TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GudafTsegay

ጉዳፍ ፀጋይ ሪከርድ በመስበር ወድድሯን በበላይነት አጠናቀቀች።

በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 3:53.09 በሆነ ደቂቃ በመግባት የ1,500 ሪከርድን (WR) በመስበር ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች።

#GudafTsegay❤️#Ethiopia

@tikvahethsport @tikvahethiopia
#GudafTsegay🇪🇹

የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ሪከርድ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።

በዩጂን በተደረገ የ " ዳይመንድ ሊግ " ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የ5,000ሜ የዓለም ሪከርድን በመስበር አሸንፋለች።

14:00.21 በሆነ ሰዓት የገባችው ጉዳፍ ፀጋይ የዓለም ሪከርዱን ከኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን በመንጠቅ ሪከርዱን የግሏ ማድረግ ችላለች።

" ትኩረቴ የነበረው የዓለም ሪከርዱን መስበር ነበር "  ያለችው ጉዳፍ በተመዘገበው ድል በጣም ደስተኛ መሆኗን እና በቀጣይ ከአስራ አራት ደቂቃ በታች ለመግባት እንደምትጥር ከድሉ በኋላ ተናግራለች።

ጉዳፍ ያሸነፈችበትን ውድድር ቪድዮ " X " ላይ መመልከት ይቻላል 👇
https://twitter.com/tikvahethiopia/status/1703549856315240553?t=Pmq3yq4O_vIS4WWyatvJGw&s=19

Video Credit - Lynne Wachira / RTS TV

Via @tikvahethsport    
#GudafTsegay #TigistAssefa

የዓለም አትሌቲክስ የአመቱ ምርጥ ሴት አትሌት ዘርፍ የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ተደርገው ድምፅ እየተሰጠ ይገኛል።

ሁለት #ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከምርጥ አስራ አንድ እጩዎች ውስጥ ይገኙበታል።

እጩዎቹም ፤ በቅርቡ የአለም የማራቶን ሪከርድን መስበር የቻለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ትዕግስት አሰፋ እንዲሁም የ5000ሜ የዓለም ክብረወሰን የሰበረችው ጉዳፍ ፀጋይ ናቸው።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ አመት የ5000 ሜትር የአለም ክብረወሰን ከመስበሯም በተጨማሪ የ10,000ሜ የዓለም ሻምፒዮን እንደነበረች ይታወሳል።

ምርጫው እንዴት ይካሄዳል ?

የዓለም አትሌቲክስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የአሸናፊዎች ምርጫ ለዓለም አትሌቲክስ ኮሚቴ እና ለዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፅ በኢሜል መስጠት እንደሚቻል ተገልጿል።

ደጋፊዎች እንዴት መምረጥ ይችላሉ ?

ሁሉም የአትሌቲክስ ደጋፊዎች የሚመርጧቸውን አትሌቶች ፎቶ በአለም አትሌቲክስ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በመፈለግ በፌስቡክ ፣ ዩቲዩብ እና ኢንስታግራም ላይክ በማድረግ እንዲሁም በ " X " ሪፖስት በማድረግ መምረጥ ይችላሉ።

ጉዳፍ ፀጋይን #ላይክ / #ሪትዊት ለማድረግ ፦

ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/100064391421386/posts/pfbid0hS68YYaTusAL2g6TrYMbMuuW1pDFv2KBQbfcD4piPiJc3XU1iDyb45k6CKCf3bgYl/?app=fbl

X / የቀድሞ ትዊተር ላይ ሪትዊት ለማድረግ ፦ https://twitter.com/WorldAthletics/status/1712082175250563508?t=rpGi0sYnnozLQvDtN4RTKQ&s=19

ኢንስታግራም ፦ https://www.instagram.com/p/CyQkhc9Mry7/?igshid=NjIwNzIyMDk2Mg==

ትዕግስት አሰፋን #ላይክ / #ሪትዊት ለማድረግ ፦

ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/100064391421386/posts/pfbid01BPvP9Vb4sF7tRxmX2Lb5BqWDgXjFB17Agijp9vWQWsJufvbrkXL3yH7PZbidcaTl/?app=fbl

X / የቀድሞ ትዊተር ሪትዊት ለማድረግ ፦ https://twitter.com/WorldAthletics/status/1712082042391802157?t=xlF0PNgzEhsBxSb56pANlw&s=19

ኢንስታግራም ፦ https://www.instagram.com/p/CyQjzyRM8Iv/?igshid=NjIwNzIyMDk2Mg==

(ሼር ያድርጉ)

@tikvahethiopia