TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
BBC አማርኛ ~ ስለቴፒ ከተማ ግጭት‼️

በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገለፁ።

ግጭቱን ተከትሎም ጥር 5/2011 ዓ. ም የዓመቱን ትምህርት መስጠት የጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርት #መቋረጡን ተሰምቷል።

ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ግቢ ተማሪ እንዳለው ከትናንት በስቲያ ግጭቱ ሲፈጠር መስጊድ ሰፈር (ባጃጅ ሰፍር) አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ወጣ ብሎ ነበር።

"በድንገት አካባቢው በግርግር ተናወጠ፤ በተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ማን ለማን እንደሚተኩስ አይታወቅም፤ ቀውጢ ተፈጠረ" ይላል።

በወቅቱም እነርሱም ራሳቸውን ለማዳን መንደር ለመንደር እየተሹለከለኩ ወደ ግቢያቸው እንዳመሩ ይናገራል።

በጊዜው በቴፒ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ችግር አጋጥሞ ስለነበር በግቢው ውስጥም ውጥረት ነግሶ ነበር ይላል። ምክንያቱ ምን እንደነበር እርግጠኛ ባይሆንም በከተማው ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ምግብ አብሳዮቹ በሥራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።

አካባቢው #ከተረጋጋም በኋላ በርካታ ቤቶች ወደተቃጠሉበት ስፍራ እንደሄዱና 'ጀምበሬ' እየተባለ የሚጠራው ሰፈር ሙሉ በሙሉ #መውደሙን እንደተመለከተ ተናግሯል።

በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ይህ የዓይን እማኝ እንደሚለው በአካባቢው በየዓመቱ ችግር እንደሚነሳ በማስታወስ አሁንም በግጭቱ ምክንያት ትምህርት #ተቋርጧል

በሚዛን ቴፒ አካባቢ የቆየ የመዋቅር ጥያቄ ነበር የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴፒ ከተማ ነዋሪ እንደገለፁት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በግምት የአንድ ትልቅ ቀበሌ 1/3ኛ የሚሆን ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

"ከዚህ በፊት ቴፒ በሸካ ዞን ሲተዳደር ቆይቷል፤ ሕዝቡ ያንን በመቃወም በዞኑ መተዳደር አንፈልግም የሚል ጥያቄ በማቅረቡ እርሱን ሰበብ ተደርጎ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት አመራ" ይላሉ።

ህዝቡ የተለያየ ኮሚቴ አዋቅሮ ለጥያቄው መልስ ለማግኘት እየተጠባበቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባልታሰበ ሁኔታ ሌሊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድንጋይ በመወራወር ተጀምሮ በመንገድ ዳር ያሉ የሚከራዩ ቤቶችን #በማቃጠል ነው የተጀመረው።

ጥቃቱ ቀን ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ሌሊት ከ9:00 ሰዓት በኋላ በርካታ ቤቶች እንደተቃጠሉና ንጋት ላይ ወደ #ጫካ ሸሽተው የነበሩት የሰፈሩ ነዋሪዎች ደርሰው ለማጥፋት ሲሞክሩ እንደነበር ይናገራሉ።

ሰዎች በተኙበት ቤቶችና መጋዘኖች ተቃጥለዋል፤ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል የሚሉት መምህሩ፤ "በወቅቱ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ እርስ በርስ እየተጠራሩ ወደ ጫካ ሸሹ፤ ይሁን እንጂ አዛውንቱ የጓደኛዬ አባት አገር ሰላም ብለው በተኙበት በስለት ተገድለዋል" ይላሉ።
"የእኔ ቤተሰቦች ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ቤታቸው ወድሟል" ሲሉ በሃዘን ይገልፃሉ።

ትናንት በቴፒ ከተማ በየመንገዱ ላይ የሚቃጠሉ የመኪና ጎማዎች፤ በቁጣ የተነሱ ወጣቶችና ነበር የሚታየው፤ የተኩስ ድምፅም ይሰማ ነበር።

በአንፃሩ ዛሬ የከተማው ነዋሪዎች በግጭቱ የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር በተለያየ ቦታ ተበታትነው ስለሚገኙ በአንፃሩ #መረጋጋት ይታይበታል ብለዋል።

በወቅቱ ሕዝቡ የፀጥታ ኃይሎች #ጣልቃ ይገባሉ ብሎ ቢጠባበቅም ግጭቱን ለማስቆም ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ጉዳት መድረሱንና ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ከስፍራው መድረሳቸውን ተናግረዋል።

መምህሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ግጭት ምክንያት በቴፒ ካምፓስ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን ይገልፃሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሁለት ግቢዎች ውጥረትና ስጋት ይታያል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳረ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው #ራስን_በራስ የማስተዳደር የቆየ ጥያቄ ቢኖርም የአሁኑ ግጭት መነሻ ግን ተቋርጦ የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር ነው ይላሉ።

አስተዳዳሪው እንዳሉት በግጭቱ 7 ሰዎች ሲሞቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የፌደራል፣ የክልልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው #ፀጥታ ለማስፈን እየሰሩ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፖሊስ ስለ ወ/ሪት ፀጋ በላቸው ምን አለ ? " ከጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር አውያለሁ " - የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በፀጋ በላቸው ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል። ፖሊስ በመግለጫው " የከተማች ነዋሪ በሆነችው ወ/ሪት ፀጋ በላቸው ላይ የደረሰባት የጠለፋ ወንጀል ጉዳዩን አስመልክተው ቤተሰቦቿ በእለቱ ለመናኸሪያ ፖሊስ በመቅረብ አቤቱታቸውን አሰምተዋል " ብሏል።…
ፀጋ ወደ ቤተሰቦቿ ብትመለስም አጋቿ ግን አልተያዘም።

ፀጋ በላቸው ከቀናት በኃላ ከታገተችበት ነፃ ወጥታ ከቤተሰቦቿ ጋር መቀላቀሏን ለማወቅ ተችሏል።

የቅርብ ቤተሰቧ እንደሆኑ የገለፁልን የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ ፀጋ በላቸው በህይወት መገኘቷን እና ከቤተሰቦቿ ጋር መቀላቀሏን በመግለፅ ድምፅ ለሆኑ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለማህበራዊ ሚዲያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

የፀጋ በላቸውን ነፃ መሆን የከተማው አስተዳደርም ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የከተማው ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ፤ በተቀናጀ ኦፕሬሽን ነፃ ወጥታ ወደ ሀዋሳ በሰላም ገብታለች ብለዋል።

ከንቲባው ፀጋ በላቸውን ያፈናት ተጠርጣሪ ግለሰብ አለመያዙን አመልክተው ፤ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፀጥታ ኃይሎች ርብርብ እያደረጉ ነው ብለዋል።

ግለሰቡ ተይዞ ለፍርድ እንደሚቀርብ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የሲዳማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በሰጠው መግለጫ ደግሞ ተጠርጣሪው ግለሰብ ወደ #ጫካ መግባቱ በመግለፅ ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ብሏል።

ፀጋ በላቸው ፤ ግንቦት 15 ቀን 2015 ከስራ ስትወጣ በወቅቱ የከተማው ከንቲባ የግል ጠባቂ በነበረው ግለሰብ ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም በመኪና ታግታ መወሰዷና አድራሻዋም ሳይታወቅ በመቅረቱ ቤተሰቦችን ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ጥሎ ነበር።

@tikvahethiopia