TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር መግለጫ፦
.
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የህክምና ባለሙያዎች እንደማንኛውም ግለሰብና ባለሙያ ጥያቄዎቻቸውን #በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የማቅረብ መብት እንዳላቸው በጽኑ ያምናል፡፡
.
ይሁንና በዛሬው እለት #በአርሲ_ዩኒቨርስቲ ያላቸውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለዩኒቨርስቲው አመራሮች ለማቅረብ የህክምና ጋወናቸውን አድርገው በመጓዝ ላይ በነበሩ ወንድና ሴት ኢንተርን ሀኪሞች ላይ የተፈጸመው ጥቃት በእጅጉ እንዳስደነገጠውና እንዳሳዘነው ማህበሩ መግለጽ ይወዳል፡፡ ይህ ጥቃት የተፈፀመው ደግሞ ህግና ስርዓትን እንዲያስከብሩ እምነትና ኃላፊነት በተሰጣቸው የህግ አስከባሪዎች መሆኑ ደግሞ ሁኔታውን እጅግ አስደንጋጭና አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲውና በኦሮሚያ የፀጥታ አካላት እጅ በንፁሐን ሀኪሞች ላይ የተፈጸመውን ይህንን አሳፋሪ ድርጊት ለማጣራት ማህበራችን ለዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም፡፡
.
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በሀኪሞች ላይ የሚፈጸም ማንኛውንም ጥቃት በጥብቅ ያወግዛል፤ በህክምና ባለሙዎች ላይ በጸጥታ አካላትም ይሁን በማንኛውም አካል በኩል የሚፈጸም ጥቃትንም በጽኑ ያወግዛል!!! በአፋጣኝ እንዲቆምም ይጠይቃል፡፡ ይህ በህክምና ባለሙያዎች ላይ የሚደርሰው የሠብዓዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ እንዲቆም ይጠይቃል!!!
.
በዚህ አጋጣሚም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ቢሮ፣ የዩኒቨርሲቲው፣ የጤና ጥበቃና የትምህርት ሚኒስቴር አካላትም ጉዳዩን አጣርተው አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠውም ጥያቄውን ያቀርባል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia