TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HappeningNow

31 የቻይና ዩኒቨርሲቲዎች በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ለአንድ ቀን የሚቆይ ኤግዚቢሽን እያካሄዱ ይገኛሉ። በኤግዚቢሽኑ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን ሁለንተናዊ ትሥሥር በትምህርት ዘርፉም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጁዋን በበኩላቸው ቻይና በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንምትቀጥል ቃል ገብተዋል።

Via #ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HappeningNow

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀግብርን የተመለከተ ከልማት አጋሮችና የሀገራት አምባሳደሮች ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HappeningNow

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር ውይይት እያካሔደ ይገኛል!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ “የ2012 ዓ.ም ሰላማዊ መማር ማስተማር ሒደትን ማረጋገጥ” በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር በግብርና እና እንሰሳት ህክምና ኮሌጅ አዳራሽ ውይይት እያካሔደ ይገኛል፡፡

በውይይቱም የዩኒቨረርሲቲው የማኔጅመንት እና የካውንስል አባላት፣ የጅማ ከተማ መስተዳድር የስራ ሐላፊዎች፣ ከአባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ ቄሮዎች እና ቃሬዎች በ2012 ዓ.ም ሠላማዊ መማር ማስተማር ሒደት ውይይት ላይ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ስራውን እንዲፈጽም ሰላም ቀዳሚ መሆኑን አንስተው ሁሉም ተሳታፊዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ አጽንኦት በመስጠት ውይይቱን እንዲያስጀምሩ ለከተማ መስተደድሩ ከንቲባ እድሉን ሰጥተዋል፡፡

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መክዩ መሐመድ በቡኩላቸው በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አባቶችና እናቶች ልጆቻቸውን አስረክበውናል፤ በመሆኑም የልጆቻችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሐላፊነት አለብን በማለት ከቀበሌ አመረር ጀምሮ፣ የከተማው መስተዳድር፣ የሐይማኖት ተቋማት የየድርሻቸውቸን ወስደው መስራት እንዳለባቸወው በመግለጽ ውይይቱን ለተሳታፊዎቸ ክፍት አድርገዋል፡፡

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HappeningNow

በሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልና በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ አሊ ከድር መሪነት በዞኑ የባህል አዳራሽ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። እየተደረገ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃና ሌሎች የመሰረተ ልማቶችን በማስመልከት ተሳታፊዎች ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HappeningNow

ከቻይና ድጋፍ ለመድረግ የመጡ የህክምና ባለሙያዎች ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ በመከናወን ላይ ስላለው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምልላሽ አሰጣጥ ወቅታዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ - #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HappeningNow #Election2013

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1133/2011 አንቀጽ 7 መሰረት የደምፅ አሰጣጡን የተረጋገጠ ውጤት ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምርጫ ቦርድ በሂደቱ ላይ የነበረው በጎ ጅምር፣ ተግዳሮት፣ ማሻሻያና ተስፋ ላይ የሚመለከታቸው አካላት ፣ የሂደቱ ተሳታፊዎች እና ሌሎች ለምርጫው ሂደት መሳካት አስተዋእጾ ያደረጉ አካላት የሚገኙበት ኮንፍረንስ በስካይ ላይት ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።  

ዝግጅቱን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።

መደበኛ መርኃግብሩ ሲጀምር በ VoiceChat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#HappeningNow

የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላትን እያስመረቀ ይገኛል።

በሀገር መከላከያ ሚኒሰቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዛሬ እያስመረቀ የሚገኘው ሶስተኛው ዙር በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ምልምል አባላትን ነው።

በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትእ አቶ ደመቀ መኮንን እንደሚገኙ ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#HappeningNow : የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት 2ኛ ዙር የጸረ ሽምቅ ፖሊስ በባምባሲ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ እያስመረቀ ይገኛል።

Photo Credit : BGMMA

@tikvahethiopia
#HappeningNow : በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ የሠላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ ከፍተኛ የክልል፣ የዞን አመራሮች ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች ተገኝተዋል።

በጉራፈርዳ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ከዚህ ቀደም በነበረው የፀጥታ ችግር በርካታ ነዋሪዎች መገደላቸው ፤ እና መፈናቀላቸው አይዘነጋም።

ፎቶ : ከቤንች ሸኮ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#HappeningNow : 9ኛ ዙር የአማራ ልዩ ሀይል ፓሊስ የምረቃ ስነ ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት በደብረማርቆስ ከተማ የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሌጅ የ9ኛ ዙር የአማራ ልዩ ሀይል ምልምል ፓሊስ ሰልጣኞችን እያስመረቀ ነው።

@tikvahethiopia