TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ስለ ጉራጌ ዞን ከDW⬇️

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በምትገኘው ኢንሴኖ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት #በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ተናገሩ። የአይን ዕማኝነታቸውን ለDW የሰጡ የአካባቢው ነዋሪ የማረቆ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌዎች ወደ መስቃን ወረዳ መካከላቸውን በመቃወም ከትናንት በስቲያ ሐሙስ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ሞተዋል። አንድ የአካባቢው ባለስልጣንም ግጭት #መፈጠሩን እና ሰዎች #መሞታቸውን አረጋግጠዋል። 

በማረቆ ወረዳ ቆሼ ከተማ የሚኖሩ የአይን ዕማኝ በሰዎች ላይ ጥቃት ሲፈጸም፣ የመኖሪያ ቤቶች #ሲቃጠሉ መመልከታቸውን አስረድተዋል። "ጥቃቱን ለማስቆም ብንሞክርም አልተሳካልንም" ያሉት የአይን እማኙ "በሁለት ቀናት ሐሙስ እና አርብ ግፋ ቢል #ከ20 ያላነሰ ሰው ሞቷል። በማረቆ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ የሟቾችን አስከሬን አሁን አንቡላንስ እየሰበሰበው ይገኛል። ግማሹ በወራጅ ወሐም ተወርውሯል" ሲሉ አስረድተዋል።

የማረቆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በለጠ ደራሮ ግጭቱ "የግል ፍላጎት ባላቸው አካላት እንደተቀሰቀሰ" ተናግረዋል። ግጭቱ "በመስቃን እና በማረቆ" መካከል የተፈጠረ አይደለም ያሉት አቶ በለጠ "መነሻው አልገባንም" ሲሉ ለDW አስረድተዋል። "በሰውም ላይም ጉዳት ደርሷል። በንብረትም ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል። በማረቆ አካባቢ በርካታ መስቃኖች አሉ። ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም። ሽማግሌዎቹ፤ አመራሮቹ እነሱን መንካት እኛን መንካት ነው። እነሱ አልበደሉንም በስመ መስቃን ማንም መነካት የለበትም በሚል በትክክል ሐብቱ የሰው ማንነቱ ተከብሮ የመስቃን ተወላጅ ምንም አልተደረገም። የማረቆ ተወላጅ ግን መስቃን ውስጥ ጥቃት እየደረሰበት ነው። በንብረቱም ላይ በሕይወቱም ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰበት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ የተጠየቁት አቶ በለጠ "ይኸን ያህል የሚል የለንም። እየለየን ነው ያለንው" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ በለጠ "የመንግሥት አካላት ሰራዊት በመላክ ጉዳዩ እየረገበ ነው። ልዩ ኃይሎችም አሉ። መከላከያዎችም አሉ። እነዚህ ንብረትም ሕይወትም የማዳን ሥራ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ከህዝቡ ጎን በመቆም ከዱርየው ጥቃት ሕዝቡን እያዳኑ ነው ያሉት" ሲሉ አክለዋል።

የቆሼው ከተማ ነዋሪ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የጸጥታ አስከባሪዎች በአካባቢው መሰማራታቸውን ገልጸዋል። "የጸጥታ አስከባሪዎች ወደ ቦታው ከተሰማሩ በኋላ የሰው ሕይወት እየጠፋ አይደለም" ያሉት አቶ በለጠ በበኩላቸው ውጥረቱ አሁንም እንዳልረገበ አስረድተዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰባት #የኢንሴኖ ከተማ ከአዲስ አበባ በ211 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ቡታጅራ አቅራቢያ ትገኛለች። በጉራጌ ዞን ሥር የሚገኙት መስቃን እና ማረቆ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአንድ ወረዳ ሥር ይተዳደሩ ነበር።

©የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia