TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia🇪🇹 vs #SouthAfrica🇿🇦

ነገ የሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ጋር ይፋለማል።

ጨዋታው በውቢቷ ባህርዳር ከተማ ነው የሚካሄደው።

ለዚሁ ጨዋታ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አባላት ዛሬ 28/01/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ሲል ባህርዳር ደርሰዋል።

የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ከረፋዱ 3:30 ጀምሮ የመጨረሻ ልምምድ በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም አድርገዋል።

ከነገው ጨዋታ ጋር በተያያዘ የብሄራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዛሬ አመሻሽ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሠጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ (ስፖርት) በኩል ደግሞ ተጨማሪ መረጃዎች ማግኘት ትችላላችሁ : https://t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

#ምንጊዜም_ኢትዮጵያ❤️

@tikvahethsport @tikvahethiopia