TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ: #የStopHateSpeech እንቅስቃሴ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ #ፕሬዘዳንቱ ዶክተር #ታከለ_ታደሰ በተገኙበት የመጨረሻው መድረክ ተካሂዷል።

ፎቶ፦ @odansiif
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባምንጭ ዝግጁ

የኢትዮጵያ ልጆች #የምንሰባሰብበት #የStopHateSpeech መድረክ ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ምሽት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ...

#TIKVAH_ETH ቤተሰብ አባላት በዝግጅቱ ላይ ተካፋይ ይሆናሉ!! #ethiopia

ሀገራችን #እንዳትፈርስ ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ! ጥላቻ ሀገር ያፈርሳል!!

🇪🇹ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ🇪🇹

ስልክ፦ 0919 74 36 30

አዘጋጅ፦

•TIKVAH-ETH
•የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
•የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ፎረም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ተስፋዎች🔝

#የTikvah_Ethiopia ሴት አባላት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሊሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ አጭር ገለፃ ተደርጎላቸዋል:: ለበርካታ ወጣት #ሴቶች አርአያ ለመሆን እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በቀጣይ ሊሰሯቸው ባሰቧቸው ስራዎች ዙሪያም በመጪው ሳምንት #ምክክር ያደርጋሉ:: በዛሬው ውይይት ላይ የተካፈሉት #አብዛኞቹ #የStopHateSpeech አስተባባሪዎች ናቸው::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ!
#StopHateSpeech
(ሚያዚያ 5 እና 6)

የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ #የStopHateSpeech መድረክ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጅታል:: ሁላችሁም የTikvah-Ethiopia ቤተሰብ አባላት እና መላው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት በዚህ ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ ላይ እንድትገኙልን በአክብሮት ጋብዘናችኃል::

#ከሁለት ዩኒቨርሲቲዎች(WSU እና AMU) የተውጣጡ 55 የTikvah-Ethiopia ቤተሰብ አባላት የፊታችን ቅዳሜ #ወልቂጤ ይገባሉ::

የጥላቻ ንግግር ሀገር ያፈርሳል!!
ሰው ሁሉ ክቡር ነው!!
ሀገራችን አለንልሽ!!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጁ - ሚያዚያ 12 እና 13
#StopHateSpeech

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech-ኩልፎ ካምፓስ👆

#በኩልፎ_ካምፓስ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። የStopHateSpeech አስተባባሪዎችን #ቴዎድሮስ_ዮሴፍ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ተቀብለዋል። በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር #ይስሀቅ_ከቸሮ የኮሌጅ ዲን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የተቋማቸው ተማሪዎች የሀገሪቱን #አንድነት ከሚሸረሽሩ ግለሰቦች ጋር #መታገል እንዳለባቸዉ እና በቀጣይም የሀገሪቱ እጣ ፈንታ #በወጣቶች ላይ መሆኑን አውቀው የሚዲያ አጠቃቀማቸውን እንዲያስተላካክሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ማስታወሻ🗓በነገው ዕለት #ተመሳሳይ መድረክ #በአባያ_ካምፓስ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል!! #አርባምንጭ_ዩንቨርስቲ

የአርባምንጭ ተማሪዎች ተቀላቀሉ👇 @tikvahethamu @tikvahethamu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech-----አባያ ካምፓስ👆

#በአባያ_ካምፓስ----አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 2ኛው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ #ዝግጅት በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ገብተዋል!

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ወደተቋማቸው በሰላም ገብተዋል። በተመሳሳይ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ወደተቋማቸው በሰላም ገብተዋል። የወልቂጤው ልዕኩ በጉዞ ላይ ይገኛል።

ቅዳሜ እና እሁድ #በሀዋሳ_ዩኒቨርስቲ #የStopHateSpeech መድረክ መካሄዱ አይዘነጋም--ፎቶዎች እና ተያያዥ መረጃዎችን ቆየት ብዬ አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ገብተዋል!!

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ወደተቋማቸው በሰላም ገብተዋል። የሰላም እና የፍቅር አምባሳደሮቹ ረጅም እና አድካሚ ጉዞ አድርገው በሀዋሳ ዩንቨርስቲ በተዘጋጀው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አስተባብረው እና ዝግጅቱን አዘጋጅተው ወደወልቂጤ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩንቨርስቲ🔝የሰላም ተምሳሌት እና የሰላም አምባሳደር በሆነው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቅዳሜው ምሽት #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በስኬት ተጠናቋል። በመድረኩ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሰላም ፎረም እና የተማሪዎች ህብረት ለእንግዶቻቸው እንኳን ደህና መጣቹ በኃላ ወጣት ተማሪዎች ራሳቸውን #ከጥላቻ_ንግግሮች እንዲቆጥቡ ለሀገሪቱ ተስፋ መሆናቸውን አውቀው ለሰላም ቅድሚያ እንዲሠጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በዕለቱ ተማሪ #ሀና_ሀይሉ "Love Speech Vs Hate Speech" በሚል ልዩ ገልፃ አድርጋለች። የጥላቻን አስከፊነት የተተነተነበት፤ የፍቅርን ሀያልነት የተገለፀበት ነበር ገለፃው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ~~እናመሰግናለን!!

በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ለጠየቅነው የትራንስፖርት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት #እየተረባረባችሁ ለምትገኙ የተቋሙ አመራሮች እና የተማሪ ተወካዮች በመላው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ ስም ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን። ሀሳባችን ከግብ እንዲደረስ ለማድረግ ሁሌም ከጎናችን እንደምትሆኑ እናምናለን። #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀጣይ መድረክ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ነው በዚህም ዝግጅት ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ20 በላይ ተማሪዎቹን ለዚህ ሀገር አድን ዘመቻ ይልካል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ👆

/ሚያዚያ 23/

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ረቡዕ ምሽት #የTIKVAH_ETH ቤተሰብ አባላት ሲገቡ በተቋሙ ተማሪዎች እና በተማሪዎች ህብረት ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በፍቅር ተቀብለው አስተናግደዋቸዋል!! እራታቸውን እጉርሰው ማደሪያቸውን አመቻችተው ወንድምና እህቶቻቸውን በክብር አስተናግደዋቸዋል።

√ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር ቀደም ብለን በተነጋገርነው መሰረት #የStopHateSpeech መድረክን ያካተተ ሌላ ትልቅ መድረክ እያዘጋጁ ስለነበር የውይይት መድረኮች ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ ሆኗል። ዩኒቨርሲቲውም በራሱ ፕሮግራም በትልቅ ዝግጅት ሊጠራ ስላሰበ የታቀዱ ስራዎች ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።

እውነት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይለያሉ! #ፍቅርን#መተሳሰብን#አንድነትን ያሳዩን የቤተሰባችን አካል ናቸው። #ክብር ይገባችኃል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመላው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፦

#የStopHateSpeech መድረክ በLTH 7 ዛሬ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ይካሄዳል። ተማሪዎች ከመቐለ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ፣ ወልቂጤ፣ ቤተሰቦቻችን ጋር ተገናኝተን እንወያያለን።

ከ9:00 ጀምሮ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር #ጀማል_አባፊጣ👆

#የStopHateSpeech የሁለት ቀን መድረክ በይፋ ተጀምሯል። በመጀመሪያው ቀን መድረክ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ተገኝተዋል። "ጅማ የመቻቻል የፍቅር የአንድነት ተምሳሌት ናት። የጅማ ሰው ሲመርቅ ቡናና ሰላም ከቤትህ አይጥፋ ይላል። ጥላቻ #ቆሻሻ ነው እራሳችንን ከዝህ ተግባር እንቆጥብ" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በከሰዓቱ መርሃግርብር በወጣት ተማሪዎች መካከል ስለጥላቻ ንግግር ውይይቶች ይደረጋሉ።

Via #Bereket
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH-ETH #የStopHateSpeech ሀገር አቀፍ ዘመቻዎች/በዩኒቨርሲቲ ደረጃ/ና በየተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ የተደረጉ ጉብኝቶችን ለመከታተል #የዩትዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ!

#ሀረማያ #ጅማ #ወልቂጤ #ሀዋሳ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #መቐለ #ዋቻሞ #ወሎ #ደብረብርሃን #ወልዲያ

Watch ""የአንድ እናት ልጆች ነን" በመቐለ ዩኒቨርሲቲ #TIKVAH_ETHIOPIA" on YouTube
https://youtu.be/qjyt56okb3U