TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ #በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ #አዲሱ_አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው እንዳሰፈሩት፥ ፖሊስን ጨምሮ በአካባቢው የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አቶ አዲሱ አያይዘውም የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ በለገጣፎ ቤት የማፍረሱ እንቅስቃሴ እንዲቆም አዘዋል። ከነዋሪዎቹ ጋርም ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል።" (በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ)
.
.
አቶ #አዲሱ_አረጋ፦ "እኔ ከአቶ #ለማ እንዲህ አይነት ትእዛዝ እንደተላለፈ #አላውቅም። የህግ ማስከበሩ ተግባር #እንደቀጠለ ግን አውቃለሁ።"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(አቶ አዲሱ አረጋን በስልክ ጠይቆ የተሰጠው ምላሽ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሽመልስና አቶ አዲሱ🛫ደንቢዶሎ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ እና የኦሮሞ ዴክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ #አዲሱ_አረጋ ከደንቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ዛሬ ወደ #ደንቢዶሎ አቅንተዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ
.
.
ትናንት ህይወቱ ያለፈው የነቀምት ከነማ ተጫዋች ወንድወሰን ዮሐንስ አሟሟት አጠያያቂ ሆኗል። የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ #አዲሱ_አረጋ ትናንት ምሸት በነቀምት ከተማ በአንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦንብ አንድ ሰው ተገደለ ቢሉም ሟቹን በቅርብ የሚያውቁ እና የሆስፒታል ምንጮች ደግሞ ወጣቱ የተገደለው ጥይት ተመትቶ ነው ይላሉ።

አቶ አዲሱ አረጋ ትናንት ከምሽቱ 1 ሰዓት አከባቢ ነቀምት ከተማ 'ፋክት' በሚባል ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦምብ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውን እና አንድ ሰው መገደሉን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፈረዋል።

አቶ አዲሱ የሟቹንም ሆነ በቦንብ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር አልጠቀሱም።

አቶ ቾምቤ ገ/ህይወት የነቀመት ከነማ አሰልጣኝ ሲሆኑ፤ ትናንት የተገደለው ወጣት የቡድናቸው ተጫዋች መሆኑን አረጋግጠዋል።

አቶ ቼምቤ እንደሚሉት ሟች ወንድወሰን ዮሐንስ ህይወቱ ያለፈው በቦንብ ፍንዳታ ሳይሆን ከፈንዳታው በኋላ በተተኮሰበት ጥይት መሆኑን ያስረዳሉ።

''እራት ለመብላት አምስት ሆነን ወጣን። እነሱ የፈረንጅ ምግብ መብላት ፈልገው 'ፋርም ላንድ' ወደሚባል ሆቴል ገቡ። እኔ ደግሞ እነሱ ካሉበት ጎን ወደሚገኘው 'ፋክት' ሄቴል ገባሁ። ቦምቡ የፈነዳው እኔ የነበርኩበት ሆቴል ውስጥ ነው'' የሚሉት አቶ ቾምቤ፤ በፍንዳታው ጉዳት ባይደርስባቸውም፤ ከተፈጠረው ግርግር ለማምለጥ ሲሞክሩ የመፈነካከት ጉዳት እንደደረሰባቸው ያስረዳሉ።

''ቦምቡ ከፈነዳ በኋላ እነ ወንደሰን ደውለው ደህን መሆኔን ጠየቀውኝ ነበር'' የሚሉት አቶ ቾምቤ፤ ተጫዋቾቹ በፍጥነት ከሚገኙበት ሆቴል ወደ መኖሪያ ቦታቸው እንዲሄዱ እንደነገሯቸው አቶ ቾምቤ ያስታውሳሉ።

''ህክምና ለማግኘት ወደ የግል ክሊኒክ ሄጄ ነበር። እዛ እያለሁ አንድ የጸጥታ ኃይል አስከባሪ የሆነ ሰው ስልክ ደውሎ ወንድሰን በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል እንደሚገኝ ነገረኝ'' በማለት ትናንት የነበረውን ሁኔታ ያስረዳሉ። አቶ ቾምቤ ሆስፒታል ሲደርሱ ተጨዋቹ ህይወቱ አልፎ ነበር።

በነቀምት ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ዳምጠው ጋረደው ተጨዋቹ በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉን ያረጋግጣሉ። ''በስተቀኝ በኩል ከብብቱ ስር የተመታ ሲሆን ጥይቱ በግራ በኩል ወጥቷል'' ያሉት ዶ/ር ዳምጠው፤ ወንድወሰን ወደ ሆስፒታል የመጣው ከምሸቱ ሁለት ሰዓት አከባቢ እንደሆነ እና ሆስፒታል ሲደርስም ህይወቱ አልፎ እንደነበረ ይናገራሉ።

ወንድወሰን ለምን እና ማን በተኮስው ጥይት እንደተገደለ የታወቀ ነገር የለም። 'ፋክት' በሚሰኘው ሆቴል ላይም ማን እና ለምን የቦምብ ጥቃት እንደሰነዘረ ባይገለጽም፤ አቶ አዲሱ ትናንት በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ቦምቡን የወረወሩ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መደረጋቸውን ገልጸዋል።

'ፋክት' ሆቴል በነቀምት ከተማ በርካታ ተጠቃሚ ካላቸው ታዋቂ ምግብ ቤቶች መካከል አንዱ ነው። በተጨማሪም የምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት፣ ፍርድ ቤት እና የዞኑ አስተዳደር ቢሮዎች 'ፋክት ሆቴል' በሚገኝበት አቅራቢያ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia