TIKVAH-ETHIOPIA
የቤት ኪራይ ጉዳይ . . . የነዋሪዎች ድምፅ ! በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ…
" የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህ ቃለ ምልልስ ወቅትም ፤ ስለ " ጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከግብር ጋር በተያያዘም የቤት ኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ የቤት ኪራይ የመጨመርን ጉዳይ " #ስግብግብነት " ነው ብለዋል።
" [የኪራይ ጭማሪ] ምክንያት ፈልጎ ማህበረሰቡን የማስጨነቅ ሂደት ነው፤ ይሄ መታረም አለበት፤ የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም። ይሄን ማረጋገጥ እንችላለን። " ብለዋል።
አሁን እንዲከፈል የተባለው ግብርም ፤ " ከ45 ዓመት በፊት የነበረን ተመን ምናልባት ወደ ዛሬ 25 ዓመት በፊት ነው ያመጣነው ፤ አሁን የሚከፈለው ክፍያ መከፈል የነበረበት የዛሬ 25 ዓመት ነው ወደዛሬው ዋጋ መጠን እንኳን አላመጣነውም ፤ በአንድ ጊዜ ይከብዳል ብለን " ያሉት ከንቲባዋ ፤ " 50 ፐርሰንት ያለው ለዚህ ነው ፤ የመኖሪያ ቤት የተመኑን 50 ፐርሰንት ብቻ ክፈል ፤ መስሪያ ቤቶች እና ቢዝነስ ተቋማት 75 ፐርሰንት ብቻ ክፈል ያልነው ጫና እንዳይሳድር ነው ፤ ስለዚ በምን ምክንያት ነው የተለየ ግብር የከፈሉት ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" አሁን የቤት ኪራይ እየጨመሩ ያሉት የግብር ስርዓቱ ውስጥ የሉም ፤ ኪራይ የሚጨምሩት የቤት ግብር እየከፈሉ አይደለም ፤ ከ800 ሺህ ውስጥ በጥቅሉ አሁን ከውሳኔው በኃላ የተጨመሩት 90 ሺህ ስንጨምር ወደ 200 ሺህ ያክል ብቻ ነው እየከፈለ ያለው 600 ሺው የለም እኮ፤ ስርዓቱ ውስጥ ድሮም አልነበረም ፤ ዛሬም የለም አሁንም አልገባም እንዴት ነው የቤት ኪራይ የሚጨምረው ? ይሄ የስግብግብነት መግለጫ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች ፤ " አስተዳደሩ ለሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ መመሪያ አስተላልፈናል ፤ ማህበረሰቡ አቤቱታ ሰሚ የሚባል ክፍል ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ውስጥ አለ የተጨመረባቸው ግብር ከነመስሪያ ቤቱ ከነውላቸው ያስመዝግቡልን ፤ ውል ግዴታ አይደለም የተጨመረባቸው ግብር መነሻ እውነት መሆኑን የሚያሳይ መረጃ / የከፈሉበትን ድሮ እና አሁን የሚከፍሉትን እንዲከፍሉ የታዘዙትን ስንት ነው የሚለውን በአቤቱታ መልክ ያስገቡን ይሄን መነሻ አድርገን ህግ እና ስርዓት እንዲከበር ስራ እንሰራለን " ሲሉ አሳውቀዋል።
" ግብሩን እየከፈለ ያለው ዝቅተኛው ማህበረሰብ ነው ፤ የቤት ኪራይ የሚጨመርበትም እሱ ላይ ነው ጨማሪው የተሻለ ገቢ ያለው ነው ግብር የማይከፍለውም የተሻለ ገቢ ያለው ነው ከዚህ በላይ ኢፍትሃዊነት ምን አለ ? እንደ መንግሥት ይሄን የማስተካከል ግዴታ አለብን ግዴታችንን ለመወጣት ጥረት እናደርጋለን " ሲሉ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia