TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጌዴኦ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አቶ ነጉሱ ጥላሁን #በጌዴኦ ላሉ ተፈናቃዮች የዕለት ምግብ ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት #ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መንግሥት የዕለት ደራሽ ምግብ ለሚያስፈልጋቸው #ድጋፍ ለማድረግ ከፌደራል እና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከዚህ ቀደምም ሲሰራ ቆይቷል፤ በዚህም እንዲቋቋሙ የተደረጉ እንዳሉም ገልጸዋል።

ነገር ግን አሁንም #የዕለት_ደራሽ_ምግብ ያልደረሳቸው ዜጎች እንዳሉ እና ችግር ላይ እንደወደቁ መንግሥት ተረድቶ የዕለት ምግብ ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶት ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ዜጎችን በማቋቋም፣ #የህግ_የበላይነትን በማረጋገጥ የሚደርሱ ማፈናቀሎችን ማስቆም መቻል ላይ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በግሎባል አልያንስ በኩል በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያኖች እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኖች #በጌዴኦ_ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ 754,707$ ወይም 21,131,796 ብር ድጋፍ አድርገዋል። በዚህ የድጋፍ ዘመቻ ላይ እስካሁን 10,799 ሰዎች ተሳትፈዋል። አጠቃላይ #ሊሰበሰብ የታቀደው 1 ሚሊዮን ዶላር ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተቻለኝን ለወገኔ!

#በጌዴኦ ማህበረሰብ ላይ በደረሰው ችግር የተጎዱ ወገቻችን #ለመርዳት በአርባሳት በፅዳት እቃዎች እና የተለቻልን አልባሳት እንዲሁም የተለያዩ አፈላጊ ቁሳቁስ እናግዝ።

አድራሻ፦ ቦሌ ሞርኒንግ ስታር ሞል
Morning⭐️Star Mall

@tsegabwolde @tikvahethiopia