TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአዲስ አበባ ነዋሪዎች #ኢትዮ_ቴሌኮም ወደ እጅ ስልካቸው #በሚልክላቸው አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች ብዛት ተማረናል ብለዋል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮምና የተለያዩ ተቋማት አጫጭር መልዕክቶች ስልካቸውን ስለሚያጨናንባቸው አገልግሎቱን እስከማቆም የደረሱ መኖራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ብዙዎቹ መልዕክቶች የማይፈለጉ፣ የግል መብትን የሚጋፉ፣ ጊዜና ገንዘብንም የሚያባክኑ ናቸው፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ኮሚኒኬሽን ሃላፊ ጨረር አክሊሉ ግን ተጠቃሚዎች የማይፈልጓቸው መልዕክቶች እንዳይደርሷቸው የሚያደርግ አሰራር በቅርቡ እንጀምራለን ብለዋል፡፡ የብሄራዊ ሎተሪ በዕጣና ዕድል ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች መልዕክት እንዲያስተላልፉ ፍቃድ የሰጣቸው አሉ፤ ፍቃድ በሌላቸው ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ይቅርታ ጠይቋል!

#ኢትዮ_ቴሌኮም በሃገሪቱ ተዘግቶ የሰነበተው የፊክስድ ብሮድባንድ እና የሞባይል ኢንተርኔት የተቋረጠው ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት ተወስኖ እንደሆነ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል። በተገልጋዮች በኩል ለተፈጠረው መጉላላት እና ለደረሰው የኢኮኖሚ ኪሳራም #ይቅርታ ጠይቋል። የፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎቱ ከሰኔ 18 ጀምሮ መለቀቁን የገለጸው ኩባንያው የስልክ ኢንተርኔት በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ተለቋል ብሏል። ነገር ግን አሁንም የስልክ ኢንተርኔት የማይሠራባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ኩባንያው በበኩሉ እንዲህ ያለው ችግር እንዳይደጋገም ምን ይበጃል የሚለውን በመለየት የመፍትሄ እያፈላለገ መሆኑን ይናገራል።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት #መቆራረጥ ምክንያት ብቻ 204 ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገለጸ። ኢትዮ ቴሌኮም የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት በዚህ ጊዜ እንዳሉት በኢንተርኔት መቆራረጥ ምክንያት ብቻ 204 ሚሊዮን ብር አጥተናል ብለዋል።

ከዚህ በፊት በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ኢትዮጵያ በቀን 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች ተብሎ የወጣው ዘገባ ስህተት መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2011 በጀት ዓመት 36 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። የተገኘው ገቢ የእቅዱን 80 በመቶ ያሳካ ሲሆን ገቢው ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ7 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ወይዘሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል።

ድርጅቱ የደንበኞቹን ቁጥር 43 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን አገራዊ የቴሌኮም ስርጭቱ 44 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአገሪቱ የተወሰኑ አካባቢዎች የጸጥታ ሁኔታ አስጊ በመሆኑ የቴሌኮም አገልግሎቶች የግድ ማቋረጥ አስፈልጓል ይሄ ደግሞ በገቢው ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮብናል ሲሉ ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

Via #ኢትዮ_ቴሌኮም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"Our beloved Muslim brothers and sisters, may the peace and love of Allah embrace your life. Wishing you and your family a very Happy Eid. Eid Mubarak!" #Ethio_telecom #ኢትዮ_ቴሌኮም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#2 እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ተፍቀው ጥቅም ላይ በዋሉ የሞባይል ካርዶች ላይ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በሚፋቀው ቦታ ላይ ተመሳሳይ ቀለም ወይም ስቲከር በመቀባትና በመለጠፍ ጥቅም ላይ ካልዋሉ አዳዲስ ካርዶች ጋር በማመሳሰል ወደ ገበያ በማሰራጨት ደንበኞቻችንን እያጭበረበሩ መሆኑን ደርሰንበታል። ስለሆነም ክቡራትና ክቡራን ደንበኞቻችን የሞባይል ካርዶችን ስትገዙ በሚፋቀው የሚስጥራዊ ቁጥር ቦታ ከተለመደው የተለየ ቅብ ወይም ተለጣፊ ነገሮች አለመኖራቸውን አስተውላችሁ እንድትገዙ በተቻለ መጠን ካርዱን ከገዛችሁበት ቦታ ወዲያውኑ እንድትሞሉ እየጠየቅን ሂሳቡ በትክክል ከተሞላ በኃላ ካርዱን በመቅደድ በተገቢው የቆሻሻ መጣያ ውስጥ በመጣል ለአጭበርባሪዎች ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እንጠይቃለን።

#ETHI_TELECOM #ኢትዮ_ቴሌኮም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም “የቴሌብር ሱፐርአፕ” በማለት የሰየመውን ማዘመኛ በዛሬው ዕለት አስተዋውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ " ቴሌብር " መተግበሪያው ቀደም ሲል ለደንበኞቹ ሲያቀርብ ከነበረው አገልግሎት በተጨማሪ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችለውን “የቴሌብር ሱፐርአፕ” በማለት የሰየመውን ማዘመኛ በቴሌብር መተግበሪያው ላይ ተግባራዊ አድርጎ በዛሬው ዕለት አስተዋውቋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፋጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ የተለያዩ አካላትን (የቢዝነስ ተቋማትን፣ ሶፍትዌር አበልጻጊዎችን፣ Solution partner, Content provider) በማካተት የዲጂታል ኢኮኖሚን እየገነባ ነው።

ኃላፊዋ ተቋሙ የሞባይል መተግበሪያው ከገንዘብ አገልግሎቶች በተጨማሪ የተለያዩ መተግበሪያዎችን በውስጡ በመያዝ ለተገልጋዩ እንደሚያደርስ ነው የገለፁት።

በ " ቴሌብር ሱፐርአፕ " የተጨመሩ አዳዲስ አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው ?

- የታቀደ ክፍያ፦ የገንዘብ እና የአየር ሰዓት ለመላክ እንዲሁም ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀኑ ለመክፈል ቀድሞ ማቀድ የሚያስችል አገልግሎት

- የድል ጨዋታ፦ አጠቃቀምን መሰረት ያደረ፣ የአጓጊ ሽልማቶች ባለቤት የሚኮንበት ልዩ ጨዋታ ነው

- ለቡድን ገንዘብ መላክ፦ ከአንድ በላይ ለሆኑ ተቀባዮች አስቀድመው በሚሞሉት መስፈርት መሰረት በአንዴ መላክ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

- የተለያዩ መተግበሪያዎችን በአንድ ቦታ፦ የተለያዩ የአገልግሎት መተግበሪያዎችን መጫን ሳያስፈልግ በአንድ ቦታ ማግኘት የሚያስችል ነው። (ለምሳሌ:- የትራንስፖርት፣ እቁብ፣ ዴሊቨሪ፣ ኢ-ኮሜርስ፣ የትምህርት ወ.ዘ.ተ)

- የተለያዩ ዝግጅቶች/የበረራ ትኬቶችን መግዛት

መተግበሪያው የፋይናንስ እና መሰል አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት፣ ለቢዝነስ ተቋማት ደግሞ ተጨማሪ የስራ እድልን ይፈጥራል፣ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ጋር በቀላሉ እንዲገናኙ ያስችላል ተብሏል።

" ቴሌብር ሱፕርአፕ " መተግበሪያ በሁለተኛው ምዕራፍ የተለያዩ አዳዲስ አገልግሌቶችን ይዞ እንደሚመጣ ተጠቁሟል። " ቴሌብር ሱፐርአፕ "ን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር በማዘመን/በማውረድ መጠቀም ይችላሉ።

ቴሌብር ሁለት አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ 30 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራቱን ገልጿል።

ባለፉት 22 ወራት ብቻ ከ101 ሺ በላይ ወኪሎች፣ ከ28 ሺህ ነጋዴዎች እንዲሁም ከ19 ባንኮች ጋር ትስስርን የፈጠረ ሲሆን ከ44 አገራት ከ1.95 ሚሊዮን ገቢ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ባስጀመረው የዲጂታል ፋይናንስ የብድርና የቁጠባ አገልግሎቱ በቴሌብር መላ የብድር አገልግሎት ለ1.4 ሚሊዮን ተጠቃሚዎቹ 2.1 ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን 400 ሺ የቴሌብር ሳንዱቅ የቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚዎቹ 1.7 ቢሊዮን ብር እንዲቆጥቡ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

በቴሌብር ሱፐርአፕ በፊት ገፅታ ወይም በጣት አሻራ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ አገልግሎት ያግኙ!

አዲሱ የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ በፊት ገፅታዎ ወይም በጣት አሻራዎ የሚሰራ ባዮሜትሪክ የደህንነት ማረጋገጫ ስላለው ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አካውንትዎ ከደህንነት ስጋት ነፃ ነው፡፡

መተግበሪያውን ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ለትንሳኤ በዓል ከባህር ማዶ ከወዳጅ ዘመድ በአጋሮቻችን #Talkremit #Worldremit #Azimo #MasterRemit #Majority #Moneytrans #Remitly #ria #Taptapsend በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ ያለ ውጣ ውረድ እና እንግልት ባሉበት ሆነው በቴሌብር ሲቀበሉ የተላከልዎትን ገንዘብ መጠን 5% እንዳሻዎ ለማንኛዉም ክፍያ ሊጠቀሙ የሚችሉበት የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ

ቴሌብር ሃዋላ የሩቁን ያቀርባል!
መልካም በዓል
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ትንሳኤ ጥቅል እስከ 50% በሚደርስ ቅናሽ ከ1ጊ.ባ ዳታ ስጦታ ጋር !

እንደ ወግ ልማዳችን እንኳን አደረሰን የምንባባልበትን ልዩ የትንሳኤ የሞባይል ጥቅል እስከ 50% በሚደርስ ቅናሽ ከ1ጊ.ባ ዳታ ስጦታ ጋር ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን!

ልዩ የትንሳኤ ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል እና *999# ለራስዎ በመግዛት እና ለወዳጅ ዘመድ በስጦታ በማበርከት በዓሉን በደስታ ያሳልፉ!

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ኢድም አይደል፤ ታዲያ ባህርማዶ ያለ ወዳጅ ዘመድ የበዓል ስጦታ በአጋሮቻችን #Talkremit #Worldremit #Azimo #MasterRemit #Majority #Moneytrans #Remitly #ria #Taptapsend በኩል ሲልክልዎና ያለ ውጣ ውረድ እና እንግልት ባሉበት ሆነው በቴሌብር ሲቀበሉ፤

እንዲሁም በዌስተርን ዩኒየን ሃዋላ የተላከልዎትን ገንዘብ በአገልግሎት ማዕከሎቻችን ሲቀበሉ እና ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ሲያስተላልፉ፤

የተላከልዎትን ገንዘብ መጠን 5% እንዳሻዎ ለማንኛዉም ክፍያ ሊጠቀሙ የሚችሉበት የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ

ቴሌብር ሃዋላ የሩቁን ያቀርባል!
ኢድ ሙባረክ!
#ኢትዮ_ቴሌኮም

በነዳጅ ማደያዎች በፍጥነት መስተናገድ ይችሉ ዘንድ ማድረግ ያለብዎትን ቅድመ-ዝግጅቶች እናስታውስዎ

⛽️ የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 በማውረድ ወይም በ*127# የቴሌብር አካውንት መክፈት

⛽️ ከቴሌብር ጋር ከተሳሰሩ 20 ባንኮች በሞባይል ባንኪንግ፣ በቴሌብር ወኪሎች እና በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከሎች ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ያስተላልፉ፡፡

⛽️ ቴሌብር ሱፐርአፕን ሲጠቀሙ ቪ.ፒ.ኤን (VPN) እየተተቀሙ ከነበረ ያጥፉ

⛽️ ለተጨማሪ ድጋፍ ወደ 127 ይደውሉ ወይም በጽሁፍ ወደ 126 ወይም የቴሌብር ማህበራዊ ገጾቻችን ጥያቄዎን ይላኩ

ማስታወሻ: የነዳጅ ክፍያ በቴሌብር በመፈጸምዎ ምንም አይነት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም።

ለተጨማሪ መረጃ bit.ly/3V3wjPF