#MinistryOfPeace
ለሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጥ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ሽልማት በሰላም ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ተሰጥቷል፡፡ የሰላም ቤተሰቦች መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሸልመዋል።
https://telegra.ph/ETH-10-21-2
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በአፋር ክልል እና በሶማሌ ክልል መካከል የተፈጠረ ችግር በውይይት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሰላም ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ዘላቂ መፍትሔ ዳይሬክተር ጄኔራል ምግባሩ አያሌው እንደገለፁት ሚኒስቴሩ ወደ ሁለቱ ክልሎች የላከው የልዑካን ቡድን የሁለቱን ክልሎች የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንስ ለማካሄድ ከስምምነት ደርሰዋል።
ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሰው ግብረ ኃይል ለችግሩ እልባት ለመሻት መጠነ ሰፊ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተር ጀኔራሉ ፣ የመፍትሄ ሃሳቦች ጎን ለጎን በመሰጠት እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አክለዋል። በዋናነት ለችግሩ እልባት ተሰጥቷል፤ በቀጣይነት ዘላቂ የሆነ ሰላም በአካባቢው እንዲኖር የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰራም ተናግረዋል።
Via EBC

የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ ስርዓት አካል የሆነው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ስራ ሊገባ እንደሆነ አብስሯል።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የቅድመ ማስጠንቀቂያው ስርዓት ማህበረሰቡን ከተለያዩ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ስርዓቱ የሙከራ ጊዜዉን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናቶች ውስጥ አገባዶ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ይገባል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Metekel
በመተከል ዞን ከ97 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
ከ58 ሺ በላይ ዜጎች ግልገል በለሰ ከተማ ይገኛሉ ፤ 39 ሺህ 679 ተፈናቃዮች በአማራ ክልል አዊ ብሔርስብ አስተዳደር በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ይገኛሉ።
ዜጎች ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ ያተደረገ ድጋፍ ፦
• በግልገል በለሰ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ33 ሺ ኩንታል በላይ ስንዴ ፣ 4 ሺ 38 ኩንታል ዓልሚ ምግብ እና 187 ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
• አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈናቃዮች 3 ሺህ 404 ኩንታል ስንዴ እና 10 ሺህ 316 ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
ይህ ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ የምግብ እህልና ቁሳቁስ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ለአብመድ አሳውቋል። #MinistryOfPeace
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#MinistryofPeace
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ዶክተር አኔቴ ዌበር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይየታቸው ወ/ሮ ሙፈሪያት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ልማት በተለያዩ መስኮች እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ አመስግነዋል።
ዶ/ር አኔቴ ዌበር በበኩላቸው፥የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም ዘመናት የቆየውን መልካም የዲፕሎማሲያዊ እና የልማት ትብብር ለመቀጠል ያለውን ጠንካራ ፍላጎት መግለጻቸውን የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።
@tikvahethiopia

" ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በመንግሰት በኩል ይከፈላል " - አቶ መሀመድ እድሪስ
ዛሬ የሰላም ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ጋር ተገናኝተው በመንበረ ፓትርያርክ መወያየታቸው ተሰምቷል።
በቅርቡ የተሾሙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር የትውውቅ ፕሮግራም አድርገዋል።
በዚህም ወቅት በሀገሪቱ የተጀመሩ የሰላም ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ላይ የጋራ ምክክር ማድረጋቸውን ሰላም ሚኒስቴር አመላክቷል።
ሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በአገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩም ተገልጿል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተ-ክርስቲያኗ ከመንግስት ጋር በመደጋገፍና በመቀራረብ በሰላም ዙሪያ ከመቼውም በላይ በትጋትና በመቀራረብ እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።
አዲሱ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ለትውውቅና ለመወያየት ወደ መንበረ ፓትሪያርክ መምጣታቸውንና ላሳዩት የአመራር ትህትና አድናቆትና ምስጋና እንዳቀረቡላቸው ተገልጿል።
አቶ መሀመድ ፤ " አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት ቤተ-ክርስቲያኗ በሰላምና በሀገረ መንግሰት ግንባታ ካላት የካበተና የዳበረ ልምድ በመነሳት በአሁኑ ሰዓት እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ አገራዊ የሰላም ፀሎት እና ጥሪ እንዲደረግ " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
" ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በመንግሰት በኩል ይከፈላል የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶችና ተቋማት ጋር በትብብርና በመደጋገፍ ይሰራል " ሲሉ አረጋግጠዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
" ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በመንግሰት በኩል ይከፈላል " - አቶ መሀመድ እድሪስ ዛሬ የሰላም ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ጋር ተገናኝተው በመንበረ ፓትርያርክ መወያየታቸው ተሰምቷል። በቅርቡ የተሾሙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር የትውውቅ ፕሮግራም…
" የሐይማኖት ሐገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር የለባቸውም ! " - የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ
የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ሚኒስትሩ በሰላም ግንባታና በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ምን አሉ ?
- መጅሊሱን ለመጎብኘት ሚኒስትሩ መምጣታቸው በራሳቸው እና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።
- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሙስሊሙን አንድነትና የሐገራችንን ሰላም ለማጠናከር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ጅምሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
- ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቀጣይ በሚያካሄደው የመጅሊስ ምርጫ መንግስት በተለይ የሰላም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ምን አሉ ?
° በዓለም መድረክ ላይ የሃገራችንን ኢትዮጵያን ስም ከፍ ለማድረግ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እየሰሩ ያሉትን ስራ አድንቀዋል።
- በአፋርና በሱማሌ ወንድም ሕዝቦች መካከል የነበረውን የቆየ አለመግባባትና ግጭት ለመፍታት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሰራው ስራ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይ ሁሉ አቀፍ የሰላምና የልማት ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
° የሐይማኖት ሐገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር እንደሌለባቸው ተናግረዋል።
° ጠቅላይ ምክር ቤቱ አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት ፣እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ሀገራዊ የሰላም ጥሪና ዱዓ በጁምዓ ሰላት ላይ የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
° መንግስት ግጭቶች በንግግር እንዲፈቱ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ያቀረበ እና ለዚህም ቁርጠኝነቱ ያለው መሆኑን ገልጸው የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶችና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አመልክተዋል።
° መጭው የመጅሊስ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

" የሐይማኖት ሐገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር የለባቸውም ! " - የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ሚኒስትሩ በሰላም…
" የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና አለው " - አቶ መሀመድ እድሪስ
የሰላም ሚኒስትር ከሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ጋር እያደረጉ ያሉትን ትውውቅና ውይይት ቀጥለው ዛሬ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር ተገናኝተዋል።
በዚህም ወቅት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ፥ " የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና አለው " ብለዋል።
" በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳይ ሰላማዊና የተረጋጋ ማህበረሰብ እንዲኖር የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ አስተዋፆ ሊኖራቸው ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በቀጣይ በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተው የሰላም ሚኒስቴርም በትብብርና በቅንጅት ከካውንስሉ ጋር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ፤ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ፥ ከመገፋፋት ይልቅ በመተባበር እና በመደጋገፍ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሃይማኖቶች ትልቅ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ሲሰራ የቆያቸውን የሰላም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በሀገራችን ሰላም ጉዳይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነ አሳውቀዋል።