TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara

" የፋኖ ኃይሎች ወደ ድርድር መግባትን በመርህ ደረጃ ይቀበሉታል፡፡ ነገር ግን በመንግሥት ላይ እምነት የላቸውም " - የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል

በአማራ ክልል በሚፋለሙት የፌዴራል መንግሥት እና የፋኖ ኃይሎች መካከል ያለው ሥር የሰደደ አለመተማመን ሰላም ለማውረድ የሚያደረገው ጥረት ፈተና እንደሆነበት፣ የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አስታውቋል።

የካውንስሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ምን አሉ ?

(ለሪፖርተር ጋዜጣ)

- የፌዴራል መንግሥት አመራሮችን ለማግኘት ጥረት ተደርጎ ነበር ግን አልተሳካም። እስካሁን ከፌዴራል መንግሥት በኩል ተገናኝቶ መወያየት የተቻለው ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ብቻ ነው። የሰላም ሚኒስቴርም ካውንስሉ የሚያቀርበውን ጥሪ እንደሚቀበል አሳውቋል።

- ከተለያዩ የፋኖ ኃይሎች ጋር ንግግር ተደርጓል። ወደ ድርድር መግባትን በመርህ ደረጃ ይቀበሉታል፡፡ ነገር ግን በመንግሥት ላይ እምነት የላቸውም። ' ጊዜ መግዣ ነው ' ብለው ያምናሉ፣ እኛንም የፈተነን ይኸው ያለመተማመን ችግር ነው።

- ከፌዴራል መንግሥት በኩል ካውንስሉ ተጨማሪ ሥራዎች ይጠብቁታል። የፌዴራል መንግሥት ለሰላም ዝግጁ መሆኑን መናገር ብቻ ሳይሆን ምቹ ሁኔታን መፍጠር አለበት።

- በሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች መካከል መተማመንን ለመፍጠር ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እገዛ ለማግኘት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር፣ ከኢጋድና ከአፍሪካ ኅብረት አመራሮች ጋር በቅርቡ ውይይት ተደርጓል።

- ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ንግግር ተደርጓል፤ እነሱ ለማገዝም ዝግጁ ናቸው። በካውንስሉ በኩል ደግሞ እየደረሰ ካለው ጉዳት አንፃር " የአማራ ክልል ሁኔታን ችላ ብላችሁታል " ብለናቸዋል።

- የአሜሪካ አምባሳደርን ጨምሮ ከስድስት ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም የክልሉን የሰላም ዕጦት ችላ ማለታቸውን ተጠቁሞ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ማሳደር እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ካውንስሉ የሚያደርገውን ጥረትም ሆነ ድርድሩ እንዲሳካ ለማገዝ ፈቃደኛ ነው። ነገር ግን በፋኖ አደረጃጀት ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡ 

ካውንስሉ አግኝቼ አናገርኳቸው የሚላቸው የፋኖ ኃይሎች እነማን ናቸው ? የትኛውን የአደረጃጀትስ ነው ያናገረው ? ለዚህ ጥያቄ ፦

" ይህንን መናገር አያስፈልግም፣ ምክንያቱም አንዳንዶች ነገሩን ' እገሌ ሊደራደር ነው ' በማለት መበሻሸቂያ አድርገውታል፡፡ በመሆኑም ከየትኛው የፋኖ አመራር ጋር እንደተወያየን መግለጽ ጠቃሚ አይደለም።

' እገሌ ሊደራደር ነው ' የሚለውን ጉዳይ የፋኖ ኃይሎች እንደ መበሻሸቂያ እየተጠቀሙበት ስለሆነ፣ ካውንስሉ የተደራጀ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በፋኖ በኩል እገሌ እንዲህ ብሏል ከማለት እንቆጠባለን። " ሲሉ መልሰዋል።

የፋኖ ኃይሎች ድርድርን በመርህ ደረጃ እንደሚቀበሉት ነገር ግን " የፌዴራል መንግሥት ድርድሩን እንደ ጊዜ መግዣነት ሊጠቀምበት ነው " የሚል እምነት እንዳላቸው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ካውንስሉን" ሀቀኛ ድርድር ለማድረግ ሳይሆን ለማምታታት ነው " የሚል ሐሳብ እንዳላቸው ተጠቁሟል።

ይሁንና አለመተማመኑን ለመቅረፍ የሁሉንም አካላት ቅንነት ካውንስሉ እንደሚፈልግ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል አመላክቷል።

#Amahra #Ethiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

'' በዚህ ጦርነት ውስጥ ማን እየተጠቀመ እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም '' - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት

" በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ዓላማው ሊገባኝ አልቻለም " ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ገለጸ።

ም/ቤቱ ይህን ያለው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።

የም/ቤቱ ዋና ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ ፥ " በሁለቱ ክልሎች ያለ መፍትሄ የቀጠለው ግጭት የጋራ ምክር ቤቱን በእጅጉ አሳስቦታል " ብለዋል።

" ንጹሃንን እየገደለ፣ እያሰቃየ እና የሀገርን ሀብት እያወደመ ያለውን ግጭት ሁለቱም አካላት ቆም ብለው አስበው ምን እንዳመጣ እራሳቸውን ሊጠይቁ " ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

" ንጹሃን፣ ባለስልጣናት እና የባለስልጣናት ልጆች እየተገደሉ እየታፈኑ ነው " ያሉት ዋና ሰብሳቢው " በዚህ ጦርነት ውስጥ ማን እየተጠቀመ እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም " ሲሉ አስረድተዋል፡፡

" በጦርነቱ እንደ ሀገር ሀገር እየተጎዳ ነው፣ እንደ ህዝብ ህዝብ እየተጎዳ ነው ፣እንደ ዜጋ ዜጎች እየተጎዱ ነው ፣እንደ ታሪክ ታሪክን እያበላሽን ነው ምን ዓይነት ስሌት አስልተን እንደምንረጋጋ አላውቅም " ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ውድመት እያስከተለ ቀጥሏል ያሉት አቶ ደስታ ችግሩን በንግግር ለመፍታት በሁለቱም ወገን ፍላጎት አይታይም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

" አንዱ በአንዱ ላይ የበላይ ለመሆን ከሚደረግ ሩጫ የዘለለ ግጭቱን በንግግር የመፍታት ፍላጎት እየተመለከትን አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ታጣቂዎች ሆኑ መንግስት ችግሩን በንግግር ከመፍታ ይልቅ ግጭቱን ስም ለማጠልሸት አንዱ ሌላውን ለመወንጀል እና የህዝብ ድጋፍ ለማግኝት እየተጠቀሙበት ነው " ብለዋል።

ምክር ቤቱ በመንግስት እና በታጣዊዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት ሁለቱም አካላት እቆምለታለሁ ፣ እቆረቆርለታለሁ የሚሉትን ህዝብ እና ሀገርን እያወደመ መሆኑን አውቀው በንግግር ችግራቸውን እንዲፈቱ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጠው ቃል ጠይቋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዕለታዊ ዛሬ ንግድ ባንክ የዶላር መግዣ ላይ ጭማሪ በማድረግ ወደ 108 ብር ከ0728 ሳንቲም አስገብቷል። መሸጫው 119 ብር ከ9608 ሳንቲም ነው። በአቢሲኒያ ባንክ አንዱ ዶላር 108 ብር ከ0729 ሳንቲም መግዣ ፤ 121 ብር ከ0416 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦላታል። በወጋገን ባንክ የዶላር መግዣው 115 ብር ከ0121 ሳንቲም ነው። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ107…
#ዶላር

የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ አሳይቷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ7 ቀናት ጭማሪ ያልታየበት ወጥ የምንዛሬ ዋጋ ነበር።

ባንኩ ዛሬ ሲያገበያይበት የነበረው የምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ የታየበት ነበር።

አንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣው ወደ 112 ብር ከ3957 ሳንቲም ደርሷል።

የመጫው ዋጋም 124 ብር ከ7592 ሳንቲም ገብቷል።

በፓውንድ ላይም ጭማሪ ተመዝግቧል።

አንዱ ፓውንድ መግዣው 141 ብር ከ6314 ሳንቲም ተቆርጦለት ውሏል። መሸጫው 157 ብር ከ9487 ሳንቲም ነበር።

ዩሮ መግዣው 125 ብር ከ0177 ሳንቲም መሸጫው 138 ብር ከ7697 ሳንቲም ሆኖ ውሏል።

የUAE ድርሃም መግዣው 30 ብር ከ6030 ሳንቲም መሸጫው 33 ብር ከ9693 ሳንቲም ገብቷል።

#Ethiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹

" ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት ትከታተላለች አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ተገቢውን ምላሽ ትሰጣለች " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፥ " የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ልዩ ትኩረት ይሰጣል " ሲሉ ጠቁመዋል።

" ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ በበጎ መንፈስ የተቃኘ ዘላቂ ዲፕሎማሲ ላይ አተኩራ ትሰራለች "ም ብለዋል።

" የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴም ሊቆም ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት እንደምትከታተልና አስፈላጊ በሆነበት ጊዜም ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።

አምባሳደር ነቢያት ፥
➡️ ከአውሮፓ ህብረት፣
➡️ ከአሜሪካ
➡️ ከተመድ ልዩ መልዕክተኞች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ጠቁመዋል።

" ለሁሉም መልዕክተኞች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ሆኖ የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል " ብለዋል። #EPA

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል፡፡

የባቡር ትራንስፖርት ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ የሚያገለግል ነበር።

የአገልግሎቱ መጀመር ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ይጨምራል ፤ የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል ብለዋል።

#Ethiopia #EngTakelUma

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ። #ኦርቶዶክስተዋሕዶ @tikvahethiopia
#Ethiopia

" በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በመላው ሀገሪቱ በተለይም #በአዲስ_አበባ መስቀል አደባባይ የተከበረው የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ህዝብ ፣ ለሀይማኖት አባቶች ፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ፣ ለወጣቶችና በተለይ ደግሞ  የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡት የፀጥታ እና ደኅንነት ኃይሎች ምስጋና አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ጨምሮ በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቀዋል።

ከንቲባዋ ፥ " በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አስተዋፅዖ ላደረጉ የሀይማኖት አባቶች ፣ የከተማው ወጣቶች ፣ ሲያስተባብሩ ለነበሩ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ሳይበግራቸው በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ላደረጉ የጸጥታ ሃይሎችና የከተማው ነዋሪዎች ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና እናቀርበላ " ብለዋል።

#የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋሕዶቤተክርስቲያን
#Ethiopia #AddisAbaba

@tikvahethiopia
#IMF #Ethiopia

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሠራተኞች ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ።

አይኤምኤፍ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ በአራት ዓመታት የሚያቀርበው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን (Extended Credit Facility) በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተደርሷል።

ስምምነቱ በይፋ በዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም ዋና የአመራር ቦርድ ከታየ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ 345 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታገኝ ተገልጿል።

" በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ጨምሮ ኢትዮጵያ አገር በቀል የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጓ በጥሩ ሁኔታ ውጤት እያሳየ ነው " ብሏል ተቋሙ በመግለጫው።

በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ያለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ለመተግበር ውሳኔ አሳልፎ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የመጣው በአልቬሮ ፒሪስ የተመራው የልዑካን ቡድን ሲሆን ከተደረሰው የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በኃላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አልቬሮ ፒሪስ ምን አሉ ?

የአይኤምኤፍ ሠራተኞችና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣኖች ስምምነት በተቋሙ ዋና የአመራር ቦርድ በቀጣይ ሳምንታት የሚታይ ይሆናል።

ቦርዱ ከተመለከተው በኋላ ኢትዮጵያ በመጀመሪያ 345 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች።

የኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ማሻሻያ በተለይም በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ ነው።

ለውጡ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት መጠንን በመጨመር ለአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ነው።

ወደፊት የአገር በቀል ምጣኔ ሃብት ፖለሲ ለውጡ የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋትና የምጣኔ ሃብት እድገት ያመጣል።

የፖሊሲ ማሻሻያው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለውን የፋይናንስ ሥርዓት በመለወጥ የዋጋ ንረትን ያረጋጋል ምጣኔ ሃብታዊ እንዲሁም ማኅበራዊ ጠቀሜታ አለው።

ገቢ መጨመርና በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ ተቋማትን ለማጠናከር የሚደረጉ የፋይናንስ ዘርፍ ለውጦች መንግሥት የሚያወጣውን ወጭ ቅደም ተከተል ለማስተካከልና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ይረዳሉ።

የዓለም የገንዘብ ተቋምን የምጣኔ ሃብት ፕሮግራም በስኬታማነት በማስተግበር ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሊመሰገኑ ይገባል።

በአልቬሮ ፒሪስ እና ቡድናቸው ንግግር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምሕረቱ፣ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እና ከገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ጋር ነው።

መረጃውን IMFን ዋቢ በማረግ ያጋራው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#VisitAmhara

ግሸን ደብረ ከርቤ !

ግሸን ደብረ ከርቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአንጋፋነታቸው ከሚታወቁት ቅዱሳን ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡

የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ሌሎች የገዳሟን ታሪክ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው ወደ ግሸን ይጓዛሉ፡፡

በተለይ ከመስቀል በዓል እስከ መስከረም 21፣ ጥር 21 እንዲሁም መጋቢት 10 ወደ ግሸን የሚጓዘው ሕዝብ በመቶ ሽዎች ይቆጠራል፡፡

በረከት ለማግኘት፣ ታሪክ ለማወቅ እና ለመፈወስ ግሸን ለእምነቱ ተከታዮች ቀዳሚ መዳረሻ ናት፡፡

በኢትዮጵያ የሀይማኖት ቱሪዝም ታሪክ ብዙ እንግዶችን በማስተናገድ ግሸን ከቀዳሚዎች መካከል ትገኛለች፡፡

ነገ መስከረም 21 ታላቁ የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ክብረ በዓል ይከበራል፡፡

እንኳን አደረሳችሁ !

(Vist Amhara)

#TourismAndPeace  #GishenDebreKerbe #SouthWollo #ReligiousFestival #Ethiopia #LandOfOrigins

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እምነት የሚጣልበት ቢሮክራሲና በየጊዜው የማይለወጥ የኢንቨስትመንት ሕግ አተገባበር ተግባራዊ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ምኅዳር ተገማች፣ የተረጋጋና ሥልጡን የሰው ኃይል የሚመራውና የውጭ ባለሀብቶች ሊተማመኑበት የሚያስችል ከባቢ እንዲፈጠር ቻይናውያን ባለሀብቶች አሳስበዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ምኅዳር ውስጥ በፀጥታ ችግር፣ በቢሮክራሲ፣ በብልሹ አሠራርና በሙስና ምክንያት ሥራ መሥራት አልቻልንም የሚል ቅሬታ በብዛት እየተደመጠ መሆኑን ገልጸው፣ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሰናል ያሉት የቻይና ባለሀብቶች ያሉት ችግሮች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

ባለው የኢንቨስትመንት ማነቆ ላይ የፖሊሲ ምክክር በማድረግ በመንግሥትና በባለሀብቶቹ መካከል ድልድይ በመሆን ይሠራል የተባለለት " አፍሪካ – ቻይና ትሬድ ኤንድ ኢንቨስትመንት ፋሲልቴሽን " የተሰኘ አማካሪ ቡድን ይፋ ተደርጓል።

የአማካሪ ቡድኑ መሥራች ቻይናዊው ባለሀብት ጉዋን ሹ ምን አሉ ?

በአገር ውስጥ የተሰማራ አምራች ኩባንያ የሚያመርተው ምርት ብቻ ሳይሆን፣ የሚመረተውን የሚጠቀመው ማኅበረሰብ ለሚቀርብለት ምርት መተማመኛ ይፈልጋል ተብሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ የተረጋጋ የፀጥታ ሁኔታና አስቻይ ፖሊሲ ያስፈልጋል።

ግልጽ የሆኑ መመርያዎች፣ ሊተነበዩና ተግባራዊ መደረግ የሚችሉ የኢንቨስትመንት ሕጎች ያስፈልጋሉ። ሕጎቹ ኢንቨስተሮች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ለአንድና ለሁለት ዓመት ብቻ ሳይሆን ረዘም ላለ ጊዜ መተማመን የሚፈጥር መልኩ ዋስትና መስጠት አለባቸው።

የውጭ ኢንቨስተሮች ሀብታቸውን በሚያፈሱባቸው አካባቢዎች ባሉ አስተዳደሮች ለንብረታቸው የጥበቃ ከለላ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ለንብረታቸው መተማመኛ ያላገኙና የሕጎች አተገባበር መለዋወጥ ያስቸገራቸው ባለሀብቶች ወደ ጎረቤት ኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ ሲሄዱ አይተናል።

በሥራ ላይ ያለው የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ወይም ሕግ ተገማችነቱ በግልጽ መቀመጡ ለኢንቨስተሮች መተማመንን ይፈጥራል። መተማመን ሲፈጠር ባለሀብቶች ባሉበት የመቆየትና ኢንቨስትመንታቸውን የማስፋት አቅማቸው ይጨምራል።

በኢትዮጵያ ያለው የግብር ሥርዓት የኩባንያዎቹን ቁመናና አፈጻጸም ግምት ውስጥ ያላስገባ ከመሆኑም በላይ አሠራሩና አወሳሰኑ ግልጽ አይደለም። በዚህም የተነሳ ኢንቨስተሮች እንዴት እምነት አድሮባቸው ሊሠሩ ይችላሉ ?

መንግሥት በአንድ በኩል የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ የኃይል አቅርቦትና መሠረት ልማት ለማሟላት ሀብት፣ እያፈሰሰ በሌላ በኩል የሚወጡ ሕጎች ይዘት ተገማችነትና አተገባበር፣ እንዲሁም አሠራሮች ከዓላማው ጋር በልኩ ካልተጣጣሙ ሒደቱ ወደኋላ ይጎትታል።

የባለሙያዎቹ ቡድን የተቋቋመው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሱና ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶች፣ በኢንቨስትመንታቸው የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ነው።

አንድ ቻይና ኤምባሲ ዲፕሎማት በኢትዮጵያ በርካታ የቻይና ኩባንያዎች መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ መሆናቸው የታመነበት ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ እየለቀቁ ወደ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ናቸው ብለዋል፡፡

ይህ የሆነው ተገማች ያልሆኑ ሕጎችና ብልሹ አሠራሮች ከቢሮክራሲ ማነቆ ጋር በመደራረባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህንን አሳሳቢ ችግር ለማስተካከል  የምሁራን ቡድኑ ትልቅ ሚና ይጠበቅበታል ብለዋል።

በየካቲት 2016 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ጀምሮ ባለሀብቶች ወደ ሌላ አገር እየተሻገሩ እንደሆነ መስማታቸውን ጠቅሰው፣ ይህ የምሁራን ስብስብ የቻይና ባለሀብቶችን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንም ሊጠቅም ይገባል ብለዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት አባልና የአማካሪ ቡድኑ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አዳሌ ኦዳ ምን አሉ ፤ " የተማሰረተው ዕውቀትን መሠረት ያደረገ ውሳኔ ለማስተላለፍ ዕገዛ የሚያደርግ ቡድን ነው " ብለዋል።

" በቀጣይ ኢንቨስተሮች ሊያጋጥማቸው የሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በማመላከትና የፖሊሲ ማማከር ሥራ በማከናወን ቀጣይነት ያለው የቢዝነስና የንግድ ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ ላይ ጥረት ይደረጋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ባለሀብቶች ተወካይ ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋይናንስ እጥረትና በጦርነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በፀጥታ ችግር የግብር ሥርዓት አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል።

" አንድ ጊዜ ከገቢዎች ቢሮ ስልክ ከተደወለ ተኝቶ ማደር የለም " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" የገቢዎችና የጉምሩክ ሠራተኞች የሚጠቀሙበት ሲስተም በትክክል ለምን አይሠራም ብዬ ስጠይቃቸው አናውቅም ይላሉ፡፡ በዚህ ላይ ሠራተኞቹ የተረጋጉ አለመሆናቸው አሳሳቢ ነው " ብለዋል፡፡

" ምንም እንኳ ትርፍ ለማግኘት ኢትዮጵያ ብንመጣም አብረን ማደግ እንችላለን፣ በየተቋማቱ ያሉ አሠራሮች ግን ይስተካከሉ " ብለዋል።

የማይገመት አሠራርና ተለዋዋጭ የሕግ አተገባበር ትልቅ ማነቆ በመሆኑ መንግሥት ማስተካከያ ያድርግ ሲሉም አሳስበዋል፡፡ #ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia