TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድራዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምን ተፈጠረ

ከዛሬ 3 ቀን በፊት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተፈጠረው ችግርን በተመለከተ ጉዳዩን ያውቁታል ከተባሉ የዩኒቨርሲቲው አካላት እና ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ይህን መረጃ አግኝቻለሁ።

መንስኤው፦

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፌደራል ፖሊስ በቋሚነት የፀጥታ ማስከበር ስራ ይሰራል። ባሳለፍነው ዓርብ ዕለት ግን ከዚህ ቀደም የነበሩት ፖሊሶች በአዳዲስ የፌደራል ፖሊስ አባላት ይተካሉ። የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ወደ ግቢው ሲገቡ ምንም ከተማሪ ተወካዮች ጋር ትውውቅ አልተደረገም፤ ከአመራሩም ጋር ምንም ትውውቅ አልተደረገም። እነዚህ ፀጥታ አስከባሪዎች ሲገቡ የላይኛው አመራርም ሆነ የተማሪ ተወካዮች የሚያውቁት ነገር አልነበረም።

እሁድ፦

እሁድ ዕለት በቶኒ በር በኩል ከእምነት ተቋማት ወደ ግቢው የሚገቡ ተማሪዎች ነበሩ። ከተማሪዎቹ መካከልም ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ያደረገ ተማሪ ወደግቢው ለመግባት ይሞክራል። የፀጥታ አካላቱ እንዲህ አይነት ይዘት ያለው ልብስ ለብሶ መግባት እንደማይቻል ይገልፃሉ። ተማሪዎቹም ከዚህ ቀደም ያለምንም እገዳ እንደሚገቡ ይናገራሉ። በዚህ መሀል አለመግባባት ይፈጠራል። ከፌደራል ፖሊስ አንዱ ተማሪው የለበሰውን ልብስ የቦጫጭቀዎል፤ ተማሪውንም እራቆቱን እንዲቀር ያደርጉታል። በዚህ ድርጊት የተበሳጩ ሌሎች ተማሪዎች በፀጥታ አስከባሪዎች ላይ ድንጋይ መወራወር ይጀምራሉ። ነገሩን ለማብረድ ፖሊስ ወደ ላይ ይተኩሳል። በዚህ መሃል አንድ የፖሊስ አባል በድንጋይ ይፈነከታል። ከዚህ በኃላ ነው እንግዴ ፖሊሶች ያገኙትን ተማሪ በየብሎኩ እየገቡ መደብደብ የጀመሩት። ብሄር፣ ማንነት ሳይመርጡ በግቢው ያሉት ተማሪዎች ላይ ድብደባ ይፈፅማሉ። የተማሪዎችን ድብደባ የሰሙት የተማሪ ተወካዮች ለከፍተኛ አመራሮች ደውለው በአፋጣኝ ይህ ድርጊት እንዲቆም ይጠይቃሉ። የግቢው አመራር ምንም የማድረግ አቅም አልነበረውም። መረጃውን ያደረሰኝ ወዳጄ እንደነገረኝ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ጭምር በፌደራል ተመቷል።

ከብዙ ጥረት እና ድካም በኃላ ፌደራል ፖሊሶቹ እያደረጉ ያሉትን ነገር እንዲያቆሙ ይደረጋል። በድብደባው የተጎዱ ተማሪዎች በርካቶች ነበሩ፤ የደሙ የቆሰሉ ብዙ ናቸው። ጉዳት የደረሰባቸውም ከፍተኛ ፤ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ተብሎ ተከፍለዋል። ዛሬም ድረስ ራሱን ስቶ ሆስፒታል የሚገኝ ተማሪ አለ። ይህ የሆነው እስከ ቀኑ 6:00 ብቻ ነው።

√በግቢው ሀይማኖታዊም ሆነ ፖለቲካዊ አጀንዳዎችን ማራመድ አይቻልም። አንዳንድ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እየተሰራ ነው። ነገሮች እስኪስተካከሉ ድረስ የተማሪዎች ህብረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በተሰላሰለ መንገድ ሲሰራ ቆይቷል።

በበር አካባቢና ሌሎች ቦታዎች ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት የስራ ተዋረዱን ሲያስረዱኝ፦ ችግር ሲኖር በቅድሚያ ተማሪዎችን ጥበቃዎች ያናግሯቸዋል፤ ከመቀጠል የተማሪ ህብረት ጉዳዩን ያየዋል፤ ከአቅም በላይ ከሆነ ብቻ ወደ ፌደራል ፖሊስ ይጠቆማል። ባለፈው እሁድ ግን ይህን ተዋረድ የተከተለ ስራ አልተሰራም ምናልባትም ፌደራል ፖሊሶቹ አዳዳሲ በመሆናቸው ሊሆን ይችላል።

ከሰዓት ምን ተፈጠረ...

ነገሩ በትንሹም ቢሆን በርዶ ነበር። ተማሪውም በግቢው ውስጥ ለነበረ የእግር ኳስ ጨዋት ወደ ስታዲየም ይሄዳል። የኳስ ጨዋታው ጥዋት በግቢው ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ነገር ተረስቶ በርካቶች የታደሙበት ነበር። በውድድሩ መሃል ችግር ይገጠራል። ችግሩ የተፈጠረው ከዚህ ቀደም በነበረ ቁርሾ እንደሆን ጉዳዩን ያስረዱኝ ተማሪዎች ገልፀውልኛል። በሜዳ ዙሪያ በተሰማው ወሬ በተማሪዎች መካከል አለመግባባት እና ግጭት ይፈጠራል።

√ከወር በፊት በሁለት ተማሪዎች መካከል የተፈጠረ የግል ፀብ ወደ ብሄር መልክ ተቀይሮ ችግሮች ተፈጥረው ነበር። በወቅቱ ችግሩን ለመፍታት ብዙ ጥረት ተደርጎ ነበር።

የዩኒቨርሲቲው ድክመት...

ከወር በፊት በነበረው አለመግባባት የማስታረቅ እና የማስማማት ስራ ሲሰራ ዋና ችግሩ የሚመለከታቸውን አካላት ላይ የማግባባት ስራ አልተሰራም። ተደብድበናል፤ ተበድለናን የሚሉትን አካላት ላይ የማስማማት ስራ አልሰራም። ይህ ድክመት ችግሩ ሙሉ በሙሉ እንዳይፈታ እና ዛራም ድረስ ችግር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።

ከጨዋታ በኃላ...

በኳስ ጨዋታ ሜዳው የተፈጠረው ችግር መልኩን ቀይሮ አድማሱን አስፍቶ ተማሪዎች እርስ በእርስ እንዲጋጩ ምክንያት ሆኗል። ችግሩ ሰፍቶ ሰኞ ትምርት እዲቋረጥ ተደርጓል። ሰኞ 4:00 አካባቢ ዳግም በተማሪዎች መካከል አለመግባባት ይፈጠራል፤ ተማሪዎችም ይጋጫሉ። በወቅቱ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ችግሩን ለመፍታት ውይይት ሲያደርጉ ነበር።

ማክሰኞ፦

በተመሳሳይ ማክሰኞ ዕለት ሰፊ ውይይት ሲደረግ ይውላል። 10:00 ገደማ የደህንነት ስጋት አድሮብናል፤ የምንጠይቀው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም፤ ከፍተኛ ችግር አለ፤ ስርዓት አልበኝነት በግቢው ነግሷል ያሉ ተማሪዎች ሻንጣቸውን ይዘው ግቢውን ለመልቀቅ ይሞክራሉ። የሚመለከታቸው አካላትም ተማሪዎችን ለማግባባት ይሞክራሉ ግን አልተሳካም። ዩኒቨርሲው ተማሪዎቹ ውጭ ቢወጡ ሌላ ችግር ሊፈጠር ይችላል በሚል በግቢው ውስጥ ሬጅስትራር አካባቢ ፍራሽ አውጥቶ አሳድሯቸዎል።

ዛሬም ችግሩ እንዳልተፈታ ሰምቻለሁ!
ተጨማሪ መረጃ ሳገኝ ወደእናተ የማደርስ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል አንዳንድ ወረዳዎች የአተት በሽታ ተከስቷል ሲል በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር በየነ ሞገስ እንደገለፁት በአማራ ክልል አበርገሌ፣ ጠለምትና በየዳ ወረዳዎች 174 ሰዎች በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታ መጠቃታቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እየመጡ ነው። በሽታው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት ጥረት እየተደረገ ነው። በበሽታው እስካሁን የደረሰ የሞት አደጋ ስለመኖሩ አልተገለፀም ። በሀገሪቱ ያለው መፈናቀል የበሽታውን መዛመት ሊያባብሰው እንደሚችል ስጋት በመኖሩ ሁለት መቶ ያህል ባለሙያዎች ችግሩን ለማቃለል ተሰማርተዋል። ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በጀትም ተመድቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dubbii(Haasaa) jibbiinsaa irraa of haa qusannu!

#Yuunivarsiitii_Jimmaa
#Yuunivarsiitii_Amboo
#Yuunivarsiitii_Bulee_Horaa
#Yuunivarsiitii_Haramaayaa
.
.
.
Yeroo dhiyootti TIKVAH_ETH'n ni dhufna.
Waa'ee biyya teenyaa irratti waliin haa mari'annu!!!.

#NAGAA #JAALALA #TOKKUMMAA
👇
#BIYYA_TEENYAAF!!!.

Nuti dargaggoonni biyya teenya #ITIYOOPHIYAA jaalala, tokkummaa fi nagaan ni ijaarra!!!.

🚫 Dubbii (Haasaa) jibbiinsaa irraa of haa qusannu.
#Stop_Hate_Speech
#update የኢፊዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ለህፃናት የካንሰር ህክምና ጥራት ለሰጡት አመራርነትና ድጋፍ ከአስላን ፕሮጀክት ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ መሰረቱን አሜሪካ ያደረገው አስላን ፕሮጀክት በልጅነት ወቅት የሚከሰትን የካንሰር በሽታ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት እና ለህፃናት የካንሰር ህክምና ጥራት የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጋል፡፡ አልሳን ፕሮጀክት ከጥቁር አንበሳ፣ ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም ኮሌጅ ጋር በመሆን በካንሰር በሽታ የተጋለጡ ህፃናት ህይወትን ለማሻሻል እየሰራ ነው ተብሏል፡፡ ዶክተር አሚር አማን በአልሳን ፕሮጀክት ለተበረከተላቸው ሽልማት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በአሜሪካ የተበረከተውን ይህን ሽልማት አቶ ፍፁም አረጋ ተቀብለዋል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቅርብ ቀን አዲስ መጽሐፍ …

‹‹የጋዜጠኞች ወግ›› በሚል ለንባብ የሚበቃውን ይህን መጽሀፍ ለመፃፍ በመቻሌ ደስታዬ ወደር የለውም፡፡እነሆ በሀገራችን የጋዜጠኞች ወግና ገጠመኝ ጉዞ ውስጥ ታሪክ የሰሩ ጀግኖችን ሃውልት ላቆም ተነስቻለሁ፡፡ በርግጥም በህይወት ያሉ እንቁዎቻችንን የማድነቅ ባህላችንን ማሳደጉ ሳይጠቅመን አይቀርም፡፡

ለተተኪ ባለራዕዮች የነገ ሩቅ ጉዟቸውን መልካም ያደርግልናልና፡፡ ነገንም በእጅጉ እንድንናፍቅ ጭምር፡፡ ላወራችሁ የምሻው ተወልደው በመኖራቸው፣ ኖረውም ትርጉም ያለው ነገር በመስራታቸው፣ ትርጉሙም ከራሳቸው አልፎ ለአብዛኛው ህብረተሰብ ስላንጸባረቀው እንቁ ጋዜጠኞች ነው፡፡ እነዚህ እንቁዎች ከራስ በላይ ለሆነ ትርጉም መፈጠራቸውን ሲያስቡት በሚቀለው ሲሞክሩት ግን በሚከብደው ዓለም ላይ በተግባር አሳይተዋል፡፡

መፅሐፉም በሚገርሙና ለማመን በሚቸግሩ በሀገራችን የጋዜጠኞች ታሪክ ውስጥ ታሪክ ሰርተው ስላለፉ ጋዜጠኞች አስቂኝ፣አሳዛኝ እና አስገራሚ ገጠመኞች ከስቱዲዮ እስከ ጦርሜዳ ያለውን ድንቅና የተመረጡ ክንውኖችን ያካተተ ነው፡፡ ገጠመኞቻቸውን ለመዳሰስም የተሞከረላቸው ጋዜጠኞች ራሱን የቻለና የየራሳቸው የሆነ ድንቅ ታሪክ አላቸው፡፡

ታሪኮቹ እንዲሁ ስለመወለድና መኖር የሚተርኩ አይደሉም፡፡ በመወለድና መኖር ውስጥ ትርጉም ላለው ነገር መስዋእት እስከመክፈል ድረስ የሚዘልቅ ቁርጠኝነትን የምናስተውልበት ነው፡፡ የዓላማ ፅናት፣ ጥረት፣ ትግል፣ የሃገር ፍቅር፣ ለህዝብ ጥቅም መኖር፣ ትውልድ መቅረጽና ሌሎችም መገለጫ የሆኑ የመኖር እውነተኛ ተፈጥሮዎችን እናይባቸዋለን፡፡ ይለናል የመጽሐፉ ደራሲ Gizachew Ashagrie Getnet

ስለ ጽሐፊው (ጋዜጠኛ ግዛቸው አሻግሬ)
ጋዜጠኛ ግዛቸው አሻግሬ ላለፉት 7 ዓመታት በተለያዩ ቦታዎች የጋዜጠኝነትን ሙያ በብቃት ሲወጣ ቆይቷል፡፡ በኢቲቪ የወጣቶች ፕሮግራም የጋዜጠኝነቱን ህይወት ጅማሮ አድርጓል፡፡

በወጣቶች ፕሮግራም ላይ፣ በዋናነትም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመዟዟር በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ ተማሪዎችን አጠቃላይ የስኬት እና የህይወት ውጣ ውረድን ለህዝብ በማድረስ ሌሎችም እንዲማሩባቸው በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡

በዚህም የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶሎታል፡፡ በኋላ ላይም በኢቲቪ የእሁድ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ አቅራቢና አዘጋጅ በመሆን በመዝናኛው ዘርፍም የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

ላለፉት 3 ዓመታት ደግሞ በግሉ ዘርፍ እንቅስቃሴ በመጀመር በብስራት ኤፍ ኤም ሬድዮ ላይ “ማራኪ መዝናኛ” የተሰኘ ፕሮግራም በዋና አዘጋጅነት እየሰራ ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ

በድሬዳዋ በተለምዶ “መስቀለኛ” በተባለው አካባቢ ሰርግ ላይ የተፈጠረ ድንገተኛ #ግጭት አድማሱን አስፍቶ ለሦስት ቀናት በአካባቢው ውጥረት እንዲነግስ አድርጓል፡፡ በግጭቱ መንስዔነት የተለያዩ ምክንያቶች እየተነገሩ ሲሆን እስከትላንት ጠዋት ድረስ በአካባቢው የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ነው ተብሏል፡፡ በግጭቱ እስካሁን ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተነግሯል፤ ከገንደተስፋ ወደመስቀለኛ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ የቆየ ሲሆን ትላንት የአካባቢው ተማሪዎችም የ10ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና አለመፈተናቸው ታውቋል፡፡

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FaceBook

ፌስ ቡክ #ከጥላቻ_ንግግር ፖሊሲው ጋር የሚጣረሱ መልዕክቶችን በቀጥታ በሚያሠራጩ ተጠቃሚዎች ላይ አዲስ የቁጥጥር ህግ ሊያስተዋውቅ ነው። በኒውዚላንድ ክሪስት ቸርች መስጊዶች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ ተጠቃሚዎችን ከፌስቡክ ማገድ እንደ አንድ የመፍትሔ ሃሳብ ቀርቧል። በፓሪስ በሚካሄደውና በፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮንና በኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን በሚመራው ጉባዔ ላይም ፅንፈኛና ተንኳሽ የሆኑ ንግግሮችን ለመቀነስ የሚረዱ ሃሳቦች ይቀርቡበታል ተብሏል። በመስጊዶቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በስፋት ከተሠራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል በኋለ ፌስቡክ ትችት አጋጥሞታል። በኒውዚላንድ ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስኪዶች ላይ በተከፈተ ተኩስ 49 ሰዎች ሲገደሉ ብዙዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል በሙሉ፦

ከጥቁር አንበሳ የተላከ...

"ኧረ ስለእግዚአብሔር ስለደሀ አምላክ እባክህን ፀግሽ, ጥቁር አንበሳ የካንሰር ህክምና ክፍል ዶክተሮች አድማ አድርገዋል ተብለን የሚያየን አጥተን ቁጭ ብለናል። ይሄ ህክምና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰጠው ጥቁር አንበሳ ብቻ ነው። እናቴን ይዤ የት ልሂድ? እባክህን መንግስት ለኛ ሲል አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ አድርግልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከዚህ ቀደም የህክምና ባለሙያዎች ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ በአመት ገደብ እንዲያገለግሉ ወይም 470 ሺ ብር እንዲከፍሉ ይጠየቁበት የነበረው አሰራር #እንዲቀር ተወስኗል። የህክምና ባለሙያዎች ዩኒቨርስቲ በነበራቸው ቆይታ በፈረሙት የውል ስምምነት መሰረት ብቻ እንደማንኛውም የዩኒቨሪሲቲ ተማሪ ትምህርት እንደጨረሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሙያ ፍቃድና ሰርተፍኬታቸውን ወስደው በፈለጉበት ቦታ በመቀጠር መስራት ይችላሉ ተብሏል፡፡ የወጪ መጋራት ግዴታቸውንም በተመለከተ በወጪ መጋራት ህግ መሰረት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው በመጨረስ ኦርጅናል ሰርተፍኬታቸውን መውሰድ እንዲችሉ ተወስኗል ሲል የጤና ጥበቃ መረጃ ያመለክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በባሕር ዳር ማዕከል ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ። በባሕር ዳር ከተማ ከ2 ዓመታት በፊት ለድርጅቱ ግንባታ የሚውል 10 ሄክታር መሬት እንደተፈቀደ ማዕከሉ አስታውሷል፡፡ በቅርቡም ቦታውን በመረከብ ግንባታው እንደሚጀመር እና ግንባታው እስኪጠናቀቅ በተጓዳኝ ጊዜያዊ ማዕከል በማቋቋም በሦስት ወራት ውስጥ ለ300 ሰው አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ነው የማዕከሉ ክሊኒክ ኃላፊ እና የባሕር ዳር ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ማኅተመ በቃሉ የተናገሩት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
√የህክምና ባለሙያዎች ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ በአመት ገደብ እንዲያገለግሉ ወይም 470 ሺ ብር እንዲከፍሉ ይጠየቁበት የነበረው አሰራር #እንዲቀር ተወስኗል።

√የህክምና ባለሙያዎች ዩኒቨርስቲ በነበራቸው ቆይታ በፈረሙት የውል ስምምነት መሰረት ብቻ እንደማንኛውም የዩኒቨሪሲቲ ተማሪ ትምህርት እንደጨረሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሙያ ፍቃድና ሰርተፍኬታቸውን ወስደው በፈለጉበት ቦታ በመቀጠር መስራት ይችላሉ።

Via የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት በጌዴኦ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ የፕሮጀክት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጋራ በመተባበር የሚተገበረው ፕሮጀክቱ አርቲስትና አክቲቪት ታማኝ በየነ ከወርልድ ቪዝን ኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተፈራርመዋል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ በጌዴኦ ዞን በተፈጠረው ግጭት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬያቸው ለመመለስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ ለተፈናቃዮቹ መጠሊያዎች እና የአርሻ መሳሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን በጎንደር አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ሰዎች የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍም አድርጓል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህክምናና በትምህርት ዘርፍ ከባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት የተቋቋመው ግብረ ሀይል ወደ ስራ መግባቱን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም ተናገሩ። ሚኒስትሯ ከ30 የመንግስት የህክምና ትምህርት ከሚሰጡ ዩኒቨርስቲዎች ከተውጣጡ ተማሪዎች እና ሀኪሞች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት እያደረጉ ነው። የተቋቋመው ግብረሀይል በትምህርት ስልጠና ፣ በክፍያ ፣ በዲዩቲ፣ በሆስፒታሎች አስተዳደር እና አሰራር እንዲሁም በግብአት አቅርቦት ላይ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ምክረ ሀሳብ የሚያቀርብ ነው። ሚኒስትሯ የሚነሱ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለችግሮች መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ወደ ስራ ከገባው ግብረ ሀይል መካከል በጤናው ዘርፍ ያለውን የትምህርት ጥራ ችግር የሚገመግም ግብረ ሀይል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech #TIKVAH_ETH

√ግንቦት 10 እና 11 - በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ማዕከልነት /ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ/

√ግንቦት 17 እና 18 - በጅማ ዩኒቨርሲቲ ማዕከልነት/ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ/

√ግንቦት 24 እና 25 - በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ማዕከልነት/ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ አ.ሳ.ቴ.ዩ፣ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ/

በቀጣይ፦

√ዲላ ዩኒቨርሲቲ ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ ፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ፣ አርሲ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፣ ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ፣ አ.አ.ቴ.ዩ.፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ

√ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፣ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ...በዚህ መልኩ 45 ቱም ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ልዩ ልዩ መድረኮች ይኖሩናል።

የዝግጅቶቹ ይዘቶች፦

√የጥላቻ ንግግሮች ዙሪያ የእርስ በእርስ ውይይት
√የፅዳት ዘመቻ
√ደም ልገሳ
√የችግኝ ተከላ
√የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች
√በTIKVAH-ETH የሙዚቃ ባንድ እና የኪነጥበብ ቡድኖች ልዩ እና አስተማሪ የኪነጥበብ ዝግጅቶች

ይህን #ሀገር_አድን ዘመቻ የሚመለከታችሁ ሁሉ #እንድታግዙም እንማፀናለን። የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን አብረን እስራ! የጥላቻ ንግግር ሀገር ያሳጣናል።

ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ!!
0919 743630 /ለተጨማሪ መረጃ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia