TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለተጎዱ የጌዲኦ ወገኖቻችን የጤና ድጋፍ ለመስጠት ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ-አቤት የተላከው የሕክምና ቡድን የሶስት ሣምንት አገልግሎቱን #አጠናቆ ተመልሷል።

Via @SPMMC (ይህን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የቴሌግራን ገፅ በመቀላቀል ተጨመሪ መረጃዎችን ያግኙ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር መግለጫ፦
.
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የህክምና ባለሙያዎች እንደማንኛውም ግለሰብና ባለሙያ ጥያቄዎቻቸውን #በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የማቅረብ መብት እንዳላቸው በጽኑ ያምናል፡፡
.
ይሁንና በዛሬው እለት #በአርሲ_ዩኒቨርስቲ ያላቸውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለዩኒቨርስቲው አመራሮች ለማቅረብ የህክምና ጋወናቸውን አድርገው በመጓዝ ላይ በነበሩ ወንድና ሴት ኢንተርን ሀኪሞች ላይ የተፈጸመው ጥቃት በእጅጉ እንዳስደነገጠውና እንዳሳዘነው ማህበሩ መግለጽ ይወዳል፡፡ ይህ ጥቃት የተፈፀመው ደግሞ ህግና ስርዓትን እንዲያስከብሩ እምነትና ኃላፊነት በተሰጣቸው የህግ አስከባሪዎች መሆኑ ደግሞ ሁኔታውን እጅግ አስደንጋጭና አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲውና በኦሮሚያ የፀጥታ አካላት እጅ በንፁሐን ሀኪሞች ላይ የተፈጸመውን ይህንን አሳፋሪ ድርጊት ለማጣራት ማህበራችን ለዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም፡፡
.
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በሀኪሞች ላይ የሚፈጸም ማንኛውንም ጥቃት በጥብቅ ያወግዛል፤ በህክምና ባለሙዎች ላይ በጸጥታ አካላትም ይሁን በማንኛውም አካል በኩል የሚፈጸም ጥቃትንም በጽኑ ያወግዛል!!! በአፋጣኝ እንዲቆምም ይጠይቃል፡፡ ይህ በህክምና ባለሙያዎች ላይ የሚደርሰው የሠብዓዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ እንዲቆም ይጠይቃል!!!
.
በዚህ አጋጣሚም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ቢሮ፣ የዩኒቨርሲቲው፣ የጤና ጥበቃና የትምህርት ሚኒስቴር አካላትም ጉዳዩን አጣርተው አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠውም ጥያቄውን ያቀርባል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech-ኩልፎ ካምፓስ👆

#በኩልፎ_ካምፓስ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። የStopHateSpeech አስተባባሪዎችን #ቴዎድሮስ_ዮሴፍ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ተቀብለዋል። በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር #ይስሀቅ_ከቸሮ የኮሌጅ ዲን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የተቋማቸው ተማሪዎች የሀገሪቱን #አንድነት ከሚሸረሽሩ ግለሰቦች ጋር #መታገል እንዳለባቸዉ እና በቀጣይም የሀገሪቱ እጣ ፈንታ #በወጣቶች ላይ መሆኑን አውቀው የሚዲያ አጠቃቀማቸውን እንዲያስተላካክሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ማስታወሻ🗓በነገው ዕለት #ተመሳሳይ መድረክ #በአባያ_ካምፓስ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል!! #አርባምንጭ_ዩንቨርስቲ

የአርባምንጭ ተማሪዎች ተቀላቀሉ👇 @tikvahethamu @tikvahethamu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ #ጥላቻ

ጥላቻ ክፉ ደዌ ነው። የአስተሳሰብ ሚዛንህን ያዛባዋል። ሁሌም ግራና ቀኙን ከማየት ይልቅ በአንድ አቅጣጫ እንድትተም ያስገድድሃል። ጥላቻ የምክንያታዊነት ባላንጣ የስሜታዊነት ደግሞ የቅርብ አጋር ነው። ትናንት ሸጋ ያልከውን ዛሬ አፈር ከድሜ እንድታስገባው፤ ዛሬ ቀሽም ያልከውን ደግሞ ነገ ከነገ ወዲያ እንድታሞካሸው ያደርግሃል። ነጩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ደግሞ ነጭ አድርጎ ያሳይሃል። ይህን ክፉ አባዜ በግዜ ወግድ ካላልከው ቤቱን እላይህ ላይ ሰርቶ ተደላድሎ ይኖራል። ጥላቻን ፊት ከሰጠከው የልብ ልብ ተሰምቶት እላይህ ላይ ወጥቶ ይጋልብብሃል። እንደ ኮሶ ተጣብቶህ እድሜ ልክህን የእኩይ ተግባሩ ተጋሪ ያደርግሃል።

“ሳይኮሎጂ ቱዴይ” ስለ ጥላቻ በአንድ መጣጥፉ ከጠቀሰው ጥቂት በመቀንጨብ ይህችን አጭር ሃሳቤን ልቋጭ፦

“Hate masks personal insecurities. Not all insecure people are haters, but all haters are insecure people…Haters cannot stop hating without exposing their personal insecurities. Haters can only stop hating when they face their insecurities.”

የሃሳብ ብዝሃነት፣ የሰለጠነ፣ ከጥላቻና ከመዘላለፍ የፀዳ ውይይት ለዘላለም ይኑር!!!

Via Sileshi Yilma Reta(SYR)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ባቲ ወረዳና በአፋር ክልል ሶስት ወረዳዎች መካከል ተነስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቀረት የተካሄደው የዕርቅና የሰላም ኮንፈረንስ የእርቅ ስምምነት በአፋር ክልል ለማድረግ በመስማማት ተጠናቀቀ። በኮንፈረንሱ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶ፣ የአገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ወረዳ ነዋሪዎች በተገኙበት በባቲ ወረዳ ተካሄዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መንግሥት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የተፈናቃይ አስመላሽና የመልሶ ማቋቋም ግብረ ኃይል፣ የጌዴኦ ዞን አመራሮችና የተፈናቃይ ተወካዮች በምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቃዮችንለመመለስ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ተመልክል። የግብረ ኃይሉ አስተባባሪ አቶ ሚጣ ሚቻ  እንዳስረዱት መንግሥት ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ለመመለስ አንድ ወር  ጊዜ መርሐ ግብር አውጥቶ እየሰራ ነው፡፡ በዚህም በቀጣይ ቀናት ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው መመለስ እንደሚጀመርም ተናግረዋል፡፡ መርሐ ግብሩን ለማስጀመር በምዕራብ ጉጂ ዞን ከቀርጫና ከብርብርሳ ኮጆ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ውይይት መደረጉንና ወረዳዎቹ የጸጥታ ችግር እንደሌለባቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የመልሶ ማቋቋምና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር  ትኩረት እንደሚሰጥ አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ለጊዜያዊ መጠለያዎች መስሪያ የሚያስፈልግ ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ሥፍራዎቹ  እንደሚልክም ገልጸዋል፡፡ የምዕራብ ጉጂ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አቶ አዱላ ህርባዬ በበኩላቸው  ተፈናቃዮችን ለመቀበል ከሕዝቡ ጋር  መወያየቱን አስታውቀዋል። ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሲመለሱ በጊዜያዊነት የሚጠለሉባቸው ሥፍራዎች ዝግጅት ኅብረተሰቡን በማስተባበር በመከናወን ላይ እንደሚገኝን አመልክተዋል፡፡ በዞኑ ምንም አይነት የጸጥታ ስጋት ሳይኖር ዜጎች በአሉባልታ ተደናግጠው መሰደዳቸውን የገለጹት ምክትል አስተዳዳሪው፣ ኅብረተሰቡ አንድነቱን በማስጠበቅ ችግር ፈጣሪዎችን እንዲታገላቸውን ጠይቀዋል፡፡ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ መኮንን ጭጩ በበኩላቸው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አሁን ካሉበት አሳሳቢ ሁኔታ ለማውጣት የሚደርስባቸውን ጫና እንደሚቀንስላቸው አመልክተዋ።
ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋምና የደህንነት ስጋትን ለመቀነስ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዴ.ሪ #ህዝብ_ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ #ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት የተለያዩ ሚኒስትሮችን ሹመት እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቁጥጥር ስር ውለዋል...

የፌደራል ፖሊስ የግዢ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባን ጨምሮ ሌሎች የግዢ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ከስንዴ ጨረታ ጋር በተያያዘ ከ44 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል በከባድ የሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ይፋ አደረገ፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ዐኛ የወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው የእነዚህን ጨምሮ የ24 ተጣርጣሪዎችን ጉዳይ መርምሯል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ #ገዱ_አዳርጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በመሆን በእጩነት ቀረቡ። #ebc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ለመከላከያ ሚንስትርነት በእጩነት ቀረቡ። #ebc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር አይሻ መሀመድ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስትር በመሆን በእጩነት ቀረቡ። #ebc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ጫላ ለሚ ተሿሚ ሚኒስትሮችን ሹመት የውሳኔ ሀሳብን እየቀረቡ ነው።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ለማ መገርሳ ዋቆ፦ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር

2. አቶ ገዱ አንድአርጋቸው፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

3. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፦ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ልማት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሹመቱ ፀደቀ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የተለያዩ #ሚኒስትሮችን ሹመት አጸደቀ።

በዚህም መሰረት፦

•አቶ ለማ መገርሳ ዋቃ፦ ሀገር መከላከያ ሚኒስትር

•አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

•አይሻ መሀመድ፦የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethiopia