማይኖርም ገልፀዋል።

Via #FBC
ፎቶ፦ #ጃዋር_መሃመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሃገር ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረውን #የኦነግ ታጣቂ ወደ ካምፕ ለማስገባት የተሰራው ስራ ላይ የማጠቃለያ ሪፖርት ቀረበ። ሪፖርቱ በመንግስትና በኦነግ የዕርቀ ሰላም ኮሚቴና የሃገር ሽማግሌዎች አማካኝነት፥ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነው የቀረበው።

ከሪፖርቱ በኋላ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦነግ አመራሮች፥ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነትና አንድነት ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ኦነግ የክልሉ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚሰራቸውን ስራዎች እንደሚደግፍም ሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ተናግረዋል።

Via #BBC
ፎቶ፦ ጃዋር መሃመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሉምበርግ ዘገባን አጣጣለ። ብሉምበርግ ዛሬ ባስነበበው ዘገባ በኢቲ 302 ከመከስከሱ በፊት የአየር መንገዱ ፓይለት ለአለቆቹ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር ብሏል።

የብሉምበርግ ዘገባ እንደሚለው ከሆነ ብረንድ ካይ ቮን ሆሰሊን የተባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ ከአደጋው በፊት ማለትም ታህሳስ 4 2011 ዓ.ም. ለከፍተኛ የአየር መንገዱ ባለስልጣናት በላከው ኢሜይል የኢንዶኔዢያ አየር መንገድ አይነት አደጋ እንዳይከሰት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን በተመለከተ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች ተጨማሪ ስልጠና እና የግንኙነት ዘዴዎችን በተመለከተ ስልጠና መሰጠት አለበት ብሏል።

የኢሜይል መልዕክቱን ተመልክቸዋለሁ የሚለው ብሉምበርግ፤ ኢሜይሉን ጽፏል የተባለውን ብረንድ ካይ ቮን ሆሰሊን አግኝቶ ማነጋገር አለመቻሉን እና የኢሜይል መልዕክቱንም ያገኘው ስሙ እንዲጠቀስ ከማይሻ ግለሰብ እንደሆነ በዘገባው አስፈሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ የቡሉምበርግ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም የብሉምበርግ ዘገባ ሙሉ በሙሉ መሰረተ ቢስ እና እውነታ የሌለው ነው ብሎታል።

‘‘በዘገባው ላይ የዜናው ምንጭ ሆኖ የተጠቀሰው አብራሪ በስነ-ምግባር ጉድለት እና የድርጅቱን አሠራር መከተል ባለመቻሉ ከአየር መንገዱ ጋር የነበረው የሥራ ስምምነት በአጭሩ የተቋረጠበት ግለሰብ ነው’’ ብሏል አየር መንገዱ።

መግለጫው አክሎም አብራሪው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያካበተውን ዝና ለማጠልሸት እየሰራ ስለሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ሲል ያትታል።

ከዚህ ቀድም ይፋ ተደርጎ የነበረው የኢቲ 302 የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶች አብራሪዎቹ ይህንን በረራ ለማድረግ የሚያችላቸው ብቃትና የምርመራ ፍቃድ እንደነበራቸው እንዲሁም አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለውን ቅድም ተከተል ቢፈጽሙም እንዳልተቻላቸው ይፋ ማደረጉ ይታወሳል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሃምሊን ፊስቱላ ማዕከል መሥራች ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ሐውልት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በተገኙበት ተመረቀ። ሐውልታቸው የቆመው በአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች በሚገኘው የሃምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆስፒታሉን ጎብኝተዋል።

"ዶ/ር ሃሚሊን ለምን እንደተፈጠሩ ያወቁ እድለኛ እናት ናቸው” ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia