TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስሜን ተራሮች🔝

የስሜን ተራሮች ቃጠሎ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው:: የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ግጭ አካባቢ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እየተቃጠለ ነው። በፓርኩ አስተርጓሚና አስጎብኝ የሆነው ወጣት አስረሳኸኝ ሞላ ለአብመድ እንደገለፀው ቃጠሎው ሰፊ ቦታን ያካለለና #ለመቆጣጠር የከበደ ነው።

ከትናንት ጀምሮ እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከዛሬ እኩለ ቀን በኋላ ከአቅም በላይ መሆኑን ተነግራል። በቃጠሎው ምክንያት በአካባቢው ያለውን ማረፊያ ካምፕ ጥለው መውጣታቸውንም ነግሮናል።

የፓርኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው ደግሞ እሳቱ በከፍተኛ ነፋስ እየታገዘ በመሆኑ ለመቆጣጠር ማስቸገሩን ተናግረዋል። በተለይ ከቀኑ 6:00 ገደማ ጀምሮ እሳቱ ሰፊ ቦታን እያካለለ መሆን ተናግረዋል።

ከፍተኛ የሰው ኃይል እሳቱን ለመቆጣጠር መሠማራቱን የገለጹት አቶ ታደሰ ምግብ እየቀረበላቸው አሁንም ከዚያው ሥራ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ነዳጅ እና የነዳጅ ውጤቶችን የሚያስተዳድር ባለሥልጣን ለማቋቋም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቂቅ ሕግ እንደቀረበ ሸገር ዘግቧል፡፡ ረቂቁ የአዲሱ ተቋም ዐላማ በመላ ሀገሪቱ ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትን እና ሥርጭትን መቆጣጠር እንደሚሆን ይገልጻል፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ነዳጅ ወደ ሀገር እንዲገባ እና ፍትሃዊ ሥርጭት እንዲኖር የቁጥጥር ሥርዓትም ይዘረጋል፡፡ ረቂቅ ሕጉ ከጸደቀ የባለሥልጣኑ ተጠሪነት ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ይሆናል፡፡

Via Sheger FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአልጀርያ ምክር ቤት ዛሬ አዲስ #የሽግግር ጊዜ መሪ ሰየመ። ባለፈው ሳምንት ሥልጣናቸውን በለቀቁት በቀድሞው የአልጀሪያ ፕሬዝዳንት አቤደላዚዝ ቡተፍሊካ ምትክ አብዱልቃድር ቤንሳላህን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት መርጧል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዝዳንት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ በ43ኛው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሠልጣኞችና የቡድን መሪዎችን ዛሬ ማምሻውን በተደገ የእራት ግብዣ ላይ አመሰገኑ። አትሌቶቹ ለሀገራቸው 5 ወርቅ፣ 3 ብርና 3 የመዳብ ሜዳልያዎችን በማስገኘት ከ63 ተሳታፊ ሀገራት በሜዳሊያ ሰንጠረዥ 1ኛ ደረጃ ላይ እንድትሆን አስችለዋል። ጠ/ሚሩ ለኮሚቴው አመራርና አብላጫ ውጤት ላስመሰገቡ አትሌቶች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበርክተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው ሌላ ክልል #እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ #ተስፋቸውን ይቁረጡ፡፡›› የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልሉ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው #ግጭት ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በግጭቱ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች እና በደረሰው የንብረት ውድመት አዴፓ ማዘኑን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ለተጎጅ ቤተሰቦችና ወገኖች #መፅናትን ተመኝተዋል፡፡

ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት የክልሉ መንግሥት ሥጋቱን ያውቀው እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም ‹‹እንደስጋት በክልሉ የፖለቲካ ኃይሎች ግጭትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምቶች ነበሩን፤ ግን ከገመትነው #የፈጠነ ሆኖብናል›› ብለዋል። ይህን ያክል የንብረት እና የሰው ሕይወት ጠፍቷል ለማለት የቴክኒክ ቡድኑ የጥናት ምላሽ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ ሕግና ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ በአዴፓ እና በክልሉ መንግሥት እምነት አጥቷል የሚሉ ሐሳቦች ይደመጣሉ በእናንተ በኩል ምን ግምገማ አለ? ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም አቶ ዮሐንስ ‹‹እንዲያውም አሁን ሕዝቡ በአዴፓ ላይ ከፍተኛ #እምነት የጣለበት ወቅት ነው፤ አዴፓ በሕዝቡ አመኔታ ማግኘቱን ተከትሎ #ለመነጣጠል የሚፈልጉ ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ በመሆኑ ሕዝቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡ ‹‹በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች የአዴፓ እና የአማራ ሕዝብ አንድነት የሚያስፈራቸው ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ ነው›› በማለትም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ መራር በሆነው በዚህ ጊዜ #አብሮነቱን እንዲያጠናክር የጠየቁት አቶ ዮሐንስ ‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው በሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ፤ ከአጐራበች ክልሎች እስከ ፌዴራል መንግሥት ድረስ ወንጀለኞችን ለመያዝ በጥምረት እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡ በክልሉ መሠል ችግር እንዳይከሰት ብቁ ዝግጅት እንደተደረም ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያማል---እጅግ በጣም ያማል‼️

በዚህ ሳምንት #የመን ርዕሠ-ከተማ #ሰነዓ ውስጥ በሁለት ትምሕርት ቤቶች አቅራቢያ በተጣለ #ቦምብ 14 ህጻናት መገደላቸዉን የተመድ #የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አወገዘ።

የድርጅቱ የመካከለኛ ምሥራቅ እና የሰሜን አፍሪቃ ክፍል ሃላፊ ጊርት ካፔላሬ እንዳሉት ህጻናትን መግደል እና አካለቸዉን ማጉደል የህጻናትን መብቶች የሚጻረሩ እጅግ ከባድ ወንጀሎች ናቸው። እርምጃው ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምሕርት ቤት እንዳይልኩ የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰዋል። በጥቃቱ ሌሎች 16 ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አብዛናዎቹ እድሜያቸው ከ9 ዓመት በታች ነው። #ሰንአ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ከሚደረግላቸው ክፉኛ ከተጎዱት ውስጥ በአስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙም እንዳሉ ገልጸዋል።

ባለፈው እሁድ የየመን አማጽያንን የሚወጋው ሳዑዲ መራሹ ህብረት ሰንአ ውስጥ በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ባካሄደው የአየር ድብደባ ቢያንስ 11 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ አማጽያን ተናግረዋል። እንደ አማጽያኑ ከተገደሉት አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ናቸው።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈይሳ ሌሊሳ ተሸለመ🔝

ከሁለት አመታት በፊት በሪዮ ኦሎምፒክ እጆቹን ከፍ አድርጎ በማጣመር የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ #በተቃዋሚዎች ላይ ይወስድ የነበረውን የኃይል እርምጃ #የተቃወመው ፈይሳ ሌሊሳ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሽልማት ተበረከተለት። ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለፈይሳ ሽልማቱ የተበረከተለት በሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር #ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ በማስገኘቱ ነው።

Photo: #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት እራስን መሆን፣ ለዓላማ መቆም፣ ህሊናን አለመዘንጋት፣ ፍርድን አለማጓደል፣ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም አርአያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው?" ዶክተር #ምህረት_ደበበ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰሜን ሸዋ ግጭት እንዲከሰት ያደረጉ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ እንሰራለን - ኦዲፒ

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርና በሰሜን ሸዋ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ግጭት እንዲከሰት ያደረጉ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ እንደሚሰራ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል፡፡

ኦዲፒ የተፈጠረዉን ችግር ለማረጋጋት እና ተመሳሳይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ በግጭቱ ህይወታቸውን ባጡ ቤተሰቦች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethopia
#Update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ከኃላፊነታቸው ተነሱ። ኮሚሽኑንን ከዘጠኝ ወራት በላይ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ መነሳታቸው ተገልጿል፡፡

ኮሚሽነሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር
የኮሚሽኑን የቀድሞ ሃላፊ አቶ ይህደጎ ሥዩምን ተክተው የተሾሙት።

ሜጀር ጄኔራል ደግፌ፣ ከኃላፊነታቸው በድንገት የተነሱበት ዝርዝር ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. የደረሳቸው የስንብት ደብዳቤ ግን ‹‹በጡረታ›› የሚል መሆኑ ታውቋል፡፡

ላለፉት ዘጠኝ ወራት ኮሚሽኑን ሲመሩ ቆይተው፣ ከሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia