TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia, #GujiZone📍

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን 5 ወረዳዎች በከፊል እና ሙሉ በሙሉ በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጀው ኦነግ ሸኔ/እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራው ታጣቂ ኃይል ቁጥጥር ስር መሆኑን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

ታጣቂዎቹ የተቆጣጠሯቸው አከባቢዎች ፦

- አርሶ አደር ማምረት አቁሟል።
- ሰዎች ለተለያዩ እንግልትና ሰቆቃ ይዳረጋሉ።
- የማህበራዊ አገልግሎትና የመንግስት ስራም በሙሉ ተቋርጧል።
- ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል።
- ጤና ጣቢያዎችም አገልግሎት አይሰጡም።

በጉጂ ዞን የጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ ነዋሪ ሳራ ጅብቻ ፦

" ... ጉሚ ኤልዳሎ በሸማቂዎቹ ስር ከገባች አራተኛ ወር እያስቆጠረ ነው፡፡

እኛ ለዓመታት በጦርነት ውስጥ ነው ያሳለፍነው፡፡ አሁንም ሰላም እንደራቀን ነው፡፡ ባንድ በኩል ድርቅ በሌላው ደግሞ ግጭት ጦርነቱ እያሳደደን ግራ በተጋባ ህይወት ውስጥ ነን፡፡

ድርቁ ከብቶቻችንን እየገደ ለርሃብ ሲዳርገን፣ የፀጥታ ችግሩ ደግሞ ትራንስፖርት እንኳ እንዳይኖር በማድረግ የተራቡት ለሞት እየዳረገ ነው፡፡

ሰው በርሃብም በጥይትም በየቀኑ ነው የሚሞተው፡፡ ስቃይ ውስጥ ነን፡፡ "

የዋደራ ከተማ ነዋሪ (ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ)፦

" ... ካለሁበት ከተማ ውጪ ያሉ በርካታ የገጠር ቀበሌዎች በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ናቸው።

ይህቺ ከተማ ዙሪያዋ በድን የተከበበ ነው፡፡ 3 እና 5 ኪሎ ሜትር ወጣ ብትል እንኳ ታጣቂዎች ተሰግስገውበታል፡፡ ከዚህ ከተማ ሰው በየትኛውም አቅጣጫ ስወጣ እያገቱ ብር ይለቅማሉ፡፡

ሰው ያለውን ሁሉ ይዘረፋል፡፡ ከገጠር ቀበሌዎችም እየተነሱ ይሄው ወደ ከተማዋ እየተሰደዱ ነው፡፡ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሲወጡ በቦታው አያገኙዋቸውም፡፡ ከመንግስት አቅም በላይ ሆኗል ለማለትም ሆነ መንግስት አከባቢውን እያስተዳደረ ነው ለማለት ተቸግረናል። ”

የጉጂ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ዮሓንስ ኦልኮ ፦

" በዞኑ 5 ወረዳዎች በከፊል እና ሙሉ በሙሉ በታጣቂዎች እጅ ስር በመውደቃቸው ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ተከስቷል፡፡ ሰው በቁም ከመቀበር ጀምሮ በነዚህ አምስት ወረዳዎች አስከፊ የሆኑ ሰቆቃዎች በህብረተሰቡ ላይ ይፈጸማል፡፡ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚሰሩ ይገደላሉ፤ ተቋማቱም ይዘረፋሉ ሰዎች እየታገቱ ብር የሚጠየቅባቸው ብዙ ናቸው "

ያንብቡ : https://telegra.ph/DW-02-25

@tikvahethiopia
#GujiZone

• " እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ባለው ጊዜ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ቁጥሩ ግን ሊጨምር ይችላል " - የሰባ ቦሩ ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ

• " የሞቱት ዜጎች ምናልባት በፀጥታ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል " - የጉጂ ዞን ኮሚኒኬሽን

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን ፤ ሰባ ቦሩ ወረዳ በድርቅ ምክንያት የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀ።

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን በሰባ ቦሩ ወረዳ ረሃብ ተከስቶ 12 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቢሮው፤ እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ባለው ጊዜ ብቻ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጾ ቁጥሩ ግን ሊጨምር እንደሚችል አሳውቋል።

በወረዳው 35,442 ዜጎች አስቸኳይ ምግብ እርዳት ያስፈልጋቸዋል የተባለ ሲሆን እነዚህ ዜጎች በንሳ ፣ በደጋላልቻ ፣ ሰባሎሌማሞ ፣ በኡቱሉ፣ ኦዴ ፣ ሀራጌሳ ቀበሌዎች ያሉ ናቸው ተብሏል።

የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት መኮና ሀጤሳ ፤ ለወረዳው አልፎ አልፎ የምግብ እርዳታ ቢመጣም ምግብ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጋር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል።

በወረዳው የሟቾች ቁጥር በየቀኑ #እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 2 ወራት የምግብ እና መሰል እርዳታቸዎች መቋረጣቸው ማህበረሰሙ ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጡን ገልፀዋል።

የጉጂ ዞን የኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ ፤ በዞኑ ቆላማ አካባቢዎች 5 ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል ብሏል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኦልኮ፤ " በረሃብ ምክንያት ስለሞቱ ሰዎች መረጃ የለኝም " ብለዋል። ነገር ግን " በአካባቢው የፀጥታ ችግር አለ " ሲሉ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Guji-Zone-08-04

@tikvahethiopia