ጉድ ሳይሰማ...
በሁለት ወር ውስጥ #በማስትሬት ዲግሪ የሚያስመርቁ የግል ኮሌጆች ተገኙ። ኢትዮጵያ ውስጥ በሁለት ወር ትምህርት በማስትሬት ዲግሪ ሲያስመርቁ የነበሩ ኮሌጆች መገኝታቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሃገሪቱ ካሉ 174 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ 46ቱ ላይ ከፍተኛ ችግር ተገኝቷል ፤ ህጋዊ ሰነድ አሟልተው በመስራት ላይ የሚገኙትም 43ቱ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድንገተኛ ፍተሻ አድርጌ ነበር ያለው ሚንስቴሩ በፍተሻዪም ያለ እውቅና ፍቃድ ተማሪ መዝግበው የሚያስተምሩ፣ #የርቀት ትምህርት ፍቃድ ወስደው መደበኛ ትምህርት የሚያስተምሩ፣ ሳያሳውቁ የካምፓስ ህንፃ የሚቀይሩ፣ ኮሌጅ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ብለው የሚያስተምሩ ኮሌጆችን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡
ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#MoE
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
መውጫ ፈተና በሁሉም መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሀግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትና ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል።
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ ተማሪዎች ባሻገር #የማታና #የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን እንደሚመለከት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለመንግስትና ለግል ዩኒቨርስቲዎች የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ሲከፍቱ እንዳሉት መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣የማታና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት መታቀዱንም ዶክተር ሳሙኤል ጠቁመዋል።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር ) በዚሁ ጊዜ ሲናገሩ የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር የተማሪዎችንና የተቋማቱን ብቃት ለማሳደግ እንደሚያስችል ጠቁመዋል።
በምክክር መድረኩ ሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገኝተዋል።
በምክክር መድረኩም በመውጫ ፈተና ዙሪያ እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ፣ የመሠረተ ልማትና የ2015 ምሩቃን መረጃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopia