TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የስራ ማቆም አድማ⬆️

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን በመጠየቅ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም #አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰራተኞቹ ለኢቢሲ በስልክ እንደገለፁት በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው #ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ፣ የሰራተኛ አያያዝ ችግር፣ የሰራተኞች ምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ መናር የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ወ/ኪዳን ሰራተኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ለአቢሲ አረጋግጠዋል፡፡

ሰራተኞቹ ያቀረቡትን ችግር ለመፍታት ውይይቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

ከሰዓት በኃላ የግንባታ ተቋራጩን ጨምሮ በሚደረግ የጋራ ውይይት ችግሩ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጨዋ ሰራዊት ነው...

"ለደንብ ልብስ #ክፍያ የሚፈጽም ጨዋ ሠራዊት ነው!! የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የሚለብሱትን የደንብ ልብስ ሲያገኙ የነበረው በክፍያ ነበር ያውቃሉ ? አንድ የሠራዊቱ አባል የተሟላ የደንብ ልብስ ለማግኘት 900 ብር መክፈል ይጠበቅበት ነበር። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የወር ደሞዝ እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ ሳለ ወታደራዊ የደንብ ልብሱን ለማሟላት ከደሞዙ ላይ ቆርጦ ይገዛ ነበር። ከዘንድሮው ዓመት ጀምሮ ግን ይህ እንዲቀር ተወስኖ ወታደራዊ የደንብ ልብሱን መንግስት በነፃ ማቅረብ ጀምሯል። እና ምን ለማለት ነው ?የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገሪቱ ከፍ እና ዝቅ ባለችባቸው ጊዜያት በሙሉ በታላቅ ሀላፊነት ረግቶ የተቀመጠ ስነ ስርዓት ያለው ሰራዊት ነው ፤ ክብር ይገባዋል ሲባል ተረት ተረት አይደለም። እናም ለሠራዊቱ ከፍ ያለ ክብር ይገባል ፣ በተለይም ተራው የሠራዊቱን አባላት ሳስብ የበለጠ ከፍ ያለ ክብር እሰጣለው።" #YohannesAnberbir

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላጆች ልጆቻችሁን አስመዝግቡ!

የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅበላ ጳጉሜ አምስት ድረስ ብቻ የሚከናወን ስለሆነ በሀዋሳ ከተማ የምትገኙና ልጆቻችሁን ትምህርት ቤት ያላስመዘገባችሁ አስመዝግቡ። በሁሉም የመንግስት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ምንም ዓይነት #ክፍያ አይጠየቅም።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
' የትምህር ቤት ክፍያ ' የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2015 የትምህርት ዘመንን የክፍያ ጭማሪ አስመልክቶ ከትምህርት ቤቶች ጋር ምክክር አድርጎ ነበር። በዚህም ፥ በ2014 ዓ/ም ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል። ነገር ግን ላለፉት 2 እና 3 አመታት ጭማሪ ሳያደርጉ የቆዩ ትምህርት ቤቶች…
#ክፍያ

የአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በቀጣይ የትምህርት ዘመን (2015 ዓ/ም) ክፍያ መጨመር የሚችሉት የግል ትምህርት ቤቶች መለየታቸውን እና ጭማሪውም ከወላጆች ጋር መክረው የሚያደርጉት መሆኑን አስታውቋል።

ጭማሪ ማድረግ የሚችሉ ት/ቤቶች በ2014 ዓ/ም ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ያላደረጉ ናቸው።

የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ህይወት ጉግሳ ጉዳዩን ከተመለከተ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል፥ " ጭማሪ ማድረግ የሚችሉት በ2014 ምንም አይነት ጭማሪ ያላደረጉ ብቻ ናቸው። ጭማር ማድረግ ይችላሉ ሲባል ደግሞ ቀጥታ ይጨምራሉ ማለት ሳይሆን ከወላጆች ጋር መክረው / ከወላጅ ኮሚቴ ጋር መክረው ሲተማመኑ ነው " ብለዋል።

ወ/ሮ ህይወት ጭማሪ የሚደረገው ክፍያ ተፈፃሚ የሚሆነው ወላጆች እና የወልጅ ኮሚቴ ያመነበት ብቻ እንደሆነም አክለዋል።

ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ባይስማሙ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ጣልቃ ገብቶ ሁለቱን አካላት የማግባባት ስራ የሚሰራ ሲሆን መንግስት ያስቀመጠውን መመሪያ ሳይከተል ወላጆች ያልተስማሙበት ወርሃዊ ክፍያ እጨምራለሁ የሚል ትምህርት ቤት ካለ እውቅና ፍቃዱ ይሰረዛል ፤ ትምህርት ቤቱ ይታሸጋል ለዚህም የተዘጋጀ በቂ መመሪያ መኖሩን የአዲስ አበባ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

በሌላ በኩል፤ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከተማሪ ወላጆች ጋር ምክክር ለማድረግ ቀድመው ቀጠሮ የያዙ ሲሆን ሁሉም ወላጆች በት/ቤት ተገኝተው የተማሪዎች መመዝገቢያ እና የወርሃዊ ክፍያ ላይ በንቃት ተሳትፈው የጋራ ውሰኔ እንዲያሳልፉ የከተማው ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጥሪ ማቅረቡን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ኮንስትራክሽን

አስገዳጁ ረቂቅ አዋጅ . . .

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ ትላልቅ #ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ #የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ረቂቁ በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ እንደሚገመገም ተገልጿል።

ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #እንዲጸድቅ ሲደረግ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም በአገሪቱ የሚገኙ ትላልቅና ዋና ዋና ተቋራጮች ከአነስተኛ ትናንሽ ተቋራጮች በጥምረት እንዲሠሩ ዕድሉን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ረቂቅ ህጉን #በአስገዳጅነት እንዲዘጋጅ የተደረገው አነስተኛ አቅም ያላቸው ተቋራጮች ሰፊ ልምድና አቅም ካላቸው ተቋራጮች ጋር በመሥራት ልምድ እንዲያገኙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በማሰብ ነው ተብሏል።

አነስተኛ ደረጃ ያላቸው ተቋራጮች ያልተገባ ተግባር ሲፈጽሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና #ክፍያ ላይም ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያስችል ሕግ መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁን በማርቀቅ ሂደት ፦
- የሕንፃ አማካሪ ድርጅቶች፤
- የሕንፃ ተቋራጭ ማህበራት፤
- በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፤
- ፕሮጀክት ያላቸው አካላት፤
- የገንዘብ ሚኒስቴር፤
- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደተሳተፉበት ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ አነስተኛ ደረጃ ያላቸው የግንባታ ተቋራጮች እራሳቸውን ብቁ አድርገው መንግሥት በሚያሰማራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ድርሻ ይዘው ለመሥራት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia
አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።

አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።

ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።

አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/

አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia