TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ችግሮች መፍታት የሚቻል ከሆነ በፍጥነት ቢፈቱ እና ህዝቡ ወደ ቀድሞው ኑሮው እንዲመለስ ቢደረግ መልካም " - የቲክቫህ አባላት

ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በክልሉ ላለው ችግር እካሁን ይሄ የሚባል መፍትሄ ባለመምጣቱ ህዝቡ ስቃዩ እየተራዘመ ነው ብለዋል።

በቅርብ ሳምንት የታዩት በጎ ነገሮች መልካም ቢሆንም በፍጥነት ወደ ታች ወርዶ በችግር ላይ ያለውን ህዝብ መታደግ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።

ነዋሪዎች ባለፉት በርካታ ወራት ፦
👉 ያለ ባንክ፣
👉 ያለ ስልክ፣
👉 ያለ ትራንስፖርት ፣
👉 ያለ የንግድ ልውውጥ፣
👉 ያለ ስራ፣
👉 ያለ ትምህርት
👉 ከምንም በላይ ደግሞ ያለ በቂ ህክምና ላይ ነው የሚገኙት ይህን ለአንድ ቀን እንኳን ለማሰብ የሚከብድ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ያሉት ችግሮች የሚፈቱበት አግባብ ቢፋጠን ፤ ዜጎችም ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ቢደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

ለበርካታ ወራት ባለው ሁኔታ ምንም ፖለቲካ የማያውቁ ፣ ስላለው ሁኔታ በቅጡ የማይረዱ እጅግ ብዙ ሰዎች አብረው የችግሩ ገፈጥ ቀማሽ ሆነዋል፤ ሌላው ቢቀር ለትንንሽ ህፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ተብሎ ፈጣን መፍትሄ ቢፈግ ሲሉም ተማፅነዋል።

በተለይም ፤ ከባንክ አለመኖር ጋር በተያያዘ ብዙ ችግር መከሰት ከጀመረ ወራት መቆጠሩንና ይህም ችግር ለማንም ግልፅ እንደሆነ አንስተዋል።

መልዕክታቸውን ከላኩ ቤተሰቦቻችን አንዱ " ቤተሰቦቼ የሚኖሩት ትግራይ ክልል ነው። ታድያ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ላይ ባንኮች አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ምክንያት ህዝቡ በብዙ ችግሮች ውስጥ እየኖር ነው " ብሏል።

አክሎም ፤ " ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በአቋራጭ መበልፅግ የሚፈልጉ እራስ ወዳዶች ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቤተሰቦቹ ብር መላክ ከሚፈልግ ሰው አላማጣ ላይ ባሉት ሰዎቻቸው ሆነው አዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ መቀመጫቸውን ካደረጉ ግለሰቦች እስከ 50 በመቶ ማስላክያ ክፍያ በመቁረጥ ከሚልከውና ከሚቀበለው ህዝብ እየዘረፉ ይገኛል " ሲል አስረድቷል።

በዚህ ላይ አስፈላጊውን እርምት ሊወሰድ እንደሚገባና በአፋጣኝ በትግራይ የባንክ አገልግሎት እንዲጀመር ሊደረግ ይገባል ሲል ጠይቋል።

በትግራይ ፤ በብር እጦት ምክንያት ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ምንም የማያውቁ ንፁሃን እየሞቱ እና እየተንገላቱ ነውና ፈጣን መፍትሄ ያስፈልጋል ብሏል።

ከዚህ ቀደም የቤተሰቦቻችን አባላት ፤ በክልሉ ውስጥ ስላለው ሁኔታ በተደጋጋሚ መግለፃቸው እና በተለይ በተለይ ለ #ህፃናት#ሴቶች እንዲሁም #አረጋዊያን ካለው ችግር እንዲወጡ ፈጣን መፍትሄ እንዲፈለግ መማፀናቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia