TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቱ🔝

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ ከኦሮሚያ ክልል ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ለማ_መገርሳ ጋር በመሆን ከኢሉባቡር ዞን ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ ተከፍቷል...

ትናንት ተዘግቶ የዋለው የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ ዛሬ ተከፍቷል። በአካባቢው #መረጋጋት የሚታይ ሲሆን፣ በታጣቂዎች ቁልፍ የተነጠቁ ተሽከርካሪዎች አልፎ አልፎ መንገድ ዘግተው/ቁመው ይታያሉ።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምርመራው ውጤት...

የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ምርመራ ውጤት የመጀመሪያ ሪፖርት ይፋ ሆነ።

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ምርመራ ውጤት የመጀመሪያ ሪፖርት ይፋ ተደርጓል።

የምርመራ ውጤቱን ይፋ ያደረጉት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ምርመራው በሚኒስቴር መ/ቤቱ በተቋቋመው የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮና ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው የአውሮፕላኑ አምራችና ዲዛይነር ጋር በጋራ ተሰርቷል ብለዋል።

በዚህም መሠረት፦

1/ አውሮፕላኑ የፀና መብረር የሚያስችል ሰርተፍኬት ያለው መሆኑ

2/ አብራሪዎቹ በረራውን መምራት የሚያስችል ብቃትና ፈቃድ ያላቸው መሆኑ

3/ አውሮፕላኑ ለበረራ ሲነሳ በትክክለኛው መስመር ለመብረር የሚያስችል ይዞታ እንደነበረው

4/ አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ቢጥሩም መቆጣጠር ግን አለመቻሉ በምርመራው ተረጋግጧል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አውሮፕላን #ከበረራ_በፊት ደህንነትቱ የተጠበቀና አነሳሱም ቢሆን ትክክለኛውን አቅጣጫ የተከተለ እንደነበር የአውሮፕላን ምርመራ ቡድኑ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ክንዱ ገዙ ከአሜሪካ ባሕር ኃይል የአፍሪካ አዛዥ አድሚራል ጄምስ ጎርደን ፎጎ ሶስተኛ ጋር ተገናኝተዋል። ሁለቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹማምንት "ፈታኝ ግን ደግሞ አስደሳች" በተባለው የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ግንባታ ላይ መወያየታቸውን ተገልጿል። መረጃውን በትዊተር ያጋራው የአሜሪካ የባሕር ኃይል የአውሮፓ እና የአፍሪካ እዝ ሁለቱ ዕዞች ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን አስታውቋል።

Via እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የአዲስ_ፓርቲ ምስረታ ገና አላለቀም 108+ #Loading...

Via Endalkachew E. Maraso
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው🔝

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ እንዲሁም የዋይት ሀውስ አማካሪ የሆኑት #ኢቫንካ_ትራምፕ በአፍሪካ የ4 ቀናት ጉብኝት ሊደርጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢቫንካ ትራምፕ ጉብኝት ከሚመሩት ዓለም አቀፍ የሴቶች ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ ወደ አፍሪካ የሚመጡት በያዝነው #የኤፕሪል ወር፤ መዳረሻዎቻቸውም #ኢትዮጵያና #አይቮሪኮስት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ በአይቮሪኮስት ቆይታቸው ትኩረቱን በሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ ላይ አድርጎ በአገሪቱ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሁለቱም አገራት የመስክ ጉብኝቶችን እንደሚያደርጉና ከፖለቲካ መሪዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ ተገልጿል፡፡

ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መሪዎችና በስራ ፈጠራ ላይ ከተሰማሩ ሴቶች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ኤቢሲ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ጋር በተያያዘ የተጎጅዎችን ጉዳይ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ እየተከታተለው መሆኑን የትራንስፖርት ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ ሚንስትሯ ወ/ሮ #ዳግማት_ሞገስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስፈላጊ መረጃዎችን በማጠናቀር ከአውሮፕላን አደጋው ጋር በተያያዘ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ጉዳይ በቅርበት በመከታተል ላይ መሆኑን በዛሬው ዕለት ገልፀዋል፡፡ ከአደጋው በኃላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰ አሉታዊ ተፅዕኖ አለ ወይ ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ፣ አየር መንገዱ ያለምንም ችግር መደበኛ ስራውን እያከናወነ መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ🛬ባህር ዳር🔝

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ወደ ባሕር ዳር አቅንተዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎችም በባሕር ዳር ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የፈለገ ሕይዎት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የኦክስጅን ማምረቻን እንደሚመርቁ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia