TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር አብይና አቶ ለማ🚁ነቀምት🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ነቀምቴ ከተማ ገብተዋል። በነቀምቴ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም የወለጋ ስታዲየምን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መርቀው እንደሚከፍቱ ይጠበቃል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝

የመብት እና ደህንነት ጥያቄዎች አሉብን ያሉት የጅማ ዩኒቨሲቲ የህክምና ተማሪዎች ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ::

ዘርዝር መረጃዎች ይኖረናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስብሰባውን ጥለው ወጥተዋል...

ጥያቄዎቻችን በአግባቡ እየተመለሱ አይደሉም ያሉት የህክምና ተማሪዎቹ ስብሰባውን ጥለው ወጥተዋል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነቀምቴ ከተማ ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነበው የወለጋ ስታዲየም የምረቃ ስነ ስርዓት እየተከሄደ ነው፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ተገኝተዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች:

•Doctors are naive:talented:symbolic: over all jewel to our society —
No More
*Disregarding
*ExploItation
*Abuse
*Insult

#stop_modern_slavery

•Treat us like human so that we can treat humans.
#Stop Mistreating Medical interns & Medical Students

•Medical Interns are not #machine can’t function 36 HRs sleeplessly!!

We should be Paid what we deserve!!

ተማሪዎቹ እያነሱት ባለው የመብት እና ደህንነት ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሚሰጥ አካል ካለ ሊያነጋግረን ይችላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ከኬኒያ ለማስመጣት ሂደት መጀመሩ ተነግሯል፡፡

የእሳት ማጥፊያ ሂሊኮፕተር ከኬኒያ የሚያስመጣው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነው ተብሏል።

ሂሊኮፕተሩን በቶሎ ወደ ሀገር ቤት ለማስመጣት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከኬንያ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከሳምንት በፊት በፓርኩ በተነሳው እሳት ከ342 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል እንደተጎዳ ይታወሳል።

ምንጭ - አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እሳት የተነሳባቸው አካባቢዎች ዋሊያዎች የሚኖሩበት ቦታ አለመሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ከኬንያ ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ኬንያ ፈቃደኛ መሆኗንና የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተሩን በቶሎ ለማስመጣትና ቃጠሎውን ለመቆጣጠርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከኬንያ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑም ታውቋል።

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia