TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ድሬዳዋ ፖሊስ⬆️

በድሬዳዋ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች በቤቶች ላይ ምልክት መደረጉን ተከትሎ ምልክቱ የጥቃት ነው በሚል በማህበራዊ ድረ ገፅ #ስጋት
ፈጣሪ ሀሳቦች ተሰራጭተዋል። በመሆኑም የአስተዳደሩና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ከትላንት ጀምሮ #የተጠናከረ ጥበቃና ክትትል እያደረጉ
መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግኑኝነት ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ሳጂን ባንታለም ግርማ ገልፀዋል።

እስከ አሁን በተጨባጭ የተፈጠረ #ችግር የለም ያሉት ዋና ሳጂን ባንታለም ግርማ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ድረ ገፅ በሚለቀቁ መረጃዎች ተደናግሮ ለሁከትና ግጭት በር ሳይክፈት የለት ተለት ሠላማዊ ኑሮውን ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። ብጥብጥ ለመፍጠር የሚፈልግ አካል ካለም በድሬዳዋ #የማይሳካ መሆኑና ፖሊስም የማይታገስ መሆኑን አውቆ ከጥፋት ድርጊት እንዲታቀብ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡ ስጋት ፈጣሪ እንቅስቃሴዎች ባየ ጊዜ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም ዋና ሳጅኑ ጠይቀዋል፦

☞025 111 16 00
☞025 111 52 11

በተያያዘ ፦ ሀምሌ 29 - 2010 በድሬዳዋ ለ13 ንፁሀን ዜጎችና ህልፈትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ሁከት ተከትሎ ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት የፊታችን #ማክሰኞ ለሕዝብ በይፋ የሚገለጽ መሆኑን ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ አሳውቀዋል።

©Diredawa Mayoroffice
@tsegabwolde @tikvahethiopia