TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከወር በፊት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር #ለተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ተጓዥ ለነበሩ እና ሕይወታቸው ላለፉ ሰዎች የ40 ቀን ማስታወሻ በጋራ ተከናወነ። የዝክር ስነ-ሥርዓቱ፦የሟቾች ቤተሰቦች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት፣ የቢሾፍቱ ወጣቶች እና የቱሉ ፈርዳ ወረዳ የሃማ ቁንጡሽሌ ቀበሌ ነዋሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የእምነት አባቶች በተገኙበት ጧፍ በማብራት እና በጸሎት ተከናውኗል። አደጋው በደረሰበት የሃማ ቁንጥሽሌ አከባቢ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መታሠቢያ እንዲሠራ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል። በዕለቱም 2500 የሚሆኑ #የቢሾፍቱ ወጣቶች በአደጋው ስፍራ #ደም ለግሰዋል።

Via DW
ፎቶ፦ TIKVAH-ETHIOPIA(DakStar)

@tsegabwolde @tikvahethiopia