TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ማስታወቂያ-ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ⬇️

ቀን ነሐሴ 20/2010 ዓ.ም.

የተከበራችሁ የተማሪዎች ወላጆች፦

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የ3ኛ ዓመት ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ከአጠቃላይ ፈተና (Holistic Exam ) ጋር በተያያዘ ማጠቃለያ (Final Exam) አንቀመጥም ማለታቸውን ተከትሎ የባሕር ዳር ቴከኖሎጅ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክ ካውንስል የ3ኛ አመት ተማሪዎችን ለ1 አመት ከትምህርት ገበታ እንድታገዱ ወስኗል፡፡

ይህ ቅጣት በዩኒቨርሲቲው ሕግና በተማሪዎች መተዳደሪያ ደምብ መሰረት የመጨረሻ ትንሹ ቅጣት ነው፡፡ ሆኖም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወላጆች ዋና ባለድርሻ አካላት እንደሆኑ በጽኑ ያምናል፡፡ ስለሆነም በባሕር ዳርና አካባቢው ያሉ የተማሪዎች ወላጆችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ማወያየት ስላስፈለገ በባሕር ዳርና አካባቢው የምትገኙ ወላጆች #ሰኞ ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. በቴክኖሎጄ ኢንስቲትዩት ፖሊ ግቢ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በአዳራሽ ቁጥር 3 እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀረሪ ክልል⬇️

የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ህገ ወጥነትን ለማስቀረት የሚሰራ ኮሚቴ ማቋቋሙን የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ገልፀዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕስ መስተዳር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ አገራችን በለውጥ ውስጥ እንዳለች ትላንት በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይፈልጉ ጥቅማቸው የተነካ አካላት በእምነትና በጎሳ #ግጭት ለመፍጠር እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በክልላችንም አልፎ አልፎ ይኸው ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልፀዋል ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በመቀጠልም #የህግ የበላይነትን ለማስከበር በክልሉ ምክር ቤት የሰላም ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ የተከማቸውን #ቆሻሻ አስመልክቶም የከተማዋ ነዋሪዎች እስካሁን ላሳዩት #ትእግስት ምስጋና አቅርበው ቆሻሻው በቀጣዮቹ ሁለት
ቀናት ውስጥ ይወገዳል ብለዋል፡፡

በፀጥታው በኩል #ከቄሮ እና #ፋኖ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ባሉበት ቦታ #ሰኞ ምክክር እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፋር ክልል ጥቃት ተፈፀመ‼️

#ሰኞ መጋቢት 16 እና #ማክሰኞ መጋቢት 17 በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ከጎረቤት ሀገራት መጡ የተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ። ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሌ ላንድ እና ከጅቡቲ አዋሳኝ አካባቢዎች በኩል በገቡ ኃይሎች መሆኑን የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ አህመድ ኻሌይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/በአፋር-ክልል-ጥቃት-ተፈፀመ-04-04-2
#MekelleUniversity

የመቐሌ ዩኒቨርስቲ በተለያየ ምክንያት ወደየ ቀያቸው መሄድ ላልቻሉ ተማሪዎች የሽኝት ኣገልግሎት ለመስጠት ባሶችን ማመቻቸቱን ገልጿል።

በመሆኑም ባሶቹ MoSHE ከ ትራንስፖርት ሚንስተር ጋር በመተባበር ኣስር (10) ባሶችን የሚያቀርብ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት መንገድ ላይ እንደሆኑ እና እሁድ ገብተው እንደሚያድሩ ማወቅ ተችሏል።

አገልግሎቱ የሚሰጣቸው ተማሪዎች :-

1. መደረሻቸውን ደቡባዊ ትግራይ የሆኑ፤
2. ከክልል ውጪ ላሉት ተማሪዎችን ደግሞ እስከ አዲስ አበባ ለሆኑ፤
3. የትግራይ ተማሪዎች ሆነው ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የሚሄዱ ካሉ፤

በዚህ መሰረት ያልተመዛገቡ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የተማሪ ህብረት ቢሮዎች እንዲመዘገቡ መልዕክት ተላልፏል።

ማሳሰቢያ:-

- ባሶቹ ልክ #ሰኞ ጠዋት 12፡00 ሰዓት ከየ #ጊቢው እንደሚነሱ አውቃችሁ ተማሪዎች አስፈላጊዉን የሆነውን ዝግጅት ሁሉ እንድታደረጉ፤

- እንዲሁም ጊቢው ውስጥ ላሉ ተመራቂ ተማሪዎች ጓደኛ እና ወላጅ የሆናችሁ ይህን ተገንዝባችው ተማሪዎችን እንድታሳውቁ ሲል የመቐሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ገልጾልናል።

Via Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.

@tikvahethmagazine
#ምርጫ2013

የምርጫ ዝግጅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል :

• በአጠቃላይ 22 የምርጫ ክልሎች አሉ።
#ሰኞ በአሶሳ ዞን ስር በሚገኙ 8 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ይካሄዳል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰኔ 14 ምርጫ በሚካሄድባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን በኢትዮጲያ የምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርጫፍ ጽ/ቤት አሳውቋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምርጫው በሁለት መርሀ ግብር ነው የሚካሄደው።

በክልሉ በ8 የምርጫ ክልሎች በ302 የምርጫ ጣቢያዎች ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫው የሚካሄድ ሲሆን፣ የጸጥታ ችግር ተስተውሎባቸው የነበሩ የመተከል እና ካማሽ ዞኖች የምርጫ ጣቢያዎች ጳጉሜ 1/2013 ዓ.ም ነው ምርጫ የሚደረገው።

ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ 7 የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ይወዳደራሉ።

ከ360 ሺ በላይ መራጮች ድምጽ መስጠት የሚያስችላቸውን ካርድ ወስደዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ድርጊቱ አስደንግጦናል፤ ረብሾናል " - ኢሰመኮ በሁለት ፖሊስ አባላት ድብደባ ሲፈፀምባት የነበረችው እናት በልመና የምትተዳደር ሲሆን አጠገቧ የነበረችውም ልጇ ናት። ድርጊቱ "ጀሞ ሚካኤል መብራት" አካባቢ የተፈፀመ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በድርጊቱ ክፉኛ መደንገጡን እና መረበሹን አሳውቋል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር…
" ሁለቱ የፖሊስ አባላት ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ " - ጠቅላይ ዐቃቤ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የተገለፀው የልጅ እናቷን ሴት የደበደቡት እና ያንገላቱት ሁለቱ የፖሊስ አባላት #ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ አሳውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራው በአስቸኳይ በማጠናቀቅ ሰኞ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
#Update

የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የወታደራዊ አመራሮች #ሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም በጎረቤት ሀገር ኬንያ ፤ ናይሮቢ ሊገናኙ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

በዚህ መድረክ ላይ የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ ተገናኝተዉ በትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት ላይ እንደሚወያዩ የተገለፀ ሲሆን በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ #ስራዎች_መጀመራቸው ተገልጿል።

በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

የፊታችን ሰኞ ደግሞ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው እንደሚወያዩ መገለፃቸውን የብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ ይወስዳሉ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ፤ " እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ያ ማለት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሯቸውን ከሞላ ጎደል እነኚህን ኮርሶችን እንዲማሩ እናደርጋለን " ብለዋል።

" ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ አራት ወር ወስደን ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ መጫረሻ አካባቢ እነኚህን ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ እናደርጋለን " ሲሉ ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና ይመዘኑና ከመቶ ይያዝላቸዋል ፤ እሱን ወደ 30% ቀይረን ከማዕከል ተመሳሳይ ፈተና በግል ተቋማትም ዕጩ ለሆኖ ፍሬሽ ተማሪዎች በመንግስት ተቋማት ላሉ እጩ ፍሬሽ ማን ተማሪዎች ተመሳሳይ ፈተና እንሰጣለን። ይሄንን አድርገን 50 % እና ከዛ በላይ ያመጡትን ወደ መደበኛ ፌሽ ማን ፕሮግራም እንዲገቡ ይደረጋል። መደበኛ ፍሬሽማን ፕሮግራም ተከታትለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ይሆናሉ " ብለዋል።

ተማሪዎች የሚማሩት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ያሳዩት ጉድለት ሲሆን ፦

- ቋንቋ፣
-  ሂሳብ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ (ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ) አስፈላጊ ከሆነ ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ ይዘት ይጨምሩላዋል ተብሏል።

በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ፦

- ጂዮግራፊ፣
- ታሪክ፣
- ቋንቋ እና ሂሳብ የሚማሩ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች እንደፍላጎታቸው ተጨማሪ ይዘት ሊጨምሩላቸው እንደሚችሉ ተገልጿል።

መንግስት ለ100 ሺህ ተማሪዎች የቅድመ ፍሬሽማን ኮርስ እድል የሚያማቻች ሲሆን ለዚህም ቁርጥ ያለ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ኮርስ ለሚወስዱ መንግስት ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ እንደሚያስቀምጥ ተነግሯል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፦

" ወጪውን ችሎ ወደ መንግስት ተቋማት የሚሄደው የግል ውሳኔ ስለሆነ አነስተኛውን መቁረጫ ነጥብ ብቻ መንገር ነው የኛ ኃላፊነት።

በመንግስት የሚሄደውን መለየት ስላለብን በዝርዝር ለሴቶች፣ ለወንዶች፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ፣ አካል ጉዳት ላለባቸው፣ ከታዳጊ ክልል ለመጡ፣ ለአርብቶ አደር አካባቢዎች በዝርዝር ማስቀመጥ ስላለብን 100 ሺ ለመቀበል ስንት ተማሪ ምንያክል መቁረጫ ነጥብ አድርገን ነው የምናገኘው የሚለው የመንግስት ውሳኔ ነው የሚሆነው።

እኚህ መንግስት ወጪያቸውን ችሎ፣ ዶርም አስገብቶ፣ አብልቶ ፣ አስተኝቶ ሬሚዲያል ፕሮግራም ለሚሰጣቸው ነው።

በራስ ለሚወሰን አነስተኛውን ነው መንገር ያለብን በራስ ውሳኔ የሚለው የግድ ወደ ግል ተቋማት ይሄዳሉ ማለት አይደለም በመንግስት ተቋማትም ሊማሩ ይችላሉ ወጪያቸውን ሸፍነው " ብለዋል።

ይኸው እድል ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

በ2014 ዓ/ም ፈተና ያለፉ #ተማሪዎችን_ምደባ እስከ #እሁድ ለማሳወቅ ፤ የቅድመ ፍሬሽማን ተማሪዎችን መቀበያ ነጥብ እስከ #ሰኞ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ተናግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #Eurobond ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም። ገንዘብ ሚኒስቴር የክፍያ መጠኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል እንደሚቻል ገልጿል። ክፍያውን ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች በፍትሃዊነት እኩል ለማስተናገድ ነው ብሏል። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #Eurobond

ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ በወቅቱ ያልከፈለችው ለምንድነው ?

ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም።

የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ የቀረበው ከ9 ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም ነበር።

ኢትዮጵያ ይህንን ቦንድ ሸጣ ከገዢዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘች ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው በ10 ዓመት ውስጥ ነው።

እስከዚያው ድረስ መንግሥት በዓመት ሁለት / 2 ጊዜ የሚፈጸም የ6.625 በመቶ ዓመታዊ ወለድ ለቦንዱ ገዢዎች ይከፍላል።

ኢትዮጵያ ባለፈው ሰኞ ዕለት 33 ሚሊዮን ዶላር ወለድ መክፈል የነበረባት ቢሆንም ክፍያውን ሳትፈጽም ቀናት አልፈዋል።

" የክፍያ መጡኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል ይቻላል ፤ ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች እኩል ለማስተናገድ ነው " - ገንዘብ ሚኒስቴር

የብድር ቦንዱን አስመልክቶ ትላንትና ከቦንድ ገዢዎች ጋር የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በነበሩበት ውይይት ተደርጎ ነበር።

ይህን በተመለከተ ገንዘብ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ኢትዮጵያ #የታኅሣሥ_ወርን ወለድ ያላስተላለፈችው ክፍያውን ለማዘግየት ወስና ነው። ይህም ለገዢዎቹ ተገልጿል።

- ኢትዮጵያ #ወለዱን_ለመክፈል የሚያስችል ገንዘብ አላት።

- ክፍያውን የማዘግየት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ሁሉንም የውጪ አበዳሪዎች በፍትሐዊነት ለማስተናገድ ሲባል ነው።

- አበዳሪዎች #በፍትሐዊነት ለመመልከት አለመቻል በዕዳ ሽግሽግ ላይ ከሌሎች የውጭ አበዳሪዎች ጋር የሚደረገውን ውይይት አደጋ ላይ ይጥለዋል። ወለዱ ቢከፍል መስተገጓጎል ሊያጋጥም ይችላል።

- በቅርቡ ከኦፊሴላዊ አበዳሪዎች ጋር የብድር ክፍያ ሽግሽግን በተመለከተ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- #የቦንድ_ገዢዎችን ጨምሮ ሌሎች አበዳሪዎችም ተመሳሳይ አይነት የብድር ክፍያ ማስተካከያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ከሁሉም አበዳሪዎች ጋር በሚኖር ግንኙነት ላይ #ወጥነት እና #እኩልነትን ለማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የብድር እፎይታ ....

* ኢትዮጵያ ላለባት ብድር #የብድር_እፎይታ ለማግኘት በ " ቡድን 20 " የጋራ ማዕቀፍ በኩል የዕዳ ሽግሽግ ለማድረግ ውይይት ስታካሂድ ቆይታ ነበር።

* ባለፈው ኅዳር ወር በቻይናና በፈረንሳይ በሚመራው የፓሪስ ክለብ አማካኝነት የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

* በዚህ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ለአበዳሪዎቿ መክፈል የሚጠበቅባትን ብድር እና ወለድ 2 ዓመት ገደማ አትከፍልም።

* ይህ የዕዳ ክፍያ ሽግሽግ በየዓመቱ የሚከፈለውን 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዕዳ በጊዜያዊነት የሚያስቀር ነው።

ኢትዮጵያ የዚህን አይነቱን ስምምነት የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንዱን ከገዙ የግል ባለሀብቶች ጋርም ለመፈጸም ትፈልጋለች።

የዋናው ብድር የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምና በየዓመቱ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔው ከ6.625 በመቶ ወደ 5.5 በመቶ ዝቅ ማድረግ ሀሳብ አላት።

መንግሥት የብድር አከፋፈሉ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የፈለገው ከሌሎች አገራት ጋር በሚያደርገው የብድር ሽግሽግ ላይ አበዳሪዎችን በተመሳሳይ መልኩ ማስተናገድን በተመለከተ ስጋት እንዳይነሳ በማሰብ መሆኑን አሳውቋል።

መንግሥት የብድር አከፋፈል ማስተካከያው ላይ ከቦንዱ ገዢዎች ጋር በተቻለ ፍጥነት ስምምነት ላይ መድረስ ጠንካራ ፍላጎት አለው።

የቦንዱ ገዢዎች ጋር ያለው ስሜት ምንድነው ?

° ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለዱን በቀኑ እንደማትከፍል ማስታወቋ በቦንዱ ገዢዎች ዘንድ በመልካም አልተወሰደም።

° የቦንዱ ገዢዎች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ አላስፈላጊ እና አሳዛኝ አድርጎ እንደሚመለከተው ገልጿል።

° የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔውን የማያጥፍም ከሆነ ከፍ ያለ ዳፋ ይኖረዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፈው #ሰኞ መክፈል የነበረባትን ወለድ ለቦንድ ገዢዎች ለማስተላለፍ የ14 ቀናት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቷታል።

በእነዚህ በተሰጡ ቀናት ውስጥ ወለዱን የማትከፍል ከሆነ ውልን አለማክበር (#technical_default) እንደሚገጥማት የዘርፉ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

" ፊች " የተሰኘው የአገራትን ብድር የመክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣ አሜሪካ ተቋም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ዕዳ የመክፈል ደረጃ ከነበረበት " ሲሲ " (CC) ደረጃ ወደ " ሲ " (C) ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል።

ተቋሙ ለዚህ ደረጃ ምደባ የጠቀሰው አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያ የቦንዱን ወለድ በቀኑ አለመክፈሏል ነው ያለ ሲሆን በ14 ቀናት ውስጥ ክፍያው ካልተፈጸመ ይህንን ደረጃ በድጋሚ ዝቅ እንደሚያደርገው ገልጿል።

Credit - BBC AMAHRIC / REUTERS

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#StockMarket (የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችን በቅርበት በሚከታተሉት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ድረገፅ ከሰጡት ቃለምልልስ የተወሰደ) ስቶክ ገበያ ምንድነው ? ለስቶክ ማርኬት ‘ የድርሻ ገበያ ’ የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን። ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ ያቀርባሉ። ሰዎች ይህን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነ መጠን…
#CapitalMarket #Ethiopia

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016 ስራ ላይ ውሎ ይገኛል።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፊታችን #ሰኞ ጀምሮ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል እንደሚጀምር አሳውቋል።

በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው አካላት በመመሪያው የተቀመጡትን የፈቃድ መስፈርቶችን በማሟላት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ የ " ኢንቨስትመንት ባንክ " ፍቃድ መስጠት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አሳውቋል።

በዚህ ላይ መሰማራት የሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟላ አካል ቢሮ ድረስ በመሄድ ማመልከቻ ማስገባት ይችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ፦

- የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ምን ማለት ነው ?

- ማመልከት የሚችለው ማነው ?

- የአገልግሎት ሰጪ ፈቃድ ለማግኘት ዋና ዋና መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

- የማመልከቻ አቀራረብ ሂደቱ ምን ይመስላል ? የሚሉትን ጉዳዮች ከላይ በተያያዘው አጭር ማብራሪያ መመልከት ይቻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኢትዮጵያ የካፓታል ገበያ ባለስልጣን ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia