TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመከላከያ ልዩ ኃይል አባል ዕድለኛ ሆነ!

መቶ አለቃ #አብዮት_ተክሉ በብላቴ ማሰልጠኛ የመከላኪያ ልዩ ኃይል አባል ነው፡፡ መ/አለቃ አብዮት ለስራ ወደ መተሀራ በተንቀሳቀሰ ጊዜ በገዛው የገና ስጦታ ሎተሪ ግማሽ ቲኬት የ1,666,666 ብር ባለዕድለኛ ሆኗል፡፡ መ/አለቃ አብዮት በደረሰው ብር ቤት ለመስራትና መቆዶኒያ ለሚገኙ አረጋውያን #ዕርዳታ_ለመስጠት እንዳሰበ ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን #ቡራዩ_ከተማ አስተዳደር መልካ ገፈርሳ ቀበሌ ዛሬ በአንድ መዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ መጸዳጃ ቤት ተደርምሶ የ4 ሕጻናት ሕይወት አልፏል።

በአደጋው ስምንት ሕጻናት ወደ መጸዳጃ ቤቱ #ጉድጓድ ገብተው እንደነበር የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ከእነዚህ ውስጥም የአራቱ ሕይወት #ወዲያውኑ ማለፉን አመልክቷል።

ቀሪዎቹ አራት ሕጻናት ደግሞ በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በቤተልና አለርት ሆስፒታሎች የሕክምና #ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የከተማዋ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በየኑ ረዳ ተናግረዋል።

በአደጋው ሕይወታቸው ላለፉት ሕጻናት ጥልቅ ሐዘን የተሰማቸው መሆኑን በከተማ አስተዳድሩ ስም የገለጹት ወይዘሮ #በየኑ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። ትምህርት ቤቶች በግቢያቸው ውስጥ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች ለተማሪዎች ደኅንነት ምቹ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ምክትል ሳጅን #ሲሳይ_ዓለሙ በበኩላቸው መጸዳጃ ቤቱ የተደረመሰው በነበረበት የጥራት ችግር መሆኑን ተናግረዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia