TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አምባሳደር #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአሜሪካ ኢምባሲ የደስታ መግለጫ አስተላለፈ፡፡ ያለ #ሴቶች ተሳትፎ አንድ ማህበረሰብ #ውጤታማ እንደማይሆን የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግስት ሴቶችን ወደ ሃላፊነት ማምጣቱ ሊያስመሰግነው ይገባል ብሏል የአሜሪካ ኢምባሲ በመግለጫው፡፡ መንግስት ሴቶችን ያቀፈ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰዱ ኢምባሲው #አድናቆቱን ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው መመረጣቸው ለአህጉር ጥሩ ዜና እንደሆነ የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር #ሙሳ_ፋኪ ተናገሩ። ሚስተር ፋኪ ዛሬ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም አጀንዳ
2063 በተሰኘው የአፍሪካ ህብረት የልማት መርሃ ግብር ትግበራ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዚዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የምትገኘውን የአሜሪካውን ፕሬዝደንት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕን አነጋግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር!

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በአሁን ሰዓት የቀይ መስቀልን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።

Via Mandefro Negash/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዘውዲቱ_ሆስፒታል

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በመገኘት የኩላሊት ሕሙማንን ጎብኝተዋል፡፡ እንደ ኢቢሲ ዘገባ በዘውዲቱ ሆስፒታል በቅናሽ እና በነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየተደረገላቸው ያሉ ሕሙማን ይገኛሉ። የኩላሊት እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ከባንኮች እና ከተለያዩ አካላት ገቢ በማሰባሰብ በዘውዲቱ እና በምኒልክ ሆስፒታሎች ለ93 ሕሙማን በነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን የትብብር መስኮች የማስፋት ፍላጎት እንዳላት ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ ገለጹ። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ኢትዮጵያና ኳታር በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ጠንካራ የሚባል ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በተለያዩ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን #የመግባቢያ ሰነዶች መፈራረማቸውም ይታወቃል። ኢትዮጵያም ከኳታር ጋር ያላትን የግንኙነት መስኮች የማስፋት ፍላጎት አሳይታለች።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሳህለወርቅ_ዘውዴ

“ አቅጣጫዬን አሳይቻለሁ፤ በዛ መሠረት ለመስራት ሞክሬአለሁ ” - የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

በበጎ ፈቃድ የተሰባሰቡ ሴቶችና የሴት መሪ ድርጅቶች በጋራ በመሆን በቅርቡ የሥራ ዘመናቸውን ላጠናቀቁት ለቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሸራተን አዲስ ሆቴል ዛሬ የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጅተው ነበር።

በዚሁ መርሀ ግብር አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ፣ የሴቶች ማኀበራት መሪዎችና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ ሴቶች ተገኝተዋል።

ፕሮግራሙ ከተዘጋጀበት ዓላማ አኳያም ለቀድሞ ፕሬዜዳንቷ “ በጣም ውድ ” እና “ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ” የተባለለት የሀገር ቅርስ ጭምር የተቀረጸበት የስዕል ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ “ ከሚገባው ቦታ አስቀምጠዋለሁ ” በማለት ስጦታውን ላበረከቱላቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣ “ የዛሬ 6 ዓመት ገደማ ያደረኩት ንግግር የ18 ደቂቃ ነበር። ጥቂት ጊዜ ነው የነበረኝ ለመዘጋጀት። የደረሰብኝም አልገባኝም ነበር ” ሲሉ አስተውሰዋል የቀድሞ ፕሬዜዳንቷ።

“ ሴቶች የሚለውን ቃል 29 ጊዜ፣ ሰላም የሚውን ቃል 30 ጊዜ ተናግሬ ነበር ” ያሉት ሳህለወርቅ፣ “ ለራሴ አልዋሽም፣ ለሌላም አልዋሽም። አቅጣጫዬን አሳይቻለሁ፣ በዛ መሠረት ለመስራት ሞክሬአለሁ ” ሲሉም አክለዋል።

“ ተያይዘን መስራት አለብን። ጡረታ የሚባለውን ነገር አሁን ነው የጀመርኩት ግን እረፍት የለም። ጡረታም ተወጥቶ እንደማይታረፍ የቀደሙኝ እያሳዩኝ ነው። ላደረጋችሁልኝ በጣም ነው የማመሰግነው ” ነው ያሉት።

የቀድሞዋ ፕሬዜዳንት ከዚህ ቀደም፣ “ ‘የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው’ ይላል ማህሙድ ‘ዝምታ ነው መልሴ’ን ሲያዜም ” ብለው፣ “ አንድ ዓመት ሞከርኩ ” የሚል ፅሑፍ በX (ቲዊተር) ገጻቸው አጋርተው ነበር።

በወቅቱም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ይህንን ምስጢር አዘል የሆነ ፅሑፋቸውን በተመለከተ ግን ዛሬም የሰጡት ማብራሪያ የለም።

የቀድሞዋ ፕሬዜዳንት ሳልለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሆነው ለ6 ዓመታት 4ኛ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው፣ የሥልጣን ዘመናቸው በመጠናቀቁ ኃላፊነታቸውን ለፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ማስረከባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia