እኛስ❓
የጥንት አባቶቻችን ያለብሄር፣ ያለዘር፣ ያለቋንቋ፣ ያለሀይማኖት ልዩነት ወራሪውን የጣልያን ጦር አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው፤ በደም በአጥንታቸው ይህቺን ሀገር #አስከብረው ለኛ #አስረክበውናል።
የዛሬዎቹ ትውልዶች እኛስ❓ለቀጣዩ ትውልድ ምን ይሆን የምናወርሰው? የትኛዋን ሀገር ነው የምናወርሰው?
ወገኖቼ ለመጪው ትውልድ ክፍፍል እናውርስ? አንድ የሚያደርገንን ሰውነትን ረስተን በብሄር መቧደንን ለልጆቻችን እናውርስ? ንገሩኝ...በዘር መከፋፈልን እናውርስ? አለመከባበርን እናውርስ?? መሰዳደብን እናውርስ? ቁጭ ብሎ ማውራትን እናውርስ? አለመደማመጥን እናውርስ?
ቆይ ምን ሰርተን አለፍን እንበል❓
አድዋ የነፃነት ምልክት ብቻ አይደልም፤ አድዋ የኢትዮጵያዊያን #አንድነት እና ጠንካራ #ትስስር መገለጫም ጭምር ነው።
አድዋን ስናከብር...እኛስ ለቀጣዩ ትውልድ ምን እናውርስ? እኛስ ለኢትዮጵያ ምን ሰርተን እንለፍ? የሚሉትን ጥያቄዎች እራሳችንን #እየጠየቅን መሆን አለበት።
በTIKVAH-ETH ስም ሁላችሁንም እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ!
ሰላም፤ ፍቅር፤ አንድነት!
#Adwa123 #አድዋ123
@tsegabwolde @tikvahethiopia