TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኮየ ፈጬ ሳይት የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራውና የከተማ አስተደሩ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልኡካን በ11ኛው ዙር የተላለፉ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል።

ነዋሪዎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ባለሟላቱ ቅሬታቸውን ገልጸውላቸዋል በተለይም #የውሃ#የመብራት አለሟሟላት እና በቅንጅት ተናበው አለመስራት በኑሮአቸው ላይ ተጽእኖ እንደፈጠረ ነው የገለጹት።

ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች የህብረተሰቡን ቅሬታ ወስደው #በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲያስቀምጡ አሳስበዋል።

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው"
.
.
የመርሃቢቴ ወረዳ ወጣቶች በአስተዳድሩ ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው አሉ። በመርሃቢቴ ወረዳ #የመብራት_ትራንስፎርመር ተነቅሎ እንዳይወሰድ አድርጋችኋል ተብለን ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው ሲሉ የአካባቢው ወጣቶች ተናገሩ፡፡

የወረዳው አስተዳድር በበኩሉ በፊት ከነበረው የተሻለ ትራንስፎርመር ለማስተከል እንቅስቃሴ ሲደረግ ሁከት የፈጠሩትን በህግ የመጠየቅ እንጂ ማስፈራሪያ አለማድረሱን ተናግሯል፡፡

የመርሃቢቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተሾመ አስፋው፤ በአማራ ክልል ትራንስፎርመር የማሳደግ ስራ እየተሰራ በመሆኑ በወረዳው የነበረው 200 ኪሎ ዋት ትራንስፎርመር አቅም ስለበዛበት ለመቀየር 315 ኪሎ ዋት ሊቀየር ሲል ብጥብጥ መነሳቱን ገልፀዋል፡፡

በዚህ ምንም አይነት ትራንስፎርመር ከአካባቢው እንዳይወጣ መደረጉን ይገልፃሉ፡፡

በአሁን ወቅት አመራሩን ከህዝቡ የመነጠል ስራ እየተከናወነ መሆኑን በመጥቀስ፤ የከተማ መዘጋጃ ቤት ትራስፎርመር ሊሰርቁ ነው በሚል ማህበራዊ ሚድያው ላይ የሚሰራጨው ወሬ ስብዕናን የሚነካ ጉዳይ በመሆኑ በህግ እንደሚታይ አመልክተዋል፡፡

እንደ አቶ ተሾመ ገለፃ ሌባ እያሉ በማህበራዊ ሚድያ የሚያሰራጩትን በህግ የመጠየቅ ስራ እንጂ ፖሊስ እያስፈራራ አደለም፤ በወረዳው ማንኛውንም ጥያቄ በሰላም እንጂ በሁከትና በብጥብጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

መምህር እንዳሻው ጌትዬ እንደሚናገረው፤ ትራንስፈርመር ሊወስዱ ሲሉ በወጣቱ ሃይል እንዲመለስ ተደርጓል፤ እንዲመለስ ጥረት ያደረጉትን ወጣቶች ፖሊስ ጣቢያ እየተጠሩ ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው፡፡

ነባሩ ትራንስፎርመር በቦታው ላይ የሚገኝ ሲሆን አዲሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ ይዘውት የመጡት አዲስ የተባለው የተበላሸ ሲሆን ከየት እንደመጣ አይታወቅም፡፡

በማይመለከታችሁ ነገር ውስጥ እየገባችሁ ነው እርምጃ ይወሰድባችኋል በማለት ኢንስፔክተር አያሌው ደበበ የሚባል የፖሊስ አዛዥ ወጣቶቹን ቢሮ በመጥራት እያስፈራራ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ ወጣቶቹ እንዳይታሰሩ በተደረገ ጥረት እስካሁን የታሰረ ወጣት እንደሌለም ጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጀሞ ነዋሪዎች...

#የመብራት_ታሪፍ በጣም በመጨመሩ ምክንያት ሕብረተሰቡ እጅግ በጣም መማረሩን በጀሞ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቆሙ። ጥቆማውን ያደረሱት የጀሞ ነዋሪዎች እንዳሉት "ካርድ ለመሙላት አብዛኞቹ አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆኑ እንዲሁም መብራት ኃይል ለማስተካከል ስራዎችን እየሰራ ባለመሆኑ እጅግ በጣም ተቸግረናል ብለዋል። የሚመለከተው አካልም ችግሩን እንዲመለከተው እና ችግሩን እንዲፈታ አጥብቀው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ የአገሪቱን የኢነርጂ ሚኒስትር በአገሪቱ የተባባሰውን #የመብራት_መጥፋት ችግር ተከትሎ ከኃላፊነት ማንሳታቸው ተነግሯል። ከሀላፊነታቸው የተነሱት የዚምባብዌ የኢነርጂል ሚኒስትር ጆራም ጉምቦ በትራንስፖርትና መሰረተ-ልማት ምክትል ሚኒስትር ፎርቹን ቻዚ ተተክተዋል፡፡ የቀድሞው የዚምባብዌ ኢነርጂ ሚኒስትር ከኃላፊነታቸው የተነሱት ከ2016 ወዲህ ባልታየ ሁኔታ በየዕለቱ እና በመላ አገሪቱ መብራት ጠፍቶ ለሰዓታት እንደሚቆይ ተቋማቸው ማስታወቁን ተከትሎ ነው፡፡ መንግስታዊው የአገልግሎት ሰጪ ተቋም ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ በየዕለቱ ከ5 እስከ 8 ለሚደርሱ ሰዓታት በመላ አገሪቱ መብራት እንደማይኖር አስታውቆ ነበር፡፡ ተቋሙ ይህን ያለው የአገሪቱ ትልቁ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ እና በድንጋይ #ከሰል የሚሰሩት አሮጌ ጄነሬተሮች የሚያመርቱት የኃይል መጠን መቀነሱን በመንስኤነት ጠቅሶ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba #የተማሪዎችምገባ

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፤ የውሃና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚከናወነው የምገባ ሥርዓት ፈተና መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው የነበረው በአ/አ ት/ት ቢሮ የተማሪዎች ምገባ ባለሙያ አቶ አለሙ ሀይሉ ፥ የምገባ ሥርዓቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ትልቁ አጋዥ ነገር እንደሆነ አስረድተዋል።

የሥርዓቱ በት/ቤቶች መኖር ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ነገር ግን በዚህ ሂደት አንዳንድ ተግዳሮቶች እንዳሉ አንስተዋል።

ምንም እንኳን ካሁን በፊት ከነበረው አንፃር ሲታይ በርካታ ለውጦች ቢኖሩም  #የውሃ_አቅርቦት ችግር ተግዳሮት መሆኑን  አመልክተዋል።

በተለይ ምገባ ላይ ብዙ ውሃ እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ አለሙ ፤ " 5 የምገባ ቀናቶች አሉ (ከሰኞ እስከ ዓርብ) በእነዚህ ቀናት መካከል የውሃ አቅርቦቱ እንደተፈለገ የማይሆንበት ጊዜ አለ " ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍም አማራጮች እየተወሰዱ መሆኑና ተጨማሪ የውሃ ታንከር ጥቅም ላይ እንደሚውል አስረድተዋል።

አንዳንድ ት/ቤቶችን በተባለው ቀንም አድሬስ ከማድረግ አኳያ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው " ከዚያ አኳያ ውሃ ነው መታገዝ ያለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

ሌላው በመንግሥት እንዲሁም በዓለም ባንክ የተሰሩ የምገባ አዳራሾች የመብራት አቅርቦት እንዲኖራቸው ከማድረግ ጋር ተያይዞ በተወሰነ ደረጃ ተግዳሮት እንዳለ አመልክተዋል።

ምንም እንኳን የምገባ አዳራሾች ቢኖሩም ምግብ ለማብሰያ የሚሆን #የመብራት_ኃይል አቅርቦት ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በት/ቤቶች ምገባ ሥራ ተሰማርተው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ሰዎች በተለይ #ከኑሮ_ውድነቱ አኳያ ሲታይ የሚከፈላቸው ክፍያ " በጣም አነስተኛ ነው " በማለት ሲያማርሩ ይደመጣሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንኑ ምሬታቸውን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ አለሙ ፤ " ከምገባ ክፍያ ጋር ተያይዞ እየቀረበ ያለው በየጊዜው እንደዬ ኑሮ ሁኔታው እየታዬ ይሻሻላል። " ብለዋል።

" ለምሳሌ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ማዕከል ያደረገ ጥናት በማድረግ ወደ #23 ብር በተማሪ (በነፍስ ወከፍ) እንዲያድግ ተደርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።

" በዚህ ዓመት ለምገባ ፕሮግራሙ መጠቀም ያለባቸው ተብሎ የተመደበው ወደ 3.2 ቢሊዮን ብር ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በዚያ ደረጃ የተወሰኑ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይኬዳል ማለት ነው። ሲጀመር (የምገባው ፕሮግራሙ) በ14 ብር ነበር አሁን #23 ብር የደረሰበት ሁኔታ አለ። ለቀጣይ ደግሞ ወቅቱን ባገናዘበ ሁኔታ እየተጠና የሚሻሻልበት አሰራሮች አሉ " ሲሉ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያገኘው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የምግብና ሥርዓተ ምግባ ቅንጅታዊ አሰራርን አስመልክቶ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሲያደርግ በነበረበት ወቅት ጥያቄ አቅርቦ ነው።

መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia